ETHIO12.COM

ኤርሚያስ ለገሰና ጌታቸው ረዳ የስልክ ግንኙነት እንዳላቸው ተሰማ 360ና ኤርሚያስ ወዴት?

የቀድሞው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ መንግስት የኮሙኒኬሽን ሚኒስትር ዳኤታ የነበረው ኤርሚያስ ለገሰ ከአቶ ጌታቸው ረዳ ጋር በተናጠል ግንኙነት እንደሚያደርግ መታወቁ ተሰማ። ቀደም ሲል ጀምሮ ” እረኛውን ምታ በጎቹ ይበተናሉ” በሚለው የዲጂታል ወያኔ መዋቅር የሚፈሰውን “የተመረጠ ቃል” እንደሚጠቀም የሚናገሩ በዜናው እንዳልተገረሙ ገልጸዋል።

በ360 “ዕለታዊ” ዝግጅት ላይ ከሃብታሙ አያሌው ጋር በጣምራ ላለፉት ሁለት ዓመታት የትህነግን አቅጣጫ እንደሚያራቡ የከሷቸው የነበሩ ሃብታሙም ሆነ ኤርሚያስ ከትህነግ ጋር ግንኙነት እንዳላቸው በተለያዩ አውዶች ሲናገሩና ሲጽፉ እንደነበር ይታወሳል።

የኢትዮ 12 የአሜሪካ ተባባሪ እንዳለው ቀደም ሲል ከተለመደው አግባብ በተለየ ኤርሚያስ ተደብቆ ለብቻው ከጌታቸው ረዳ ጋር በስልክ እንደሚገናኝ ሃብታሙ አያሌው አውቋል። ሰሞኑንን እየተካረሩ የመጡትም በዚሁ ምክንያት ነው።

ዘወትር አንዱ ሌላኛውን እየደገፉ መንግስትን፣ በተለይም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን ከሕዝብ ለመነጠል ዘመቻ ሲያካሂዱ የሚታወቁት ሃብታሙና ኤርሚያስ፣ ባለፈው ዓርብ ዱላ ቀረሽ ዘለፋ ውስጥ የገቡበት ዋና ምክንያት ኤርሚያስ ሃብታሙን ዘሎ በድብቅ ከጌታቸው ረዳ ጋር መግጠሙ እንደሆነ ተባባሪያችን አመልክቷል።

በእለቱ “ዕለታዊ” ዝግጅት ላይ ሃብታሙ “ስለወያኔ ሲነሳ ያንቀጠቅጥሃል ” በሚል ኤርሚያስን ክፉኛ ሲዘልፈው ተሰምቷል። ይህን ከማለቱ በፊትም ” እኔም ሆንኩ አንተ ኢህአዴግ በነበርንበት ወቅት ለፈጸምነው እንደ ድርሻችን እንጠየቃለን” ካለ በሁዋላ ተቃዋሚ ናቸው ተብለው የሚገመቱ ዜጎችን ለመምታት በተደነገገው የጸረ ሽብር ህግ የኤርሚያስ ሚና ጉልህ እንደነበር በይፋ አስታውቋል። ከዚህም የዘለለ ተናግሮት ነበር። “እኔ እዛው ሆኜ ታግያለሁ” ሲልም ኤርሚያስ “ሲፋጅ በማንኪያ፣ ሲቀዘቅዝ በጄ ” እንዲሉ አይነት መሆኑንን አመልክቷል።

ሰኞና ማክሰኞ ከኢየሩስና ከብሩክ ጋር ብቻውን 360 ላይ የቀረበው ኤርሚያስ ለገሰ ብቻ ሲሆን፣ ሃብታሙ ያልቀረበበት ምክንያት ለጊዜው አልታወቀም። ሃብታሙ ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ ” አሁን አማራን እየጨረሰ ያለው ትህነግ ነው” በሚል አቋሙን አጥርቶ የመጣ ሲሆን፣ ኤርሚያስ “አዎ፣ ግን …” እያለ የትህነግን በደለና ወንጀል ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ሲያጋራ ተስተውሏል። ይህ አካሄድ አዲስ ባይሆንም ኤርሚያስ አሁንም ሆን ብሎ የሚያደርገው እንደሆነ ከ360 አካባቢ ተሰምቷል።

ቀደም ሲል በስምምነት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን ለይቶ በማሳጣትና የትህነግን ሃጢያት ተካፋይ በማድረግ ተግባር ላይ ተሳትፎው የጎላ እንደሆነ የሚጠቀስለት 360፣ ከጀርባ ሆነው ከሚረዱት አጋሮቹ በተጨማሪ 360ን በገሃድ የሚደግፈው የመረጃ ቴሌቪዥን ባለቤት ሚናቸውን ይለያሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ተናግረዋል። ” ከአማራ ጋር ሂሳብ አወራርዳለሁ፤ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ሲኦልም ከሆነ እንገባለን” ከሚል ድርጅትና የድርጅት አመራር ጋር ግንኙነት ካለው ሚዲያና አዘጋጆቹ ጋር የመረጃ ቲቪ ባለቤት ሚናቸውን ሳይለዩ የት ድረስ እንደሚዘልቁ ግራ የገባቸውም አሉ።

አንሙት አብርሃም በቅርቡ “ሰላም ስበክ ወንድም ዓለም” እንዳለው በማህበራዊ ገጹ ማንሸራሸሩን ያስታወሱ “ኤርሚያስ ከጌታቸው ጋር የስልክ ግንኙነት አለው መባሉ አያስገርምም” ባይ ናቸው።

አንሙት አብርሃም ቀደም ሲል ENN (ኢ ኤን ኤን) በሚባለውና ዶክተር ደብረጽዮን በቦርድ እየመሩት በነበረው የቴሌቪዥን ላይ ይሰራ የነበረ፣ አሁን የአማራ አክቲቪስት መሆኑን በይፋ ያስታወቀ ነው።

ሲያስረዱም “360 ላይ ላለፉት ሁለት ዓመታት ይቀርቡ የነበሩት ፕሮግራሞች በሙሉ የትህነግ ሃሳብና ዓለማ ላይ የተቸከሉ ነበሩ። በተለይ ኤርሚያስ ሌላው ‘በረከት ስምዖን’ ነው ሲባል በጅምላ ሲጮሁ የነበሩ አዲስ ይሆናባቸው ካልሆነ በቀር ለሌሎች ከድሮም ግልጽ ነበር” ብለዋል።

ኤርሚያስ “ከኦሮሚያ ዘርፋለች” ብሎ ለሰደባት ከተማ፣ በባለ አደራ ምክትል ሊቀመንበር የሆነላት እንደሆነ ያስታወሱ፣ ሃብታሙ በደረጃ ዝቅ ቢልም ከትህነግ ጋር ግንኙነት እንደነበረው አይጠራጠሩም። ሆኖም ግን ትህነግ ” ከአማራ ጋር የማወራርደው ሂሳብ አለ” በሚል በሰላማዊ ዜጎች ላይ ወረራ ካካሄደ ብሁዋላ ምክር ሰምቶ ወደ ቀልቡ መመለሱን በበጎ ተመክተዋል።

ሰኞና ማክሰኞ ብቻውን የቀረበው ኤርሚያስ ለገሰ ቃሊቲ አቃቂ መምህር እያለ ካድሬነትን ሲጀመር በመድረክ ታጋዮችን እያነሳ ያለቅስ እንደነበር በቅርብ የሚያውቁት መመህር ባለደረቦቹ ምስክርነት መስጠታቸው አይዘነጋም። በ1097 ምርጫ አፈ ቀላጤ ሆኖ ህዝብ ሲፈጅ ትህነግን ይከላከል እንደነበር አይዘነጋም። ጀግና ብርቁ የሆነው ዲያስፖራ ሁሉን ረስቶ ያጨበጨበለት ኤርሚያስና የ360 ግንኙነት ምን ሊሆን እንደሚችል ለጊዜው መረጃ የለም። ኤርሚያስ፣ ሃብታሙም ሆነ 360 የሚሉት ካለ ዝግጅት ክፍሉ ለማካከተት ዝግጁ ነው። ኤርሚያስን ግን ተባብሪያችን በእጅ ስልኩ ደውሎ ሊያገኘው አለመቻሉን አምለክቷል።

Exit mobile version