Site icon ETHIO12.COM

“ በደባርቅ አሸባሪው ህወሓት ያሰማራው ከስድስት በላይ ክፍለጦር ተደመሰሰ”

የትግራይ ወራሪ አሸባሪና ዘራፊ ቡድን በደባርቅ ወረዳ ቦዛ አካባቢን በማለፍ የዳባት ወረዳ ዲያ የሚባል የሸለቆ መንገድ ተከትሎ ጭና የተባለ ቀበሌ አድርጎ የወቅን ተራራንና መሰል የተያያዙ ሰንሰለታማ ኮረብታወችን ተቆጣጥሬ ደባርቅን እይዛለሁ ከዛም ጎንደርን በቀላሉ ለመቆጣጠር ያስችለኛል ብሎ ያሰለፈው ከስድስት በላይ ክፍለ ጦር መደምሰሱ ተገለጸ።

ይህንን የአሸባሪው ቡድንን እቅድ ለማክሸፍ ለተከታታይ 30 ስዓታት በተካሄደ ውጊያ ከስድስት በላይ ክፍለ ጦሩ ተደምስሶ ፍላጎቱ መና ቀርቷል።

በውጊያው ጀግናው የሃገር መከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ሃይል፣ የአማራ ሚሊሻ እና ፋኖ የዳባትና ደባርቅ ወጣትና ህዝብ በጋራ መሳተፋቸው ተገልጿል።

በዚህ ውጊያ ላይ ወራሪው ቡድን አስገድዶ ያሰለፈው ከ6 ክፍለ ጦር በላይ ታጣቂ ሀይል ሙሉ በሙሉ ተደመስሶአል ያለው የአማራ ብልጽግና፤ ቡድኑ ቀጣይ አስገድዶ ለሚያቀርበው ሃይልም ልኩን እንደሚሰጠው እና ቀጣይ የተወረሩ ቦታወችን ሙሉ በሙሉ ነፃ ለማድረግ ህዝቡ፣ ሚሊሻው፣ ልዩ ሃይሉና ፋኖ ከጀግናው መከላከያ ሰራዊት ጋር በመቀናጀት አኩሪ ገድል ለመፈፀም በመገስገስ ላይ እደሚገኙ ገልጿል።. (ኢ ፕ ድ)

Exit mobile version