Site icon ETHIO12.COM

ደቡብ ጎንደር- ሰላማዊ ህይወት ጀመረች – በጭና ተራሮች የመሸገ ስድስት ክፍለ ጦር “ዋጋ ቢስ” ሆነ

አሸባሪው የህወሓት ታጣቂ ከአማራ ህዝብ ጋር ሂሳብ አወራርዳለሁ ብሎ ገብቶ የተቀበረበት የደቡብ ጎንደር ዞን ወደ ተሟላ ሠላማዊ እንቀስቃሴ መመለሱን የዞኑ አስተዳዳሪ አስታወቁ፡፡ በጭና ተራሮች መሽጎ የነበረ ስድስት ክፍለጦር መመታቱ ተሰማ። ቪዲዮውን ይመልከቱ።

የዩቲዩብ ገጻችንን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ መረጃ ይጋሩ

የደቡብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቀለምወርቅ ምህረቴ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘጋቢዎች እንዳሉት፤ ወራሪው የትህነግ ቡድን የገባበት ደቡብ ጎንደር ዞን መቀበሪያው መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ከባድ መሳሪያ ተኩስ ሲሰማ የቆየው ማህበረሰቡ በአሁኑ ወቅት ሠላማዊ እንቅስቃሴ በማድረግ ተረጋግቶ ኑሮውን እየመራ ሠራዊቱንም እያገዘ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ህዝቡ ሠላማዊ ኑሮውን እንዲቀጥልና ወደ ሥራ ለማስገባት ከፍተኛ ርብርብ ተደርጓል ያሉት ዋና አስተዳዳሪው፤ በወራሪው ጠላት ጉዳት ደርሶባቸው የነበሩ እንደ መብራትና ቴሌ ያሉ መሠረተ ልማቶችም ወደ አገልግሎት እየገቡ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

አካባቢያቸውን ለቀው የወጡ እየተመለሱ መሆናቸውን፤ አመራሩም ወደ መደበኛ ሥራው መመለሱንና የተጠናከረ አደረጃጀት መፈጠሩን ፤ የመንግስት መዋቅሮችም ወደ ሥራ እንዲገቡ መደረጉን ገልጸዋል፡፡ አሁን ባለው ሁኔታም ህዝቡ ወደ ተለመደው ሠላማዊ እንቅስቃሴ መመለሱን ተናግረዋል፡፡ዋና አስተዳዳሪው አክለውም፤ “ጠላትን ቀብረን እስከምነጨርሰው ድረስ ተረባርበን እናጠፈዋለን፡፡

ጠላትን ከቀበርንበትና ካስለቀቅንብትን ቦታ አልፈን መንግስት በሚሰጠው አቅጣጫ ጠላት እስከ መጨረሻው እናጠፋዋለን” ብለዋል፡፡ ለዚህም በየአካባቢው ያሉት አመራሮች እየተደገፉና እየተጠናከሩ ህዝቡን እንዲያነቁና እንዲያደረጁ እንዲሁም ለወታደራዊ ሥራው የሚያስፈልጉ መረጃዎችን እንዲገኙ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የአሸባሪው ህወሓት ቡደን ወረራ አካሂዶባቸው የነበሩ የደቡብ ጎንደር ዞን አካባቢዎች ያሉ ነዋሪዎች ሀብት ንብረታቸው ቢዘረፍም የተለመደውን ማህበራዊ እንቅስቃሴ መጀመራቸውን በሥፍራው የሚገኙ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘጋቢዎች ተመልክተዋል፡፡

በአዲሱ ገረመው (መቄት)

Exit mobile version