Site icon ETHIO12.COM

በክህደት ለትህነግ ሲሰሩ ነበር የተባሉ የመከላከያ መኮንኖች ተፈረደባቸው

የደቡብ ዕዝ ቀዳማዊ ወታደራዊ ፍርድ ቤት ለአሸባሪው ህወሓት ሲሰሩ የነበሩ 16 የሠራዊት አባላት ላይ ከ2 ዓመት ከ9 ወር እስከ 18 ዓመት ከ8 ወር በሚደርስ ፅኑ እስራት እንዲቀጡ መውሰኑ ተገለጸ።

የደቡብ ዕዝ ቀዳማዊ ወታደራዊ ፍርድ ቤት ዛሬ ጠዋት በነበረው ችሎት የዕዙ የሠራዊት አባላት ሆነው ለአሸባሪው የህወሓት ቡድን ሲሰሩ በነበሩ 16 የሠራዊት አባላት ላይ የመጨረሻ የፍርድ ውሳኔ ባሳለፈበት ወቅት ነው ይህ የተሰማው።

ተከሳሽ የሠራዊት አባላቱ ከቀረቡባቸው ክሶች በከፊል ሲያስተባብሉ በከፊል አምነዋል።አቃቤ ሕግም የሰነድና የሰው ማስረጃዎችን አቅርቦ የተከራከረ ሲሆን የተከሳሽ ጠበቆች በበኩላቸው ተከሳሽ የሠራዊት አባላቱ ከዚህ ቀደም በርካታ አዎንታዊ ተግባራትን ያከናወኑ እና የቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆናቸውን ከግምት ውስጥ በማስገባት ፍርድ ቤቱ የቅጣት ማቅለያ እንዲያደርግላቸው ጠይቋል።

ግራ ቀኙን ያዳመጠው ወታደራዊ ፍርድ ቤትም ዛሬ ጠዋት ባዋለው ችሎት በ16 የሠራዊት አባላት ላይ የጥፋተኝነት ብይን ሰጥቷል።በዚሁ መሠረት

1. መጋቢ ሃምሳ አለቃ አብርሃም ገበቦ 2 ዓመት ከ9 ወር

2. ሃምሳ አለቃ ጊዴይ ገ/ዮሐንስ 18 ዓመት

3. ሻለቃ ባሻ ሹምዬ ወልደብርሃን 17 ዓመት

4. ሌ/ኮሎኔል ገ/ኪዳን ወ/ማሪያም 18 ዓመት

5. ሻምበል ሀብቱ አበራ 17 ዓመት

6. ኮሎኔል ወንድም ገ/ዋህድ 18 ዓመት ከ3 ወር

7. መቶ አለቃ ካሱ ብርሃነ 18 ዓመት

8. መቶ አለቃ ሹመንዲ ትርፌ 18 ዓመት ከ8 ወር

9. ኮሎኔል ገብረሳሙኤል ወላይ 14 ዓመት ከ2 ወር

10. ም/ መቶ አለቃ አደም ያደታ 6 ዓመት

11. ሃ/ አለቃ ኪኒሶ መኮንን 5 ዓመት

12. መቶ አለቃ ላዕከ ክንፈ 13 ዓመት ከ1ወር

13. ሌተናል ኮሎኔል ብርሃነ ወላይ 10 ዓመት

14. ሌተናል ኮሎኔል ወልዳይ ብርሃነ 5 ዓመት ከ 5ወር

15. ኮሎኔል ሃዱሽ ገ/መድህን 13 ዓመት ከ2 ወር

16. ሻምበል ብርሃነ ገ/ወልድ

17 ዓመት የተወሰነባቸው ሲሆን ወታደራዊ ፍርድ ቤቱ በወንጀል ድርጊት ተጠርጥረው እጃቸው ከተያዘበት ቀን ጀምሮ በሚታሰብ ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ብይን መሰጠቱን የኢትዮጵያ ብሮድ ካስት ዘግቧል።

Exit mobile version