ETHIO12.COM

አሸባሪው ለህዝቡ ሊደርስ የሚገባውን ሀይል ሰጪ ምግብ እንዴት አገኘ?

ዩኤስኤይድና ከአሸባሪው ታጣቂ የተገኘው ሃይል ሰጪ ምግብ ጉዳይ!

ከአሸባሪው ህወሃት አባል እጅ ሃይልና ሙቀት ሰጪ ምግቦች ተገኝተዋል።

እነዚህ ሃይልና ሙቀት ሰጪ ምግቦች ዓለምአቀፍ የእርዳታ ደርጅቶች “ለትግራይ ህዝብ እናከፋፍላለን” ብለው ወደ ትግራይ የወሰዷቸው ናቸው።

መንግስት የተናጠል ተኩስ አቁም አድርጎ ከትግራይ ክልል ከወጣ በኋላ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ የሰብዓዊ እርዳታዎችን ሙሉ ለሙሉ እያቀረቡ ይገኛሉ።

አምስት ዓለምአቀፍ ድርጅቶችም ለተረጂዎች ሰብዓዊ እርዳታ እያደረሱ እንደሆነም ይታወቃል። ጥያቄው የአሸባሪው ህወሓት አመራር ለህዝቡ ሊደርስ የሚገባውን ሀይል ሰጪ ምግብ እንዴት አገኘ? ከሚለው ያልፋል።

ከአሜሪካ ህዝብና ከተቀሩ አገራት ህዝቦች “ለተረጂዎች” በሚል ሽፋን በሚሰበሰብ ገንዘብ አሸባሪዎችን የመቀለብ ያልተገባ ተግባር እንዴት ተፈፀመ ብሎም ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሊጠይቅ ይገባል።

የብሄራዊ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽነር ምትኩ ካሳ ስለጉዳዩ እንዳሉት፤ ”አምስቱ የእርዳታ ድርጅቶች በተሰማሩባቸው አካባቢዎች የሰጧቸውን እርዳታዎች ለተረጂው መድረሱን የማረጋገጥ ግዴታ አለባቸው”።

እነርሱ ግን ይህን ግዴታ አላከበሩም። ለትግራይ ህዝብ የእርዳታ ምግቡ በትክክል የመድረሱን ጉዳይ ሳያረጋግጡና ግዴታቸውን ሳይወጡ መንግስት ለመውቀስ ተደጋጋሚ ሙከራ እድርገዋል።

ሀቁ ይህ ሆኖ ሳለ፣ የአሜሪካ ተራድዖ ድርጅት (ዩኤስኤድ) ዋና አስተዳዳሪ ሳማንታ ፓወር መንግስትን በተደጋጋሚ በምግብ አቅርቦት በኩል ሲወቅሱ ይሰማሉ። ሰሞኑን እንኳን የዕርዳታ ሰራተኞች “ለተቸገረው ሕዝብ የሚያቀርቡት ምግብ ተሟጦ እያለቀ ነው” በማለት መግለጫ ሰጥተዋል። ከአሜሪካ ህዝብ የተላከውን እርዳታ አሸባሪው የህወሃት ታጣቂ እጅ እየደረሰ እንዴት አያልቅ? የሚለውን ጥያቄ ማንሳት ግድ ይለናል።

የወይዘሮ ሳማንታ ክስ ምንጩ ለትግራይ ህዝብ አዝነው ያለመሆኑን በከሃዲው ኮሎኔል እጅ የተገኘውን ማስረጃ ዋቢ ማድረግ ይቻላል።

ከሃዲው ኮሎኔል እንዴት ሃይል ሰጪ ምግብ አገኘ?

በአማራ ክልል ጋሳይ ግንባር ጦርነት ተካሄደ። በዚህ ግንባር በጀግንነት የተፋለሙት ድል ነሱ፤ አሸባሪው ህወሃት ቡድን ተደመሰሰ፤ ከፊሉ ሸሸ፣ አቅም ያጠረውም ተማረከ። ከተማረኩት መካከል ከሃዲው ኮሎኔል ገብረህይወት ገብረአላፍ ይገኝበታል።

ከሃዲው ኮሎኔል አራት መታወቂያ ይዟል።

“አገር ለማፍረስ ተልዕኮ ተሰጥቶኛል” ሲል የተናገረው ከሃዲው ኮሎኔል፤ የአሸባሪውን ህወሃት ተልእኮ ለማሳካት ራሱን እየቀያየረ ከቦታ ወደ ቦታ እንደሚዘዋወር መታወቂያው አመላካች ነው።

ከሃዲው ኮሎኔሉ፣ በጋሳይ ግንባር ሲማረክ እጁ ላይ ከተገኙት መታወቂያዎቹ በተጨማሪ ለየት ያለውና የሰውን ትኩረት የሚይዘው የሚመገባቸው በሃይል ሰጪነት የበለጸጉት የታሸጉ ምግቦቹ ናቸው።

ምግቦቹ በአሸባሪው ህወሃት የተሳሳተ አጀንዳ መከራና ስቃይ እየተቀበለ ላለው የትግራይ ህዝብ በእርዳታ የተላኩ መሆናቸው በማሸጊያቸው ላይ ከተለጠፈው ስያሜ መረዳት አያዳግትም።

ለትግራይ ህዝብ “እርዳታ ማድረስ አልቻልንም” እያሉ የሚከሱት ዓለም አቀፍ ተቋማቱ ከህዝቡ አልፎ የአሸባሪው ሕወሃት ታጣቂ እጅ የሃይል ሰጪ ምግቡ እስከሚደርስ የት ነበሩ? ወይስ የዚህ ሴራ አካል ናቸው? የሚለው በፅኑ ሊጠየቅ ይገባል። ይህ ጥያቄ ምላሽ ማግኘት አለበት። ለእርዳታ የሄደ ሃይል ሰጪ ብስኩት ከአሸባሪው እጅ መገኘቱ ድጋፉ ለትግራይ ህዝብ ሳይሆን ሽብር እየፈፀሙ ላሉ ታጣቂዎች እየደረሰ ስለመሆኑ አረጋጋጭ ነውና።

በጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት የተማረከው ከሀዲው ኮሎኔል ለአንድ ቤተሰብ የሚሆን ሃይል ሰጪ ምግብ ይዞ መገኘት የሚያሳየው የእርዳታ ሂደቱ ላይ ችግር መኖሩን ነው። የአሸባሪ ህወሃትን እድሜ ለማራዘም ለህዝብ መሰጠት ያለበት ምግብ እየተከፋፈለ የጦርነቱን እድሜ ለማራዘም የሚሰራ ደባ መኖሩንም ያመላክታል።

በሳምንቱ መጨረሻ ላይ “የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦቱ በአስከፊ ሁኔታ አሁንም በቂ አይደለም” ያሉት ሳማንታ ለተፈጠረው ችግር የኢትዮጵያን መንግሥት ቢወቅሱም፤ ጀግናው ሰራዊት በተቆጣጠረባቸው አካባቢዎችና ከተማረኩት የአሸባሪው ህወሃት ታጣቂዎች የሚገኘው በንጥረ ነገር የበለጸገ ሃይል ሰጪ ምግብ ጉዳዩ የተለየ መልክ እንዳለው ያንጸባርቃል።

ለነገሩ እነዚሁ ሀላፊዎች በአሸባሪው ህወሃት ታጣቂዎች ህይወታቸው የሚቀጠፍ ንጹሃንን ሁኔታ የማይጠቅሱ፣ በአማራና አፋር ክልሎች የተፈናቀሉ ዜጎች ጉዳይ የማይገዳቸው መሆናቸውን በተግባር አሳይተዋል።

ይልቁንም ዓላማቸው በሰብዓዊ እርዳታው የሚገኘው ሃይል ሰጪ ምግብ አሸባሪው ህወሃት እንዲጠቀምበት ያለመና “ለትግራይ ህዝብ እርዳታ አልደረሰውም” በሚል ሰበብ ኢትዮጵያ ውስጥ ትርምስ እንዲፈጠር የማድረግ ተግባር ነው።

ኮሚሽኑ የእርዳታ አቅርቦት ሪፖርት እርዳታውን ከሚያከፋፍሉት ተቋማት የመቀበል፣ የመቆጣጠር ሃላፊነት አለበት፤ ይህን ምን ያህል ሰርቷል?

“በአዲሱ አወቃቀር ሪፖርት ማቅረብ ይገባቸዋል። ሪፖርት እንዲያቀርቡ እየተነገራቸው ቢሆንም አላቀረቡም። እስከአሁን እርዳታውን ለማን እንደሰጡ እንዴት እንዳከፋፈሉ የሚታወቅ ነገር የለም” በማለት ኮሚሽነር ምትኩ ይናገራሉ።

የራሱን ሃላፊነት በአግባቡ ያልተወጣ ዓለምአቀፍ ተቋም እንዴት ሌላውን መውቀስ ይችላል? ለእርዳታ የመጣውን ለአሸባሪው እንዲደርስ እየሰሩ አልደረሰም ብሎ መጮህ አድሏዊነትን በጉልህ ያንጸባርቃል። የሳማንታ ጩሄትም ባህሪው ይህ ነው።

በአሁኑ ወቅት መንግስት የፍተሻ ጣቢያዎችን የስራ ጫና ለማቃለልና ፍጥነት እንዲኖረው ለማድረግ እየሰራ ነው። እነርሱ የመንግስትን ስራ ከመደገፍ ይልቅ ለአሸባሪው ህወሃት ተቆርቋሪነታቸውን በተናበበ መልኩም እያሳዩን ነው። viaENA

Exit mobile version