Site icon ETHIO12.COM

ለእርጉዝ ሴቶች የተከለከሉ ምግቦች

✅ ጉበት
ቫይታሚን ኤ ህፃኑ በማህፀን ውስጥ ለሚኖረው እድገት አስፈላጊ ነው። ይህን ቫይታሚን እርጉዝ ሴቶች ከፍራፍሬ፣ አትክልት፣ ሥጋ እና እንቁላል ያገኙታል። ነገር ግን ከመጠን በላይ የሆነ ቫይታሚን ኤ ለህፃኑ መጥፎ ሲሆን በወሊድ ጊዜ ችግር ያስከትላል

✅ የወተት ምርቶች (ፓስቸራይዝድ ያልሆኑ)

እርጉዝ ሴት በቀን ከሁለት እስከ ሶስት ጊዜ የወተት ምርቶችን ማግኘት አለባት። በውስጣቸውም ካልሲየም፣ ፕሮቲን እና ቫይታሚን ዲ ሲይዙ የሚወለደውን ህፃን ታዳጊ አጥንት፣ ጥርስ፣ ልብ እና ነርቭ በመገንባት ይጠቅማሉ። ነገር ግን ሁሉም የወተት ምርቶች ለአንቺ ምግብነት መልካም አይደሉም ስለዚህ ጥሬ ወተት እና ሌሎች ጥሬ የወተት ምርቶችን መጠቀም የለብሽም።

✅ በሂደት ያለፈ ሥጋ (Processed Meat)

በፍጥነት የሚደርስ እና ቀላል ምግብ መመገብ ስናስብ የአብዛኛዎቻችን ምርጫ ሳንድዊች ነው። ነገር ግን እርጉዝ ከሆንሽ ሳንዱዊቹ ከምን ከምን እንደተሰራ በቅርበት መመልከት አለብሽ። ምክንያቱም ሊስቴሪያ ለተባለ ባክቴሪያ ሊኖረው ይችላል የሚል ስጋት ስላለ ነው። ይህ ባክቴሪያ በጣም በቀዝቃዛ የአየር ሁኔታ እድገቱን የሚቀጥል ብቸኛ ባክቴሪያ ነው።

✅ ሳላድ

ሳላድ ከትኩስ አትክልትና ፍራፍሬ የሚዘጋጅ ነው። ይህም ቁጥር አንድ ተመራጭ ጤናማ ምግብ ያደርገዋል። ነገር ግን በአትክልት ቤት፣ ጁስ ቤት እና ካፍቴሪያ ውስጥ ሳላድ መመገብሽን አቁሚ ምክንያቱም አትክለቶቹ የሚቀመጡበት የሙቀት ሁኔታ፣ የተዘጋጁበት ሰዓት የምግቦቹን ለጤና ተስማሚነት ስለሚወስን ነው። ስለዚህ በቤትሽ ውስጥ ሰርተሽ መመገቡ ተመራጭ ነው።

✅ ጁስ (ፓስቸራይዝድ ያልሆነ)

ጁስ መጠጣት አትክልቶች እና ፍራፍሬዎችን በምግብ ገበታሽ ውስጥ በቀላሉ የምታካትችበት መንገድ ነው ነገር ግን ሁሉም ጁሶች ለአንቺ ንጽህና ጤናማ አይደሉም። ምክንያቱም ኢሸርሺያ ኮላይ ወይም ሊስቴሪያ (E. coli or Listeria) የተባሉ ባክቴሪያዎችን በውስጣቸው ሊይዙ ስለሚችሉ ነው።

✅ በበቂ ሁኔታ ያልበሰለ ሥጋ እና ጥሬ የአሳ ሥጋ
እርጉዝ በምትሆኝበት ጊዜ ጥሬ ሥጋ እና ጥሬ የአሳ ሥጋን ቻው ብለሽ መሰናበት አለብሽ። ባክቴሪያ እና ሌሎች በሽታ አምጪ ህዋሶች በደንብ ባልበሰለ ወይም በጥሬ ሥጋ ላይ እና በባህር ውስጥ ምግቦች ውስጥ መኖር ስለሚችሉ ነው።

✅በበቂ ሁኔታ ያልበሰለ እንቁላል

እንቁላል የፕሮቲን፣ ቫይታሚን እና ሜኔራል መገኛ ምንጭ ነው። ነገር ግን እርጉዝ ከሆንሽ የምትመገቢው እንቁላል በደንብ መብሰሉን ማረጋገጥ አለብሽ። በትክክል ካልበሰለ ግን ሳልሞኔላ (Salmonella) ለተባለ ባክቴሪያ የመጋለጥ ዕድል አለሽ።

✅ቡና

ካፌይን ትልቅ ትኩረት የምትሰጭው ጉዳይ ነው። ከፍተኛ መጠን ያለው ቡና በእርግዝና ወቅት መጠጣት ከማስጨንገፍ/ ማስወረድ ጋር ይያያዛል።

✅ ከፍተኛ ሜርኩሪ ያለው አሳ

እርጉዝ የሆነች ሴት ከፍተኛ የሆነ ሜርኩሪ ያላቸውን አሳዎች መመገብ ማቆም አለባት። ይህ ኬሚካል በሰውነትሽ ውስጥ የመከማቸት ባህሪ ስላለው የነርቭ ሥርዓትሽን ሊጎዳው ስለሚችል ነው።

✅ አልኮል

ብዙ ኤክስፐርቶች እንደሚስማሙት አንድ እርጉዝ የሆነች በእርግዝናዋ ወቅት የአልኮል መጠጥ መጠጣት የለባትም የዚህም ምክንያት ልጅ ላይ የሚከሰተውን ፌታል አልኮሊክ ሲንድረምን (Fetal Alcohol Syndrome) ለመከላከል ሲባል ነው።

ዋናው ጤና ነው!

Via Getu temesgen FB

Exit mobile version