Site icon ETHIO12.COM

የትህነግ አመራሮች ሙሉ በሙሉ ወደ አገረ ሰላም ዋሻ ለመመለስ ተዘጋጅተዋል

ወደ አማራና አፋር ክልል በመዝለቅ የውጊያ አድማሱን በማስፋት አዲስ አበባ ለመግባት የሚያግደው ሃልይ እንደሌለ ሲያስታውቅ የነበረው የትህነግ ሃይል ሙሉ በሙሉ ወደ ቀድሞ ምሽጉ ለመመልስ ዝግጅት ላይ መሆኑ ተሰማ። በግንባር ውሎ የመንግስት ሃይሎች እየቀናቸው መሆኑን በዝርዝር እያስትወቁ ነው። ቀኑ ባይቆረጥም ሙሉ ማጥቃት የሚጀመረበት ቀን የተቃረበ እንደሆነ እየተገለጸ ነው።

የኢትዮ12 የአሜሪካ ተባባሪ ከቅርብ የትህነግ ከፍተኛ አመራሮች መስማቱን ጠቅሶ እንዳለው፣ የጦር ሜዳው ዘመቻ በሚፈለገው መልኩ ባለመሄዱ ለጥንቃቄ አመራሩ ወደ ቆላ ተምቤን ሙሉ በሙሉ ፊቱን ለማምራት ዝግጅት ላይ ነው።

የችግር ጊዜ ማለፊያ በሆናቸውና ቀደሞ በበረሃ እያሉ በቆረቆሩት የአገረ ሰላም ዋሻዎች ከቆዩ በሁዋላ ወደ መቀለ የተመለሰው ትህነግ አልፎ አልፎ ብቅ መለስ ከማለት ውጪ በዋናው የክልሉ መስተዳደር ቢሮ ስራ እንደማያከናውንበት ቀደም ሲል ይታወቃል። ስብሰባዎችና የኮሚቴ ስራዎች በአሳቻ ቦታዎችና በማይገመቱ ስፍራዎች እንደሚያካሄዱ ቀደም ብሎ መዘገቡ ይታወሳል።

ከአየር ጥቃት ሊደርስ እንደሚችል በመስጋት የሚታወቀውን የክልሉን ቢሮዎች በነጻነት ከፍተኛ ባለስልጣናት እንደማይጠቀሙበት የነገረን ተባባሪያችን፣ አሁን ላይ ባልተጠበቀ ሁኔታ የተነሳው የህዝብ ማዕበልና የመከላከያ ሰራዊት ዳግም በሁሉም አቅጣጫ መጠናከር ስጋት ፈጥሯል። በተለይም በአፋር ግንባርና በራያ ግንባር የመከላከያ ሰራዊት ወደ ትግራይ ዘልቆ መግባቱ በትህነግ ዘንድ ድንጋጤውን ከፍ አድርጎታል።

አሶሲየትድ ፕረስ “የፌደራል ሃይሎች” ያላቸው መከላከያ፣ ልዩ ፖሊስ፣ ሚሊሽና የአካባቢ አርበኞች ማይጨውን እና አምባላጌን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠራቸውንና ወደ መቀለ ለመንደርደር የሚያመቻቸው መሆኑንን ዘግቧል። ዘገባው ” ባለኝ መረጃ መሰረት” ብሎ እንዳለው በርካታ ቦታዎችን ይዞ የነበረው ትህነግ፣ ኮረም፣አላማጣ፣ ቆቦ ከተማ ያለው ሃይሉ መቀለ ካለው ማዘዣ ጣቢያው ጋር እንዳይገናኝ ተደርጎ መቆረጡን ይፋ አድርጓል። ከስር ሊንኩን ተጭነው ያንብቡ።

The federal forces of Ethiopia on Friday took control of Maychew and Ambalagie, strategic towns in south Tigray region after they began a rolling counterattack back toward the capital, Mekelle.Information reaching APA revealed that fighters of the rebel Tigray People’s Liberation Front (TPLF) who took control of various towns including Korem, Alamata, Korem and Kobo towns have been cut off from their command center in Mekele, capital of Tigray region.

በአፋር ግንባር ከፍተኛ የሰው ሃይል እንዳጣ፣ የያዛቸውን ቦታዎች መልቀቁ ይፋ በሆነ ማግስት ” ለአፋር ወንድሞቻችን አዝነን ዘመቻውን ሰርዘነዋል” ሲል ምክንያት የሰጠው ትህነግ፣ በይፋ ባያምንም በግንባሩ ከፍተኛ ዋጋ እንደከፈለ በአፈ ቀላጤው አማካይነት አስታውቋል። አፈ ቀላጤ ጌታቸው ጉዳቱንና ኪሳራውን በዝርዝር አላስታወቁም።

በምዕራብ ግንባር በተደጋጋሚ የሱዳንን ኮሪዶር ለማስለቀቅ ሙከራ ያደረገው የትህነግ ሃይል አስራ ሶስት ጊዜ የተመከተ ሲሆን አሁን እንደሚሰማው ከሆነ በዛም በኩል ጥቃት ሊጀመር እንደሚችል ምልክት ተሰጥቷል። በጋይንትና በጉና ተራራ ያለው ጦርነትም በህዝብ ተጋዳይነት መልኩን እየቀየረ፣ “ትህነግ ያሰለፈው መንጋ ቦታ የመያዝ ሳይሆን ተንጠበጥቦና ተበጣጥሶ ሊጥና ሌማት ስርቆት፣ ቆርቆሮና የበር ደፍ ማውለቅ ውስጥ ገብቷል። የሰው ሃይል አስገብቶ ማገዝ አልቻለም” ሲሉ የአካባቢው አስተዳደር ወቅታዊ መረጃ ሰጥተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ” ጠላት እጃችን ውስጥ እየገባ ነው” ባሉ ቀናት ውስጥ ከስፋራው የሚወጡ መረጃዎች የተበጣጠሰው ሃይል መውጫ ማጣቱን የሚገልጽ፣ የሰው ማእበል አስነስቶ በወረረበት ስፍራ ሁሉ መፈናፈኛ ማታቱና፣ አርሶ አደሩ እየመከተና ትጥቅ እያስፈታ እንደሆነ ነው። በትህነግ በኩል በሁለት ቀናት ውስጥ ባህር ዳርና ጎንደር እንደሚገቡ አቶ ጌታቸው ቢያስታውቁም ዛሬ ሶስተኛ ቀን ሲሆን የት እንደደረሱ ያሉት ነገር የለም።

እንደ አሶሲየትድ ፕሪስ መረጃ ወደ መቀለ ለመብረር አንድ ከተማ ( መሆኒ) ብቻ የሚቀረው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከአራቱም አቅጣጫ ” አፍ የሚያሲዝ” ያለውንና በቅርቡ እንደሚያሳይ ያስታወቀውን ድል ፍርሃቻ ይሁን የስትራቴጂ ለውጥ ባይታወቅም ትህነግ ወደ ቀድሞ በረሃ ሊመልስ ዝግጁ መሆኑ ታውቋል።

ሱዳን ካሉ የድርጅቱ ባለስልጣን ጋር እንድተነጋገረች ጠቅሳ ለተባባሪያችን ያስረዳቸው እንዳለችው ” እነ ጀነራል ጻድቃን ከአገረ ሰላም ቢወጡም መቀለ አይቀመጡም። መቀለ ያሉትም ቢሆኑ ቋሚ አድራሻቸው አይታውቅም። ስፍራ እየቀያየሩ ነው የሚሰሩት፣ የሚተኙት፣ የሚሰበሰቡት። አሁን ግን ሙሉ በሙሉ በድንገት ወደ ቀደሞ ቦታ ለመመለስ ሎጅስቲክና አንዳንድ የጎደሉ ነገሮች እየተሟላ ነው”

ይህንን መረጃ አስመልክቶ የአዲስ አበባ ዘጋቢያችን ያነጋገራቸው ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ እንዳሉት አሁን ላይ ወደ አገረ ሰላም ዋሻ የመግባት ውሳኔ ስለመኖሩ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ አስታውቀው፣ ” ዳግም የሚሸወድ የለም” ብለዋል። ማብራሪያ ከመስጠትም ተቆጥበዋል።

Exit mobile version