Site icon ETHIO12.COM

“ሰዎች በመንግሥት ባይገደቡ ኖሮ ይሄን ጊዜ ተላልቀው ነበር” – ቶማስ ሆብስ (1588-1679)

ዌስትፖርት ነው የተወለደው፤ ማልሜስቡሪይ አቅራቢያ በዊልሻየር፣ ኢንግላንድ። ሀብታም አጐቱ ወጪውን ሸፍኖለት ወደ ማግዳሊን ሆል፣ ኦክስፎርድ ለትምህርት ሰደደው። ቶማስ ሆብስ የመጀመሪያ ዲግሪውን በ1608 እንደያዘ የዴቪንሻየር ኧርል የበኩር ልጅ ለሆነው ዊሊያም ካቬንዲሽ አስጠኚ ሆነ። ከካቬንዲሽ ቤተሰቦች ጋር በነበረው የጠበቀ ትስስር በዘመኑ ስመ-ጥር ከነበሩ ምሁራን ጋር እንዲገናኛ ምክንያት ሆነው፤ በተጠቃሽም በእሱ ላይ ጉልህ ተፅዕኖ ካሳደረው ሰር ፍራንሲስ ቤከን ጋር። ወደ ጥናታዊ ሥራዎች እንዲያተኩርም ጊዜና መንገዱን አመቻችቶለታል።

የቶማስ ሆብስ የፖለቲካ እሳቤ፣ የእንግሊዝ እርስ-በርስ ጦርነትን እና የ17ኛውን ክፍለ ዘመን ሳይንሳዊ አብዮት ተሞክሮዎች ከታዘበ ሰው የመነጨ ነው። እሳቤውንም እንድንረዳው ይህን እውነታ መገንዘብ አስፈላጊ ነው።

የፖለቲካ እሳቤዎቹን በተለያዩ ጊዜያት ቀምሯቸው ቢታይም፣ ይበልጥ ምሉዕ ሆነውና ተፅዕኖ በሚፈጥር አገላለፅ የቀረቡት “#Leviathan” በተሰኘው ሥራው ነው። ፖለቲካን የተመለከተበት መንገድ ራስ-አወቅ በሆነ መልኩ ሳይንሳዊ ነው። ጥያቄዎችን የማንሳት ስልቱ፣ በከፊል ከጋሊሊዮ እና ከቤከን ጋር ከሚያያዘው ነገሮችን በታትኖ ከማገናኘት (resolutive- compositive) ዘዴ የተወሰደ ሲሆን፣ በከፊል ደግሞ በዩክሊድ አቀራረብ ላይ ተመልክቶት ያማለለውን ጥቃቅን ክፍሎችን ለመረዳት ጥቅል ምንነታቸውን ከፋፍሎ በአመክኒዮ የመመርመር ዘዴን (deductive reasoning) ይጠቀማል። ትክክለኛው የፖለቲካ ግንዛቤ ላይ ለመድረስ ከፈለግን፣ በቅድሚያ ህብረተሰባዊ ጥቅሎችን ወደ ትናንሽ ክፍሎቻቸው – በተጠቃሽም ወደ ግለሰብ ሰብዓዊ ፍጡራን – ተንትኖ መረዳት ግድ ይለናል። ከዚያም እነዚያን ክፍሎች ለይተን ጠባይ እና ምግባራቸውን ካጠናን በኋላ፣ እንደ ቀዳሚ መርሆዎች አድርገን በመቁጠር ማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ አወቃቀርን በተመለከተ እነሱን በመንተራስ ምክንያታዊ ድምዳሜዎችን መምዘዝ እንችላለን። በዚህ መንገድ፣ እንደ ሆብስ ሐሰብ ከሆነ፣ ፖለቲካን እንደማንኛውም ሳይንስ በሁለት እግሩ በእርግጠኝነት ማቆም ይቻላል፤ እንዲሁም ሰላም እና መረጋጋትን የማረጋገጫ ጥርጥር የለሽ ዘዴዎችን ወደሚያበረክትልን የፖለቲካ ሁኔታ መድረስ ይቻለናል።

በሥነ-ምግባሮች እና በሥልጣኔ ካልተበረዘ ሰብዓዊ ፍጡር ከሆነ ግለሰብ፣ ማለትም ከ«ተፈጥሯዊ» ሰብዓዊ ፍጡር የምናገኘው ምንድነው? ሆብስ ገና በ1630 ገደማ – በይበልጥ ለቤከን ተፅዕኖ ምስጋና ይግባውና – አጠቃላዩን የተፈጥሮ ሥርዓት ሕሊናን ወይም ነፍስን መጠቀም ሳያስፈልግ፣ በአካል ወይም በሰውነት (body) አማካኝነት ማብራራት እንደሚቻል አምኖ ተቀብሏል። “De corpore” ላይ መከራከሪያውን እንዳስቀመጠው፣ የሳይንስ ተግባር የተለያዩ አካላዊ (Corporeal) እንቅስቃሴ ዓይነቶችን ተፅዕኖ መመርመርና መግለፅ ነው፤ ይህ እንደሱ ሐሳብ ለፊዚክስ እውነት እንደሆነው ሁሉ፣ ለፊዚዮሎጂም ሆነ ለሳይኮሎጂ እውነት ነው።

የእርሱ ቁሳዊነት ወይም ማቴሪያሊዝም (ቁስን መሠረት ባደረገ ትንታኔ ላይ ያነጣጠረ አስተምህሮ) ለሰው ልጅ ባሕሪይ ምልከታው ማዕከል ነው። (ይህ ቁሳዊነቱም በእርሱ ዘመን በነበሩት ፈላስፎች ዘንድ በኢ-አማኝነትን /atheist/ ተፈርጆ እንዲወገዝ አድርጎታል።) እንደሱ ሐሳብ፣ የእያንዳንዱ ሰብዓዊ ፍጡር አካል እንደሰዓት መቁጠሪያ ዓይነት ውስብስብ ማሽን እንጂ ሌላ አይደለም። እንዲህ ዓይነት ገለፃውን በስፋት ያዳበረው “Decorpora”ላይ ነው። ልብ ስፕሪንገግ (ተለጣጭ) ናት፤ ነርቮች ገመዶች ናቸው፤ እንዲሁም መገጣጠሚያዎች (joints) ደግሞ ለአጠቃላዩ አካል መንቀሳቀስን የሚፈጥሩ ተሽከርካሪዎች (ጐማች) ናቸው። የአካል ባሕሪይ፣ በስሜት ህዋሳት በኩል ከውጫዊው ዓለም ለሚመጡት ቀስቃሾች (Stimuli) ተከታታይ ምላሾችን መስጠት ነው። አንዳንድ ቀስቃሾች፣ የእኛን «መሠረታዊ እንቅስቃሴ» ስለሚያሻሽሉ፣ ደስታን የሚሰጡ (pleasurable) ናቸው። እነዚህን ጥሩ ወይም “good” እንላቸዋለን። እነሱን አስመልክቶ ያለን ስሜን የመፈለግ ወይም የመሻት ዓይነት ነው፤ እናም እንዲበረክቱና የቆይታ ጊዜያቸው እንዲራዘም እንተጋለን። ደስታ በገነነበት (በገዘፈበት) ሁኔታ ውስጥ በሆንን ጊዜ፣ ያ ሁኔታችን “#felicity” ወይም ምሉዕ ደስተኝነት ይባላል።

የእኛን መሠረታዊ እንቅስቃሴዎች የሚገድቡ ሌሎች ቀስቃሾች (stimuli) ደግሞ የሚያሳምሙ (painful) ናቸው። እነዚህን መትፎ ወይም “evil” እንላቸዋለን፤ ለእነሱ ያለን ስሜትም የጥላቻ ዓይነት ሲሆን፤ ልናስወግዳቸውም እንተጋለን። «ጥሩ» እና «መጥፎ» ሌላ ምንም ትርጉም የላቸውም – «ደስታ አምጪ» እና «አሳማሚ» ከመሆን በቀር፤ ለምንፈልጋቸው ነገሮች እና ለምንጠላቸው (ለማንፈልጋቸው) ነገሮች ያወጣናቸው መጠሪያ ስሞች ናቸው። (ሆብስ የቋንቋ ምልከታው “ስማዊ” ወይም ኖሚናልስት ነው። ስማዊነት ወይም nominalism – በተመሳሳይ ቃል የሚፈረጁ የተለያዩ ነገሮች ከስም በቀር ምንም የሚጋሩት ነገር የለም የሚል ፍልስፍና ነው።) «ማስተዋል» (ወይም reason – የማሰብ ኃይል) ምሉዕ ደስተኝነትን በአግባቡ ማሳካት የሚያስችለን ወይም ተቃራኒውን እንድናስወግድ የሚያደርገን ወሳኝ ከፍል ነው። እኛ የምንፈራው እና ከምንም ነገር በላይ ልናስወግደው የምንፈገው ሞት ሲሆን፣ ሞት የምሉዕ ደስተኝነት ቀጣይነትን የማይቻል የሚያደርግ ክስተት ነው። የግለሰቦች ደርጊት ሁልጊዜ እስከተቻላቸው ድረስና በተቻለቸው ዘዴ ሁሉ በህይወት እንዲቆዩ የሚያደርጋቸውን መንገድ የተከተለ መሆኑ የተሞክሮ እውነታ ነው።

ሆብስ ይህን ምልከታ በመንተራስ፣ ለእያንዳንዱ ሰው ተፈጥሮውን እንደነበረ ለማቆየት የራሱን ጉልበት እንደራሱ ፈቃድ ይጠቀም ዘንድ የተፈጥሮ መብት ወይም ቀድሞውኑ የነበረ መብት መስጠት እንዳለብን “Leviathan”ላይ አስፍሯል። «መብት» የሚለውን ሰዎች አሁን በተግባር ስለሚፈፅሙት ድርጊት የተሰጠ ከሚመስለው እውነታን መሠረት ካደረገ ጥቅላዊ ድምዳሜ ላይ አንጥሮ ማውጣት ጥያቄ የሚያስነሳ የአመክኒዩ አካሄድ ሊመስል ይችላል። ነገር ግን ሆብስ ባለመብት መሆን ምን ስለመሆኑ የተለየ ሐሳብ እንዳያስቀምጥ በራሱ የማቴሪያሊስት ሳይኮሎጂ ተገድቧል፤ እናም በመብት እሳቤ ላይ መቀጠሉን የመረጠበት ምክንያት፣ ህብረተሰብን እና መንግሥትን የምንፈጥረው፣ እንደሱ ሐሳብ፣ የራሳችንን “የተፈጥሮ መብት” አሳልፈን ስንሰጥ ነው።

የሆብስ ቁሳዊ (ማቴሪያሊስት) እና ሄዶኒስት (ለሰው ልጅ ህይወት ከፍተኛ መልካም ነገር እና ትክክለኛው ግብ ደስታ ነው የሚል አስተምህሮ) ሳይኮሎጂው፣ በሚያስደንቅ ዝርዝር እና ተያያዥነት ተብራርቷል፤ ምንም እንኳን ዲተርሚኒዝም (ማንኛውም ድርጊት እና ክስተት ከፈቃድ ውጪ በሆኑ ምክንያቶች ይወሰናል የሚል ፍልስፍና) እና ነፃ ፈቃድን (free will) በተመለከተ፣ የቱም ጋ በተሟላ መልኩ ያልመለሳቸውን ጥያቄዎች ያስነሳ ቢሆንም። በግልጽ ባያመለክተውም፣ በሕሊናው ውጤቱ መጥፎ ከሆነ እራስን ማስቀደም (egoism) ጋር የተያያዘ ነው። ይህ የሆብስ አመለካከት በመንግሥት ምንነት እና ዓላማዎች ግንዛቤው ላይ መሠረታዊ ሆኖ ይታያል። እያንዳንዱ ግለሰብ፣ በሳቢ እና ገፊ የደስታ እና የህመም ኃይሎች አማካኝነት

Via Ermias tokuma

Exit mobile version