አማራ ክልል እንደ አዲስ እየተሰራ ነው፤ በክልሉ የከተማ መሬት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ታገደ

የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ሌጋሲ ተሸክሞ ግማሽ እግሩን ብልጽግና ውስጥ እንዳስገባ የሚነገርለት አማራ ክልል ከታች የቀበሌ መዋቅር አንስቶ እስከ አናቱ በአዲስ እየተሰራ መሆኑ የክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ሃላፊ ይርጋ ሲሳይ አስታወቀዋል። አዳዲስ ሹመት የተሰጠ ሲሆን በክልሉ የከተማ መሬት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ታገዷል።

ሌብነትና ብር አላቸው የሚባሉ እንዳሻቸው የሚጋልቡበትና የታጠቁ ሃይሎች በአደባባይ ታጅበው የራሳቸውን ደባል አስተዳደር በመመስረት ህግ ዘሞበት ወደ ቀውስ የገባው የአማራ ክልል እንደ አዲስ እንደሚዋቀር አቶ ይርጋ ያስታወቁት አዲሱሱን ዓመት አስመልክተው የክልሉን ወቅታዊ ሁኔታ በገለጹበት መግለቻቸው ነው።

በክልሉ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ የሰጡ አቶ ይርጋ የአማራ ህዝብ በማይመጥነው ደረጃ ጥፋት መፈጸሙን አመልክተው በዚህ ሰላም ወዳድ ህዝብ ሙሉ ድጋፍ ክልሉ ወደ ሰላም ተመልሶ እያገገም መሆኑን ገልጸዋል። ህዝቡን በሚመጥነው ደረጃ በአዲስ መልኩ አዲስ አመራር እንደሚዋቀርና በህዝብ ጥያቄዎች ላይ ርብርብ እንደሚደረግ አመልክተዋል።

“ከማንም በላይ የደረሰልን መከላከያ ነው” ሲሉ የአማራ ህዝብ ይህን ውለታ እንደማይዘነጋው ያወሱት ሃላፊው ” በርካታ ጥያቄዎች አሉን በዴሞክራሲያዊ አግባብ ለማሳካት አስፈላጊውን ሁሉ በሰላማዊ መገድ እንጥራለን። ይህ ካልሆነ ደግሞ መከላከያ አስፈልጊ እንደሆነ መታመን አለበት” ሲሉ የጥንቃቄ መልዕክትም አስተላልፈዋል። መከላከያ አገር በመሆኑ በየትኛውም ወቅት ክብርና ፍቅር ሊለይወ እንደማይገባ ጠቁመው ህዝብ የተለመደውን ድጋፍ እንዲያደርግለት አሳስበዋል። ይህ ሲሆን አሁን ክልሉ በፍጥነት ወደ ልማት ፊቱን ያዞራል ብለዋል።

“ትህነግ ያሰፋለትን ጨርቅ ባንዲራ ብሎ ተሸክሟል” በሚል የሚወቀሰውና አብዛኛው መዋቅሩ በትህነግ መዋቅር ስር የተቸነከረ እንደሆነ የሚነገርለት የአማራ ክልል ሙሉ በሙሉ በሁሉም ዘርፍ የአደረጃጀት ለውጥ፣ የአማራር ቅያሬና የማጥራ ስራ እያከናወነ መሆኑ ተመልክቷል።

በሌላ ዜና በክልሉ ከተሞች የከተማ መሬት ማስተላለፍ፣ ማዘጋጀትና አገልግሎት መስጠት ሥራዎች ሙሉ በሙሉ እንዲያቆሙ ትዕዛዝ መተላለፉ ታውቋል። የመሬት ዝርፊያና ንግድ በመላው አገሪቱ የተስፋፋ ቢሆንም አማራ ክልል ከተሞች በተለይም ባህርዳር በገሃድ እንደሚቸበቸብ፣ ብር አለኝ የሚሉ የተከለከለ ስፍራ ሳይቀር እንደሚያጥሩ፣ ከተሰታቸው ቦታ በላይ በሃይል እንደሚተቀልሉ በመጥቀስ ህዝብ ሲያማርር መቆየቱ ይታወሳል።

See also  “ትግራይ! የቁርጥ ቀን የነፍስ አድን ልጆችዋን ለመከራ ነጋዴዎች አትገብርም”!!

በደብረ ብርሃን በፎርጂድ የባንክ መረጃ ለመሃንዲሶችና የሚመለከታቸው የአስተዳደር አካላት መሬት መቸብቸቡን የሚገልጹ በኢንቨስትመንት ስም የተወሰዱ ቦታዎች ላይ ማጣሪያ እንዲደረግ ጥያቄ እየቀረበ ነው። በፎርጂድ የባንክ መረጃ ምንም ገንዘብ ሳይኖራቸው በደብረብርሃን በኢንቨስትመንት ስም መሬት የወሰዱ እጅግ የበዙ መሬቱ አየር በአየር መሸጣቸው ስለሚታወቅ ክልሉ የጀመረውን ምንጠራ አጥናክሮ ለለውጥ ቁርጠኛ እንዲሆን የሚጠይቁ በርካታ ናቸው።

በክልሉ የከተማና መሰረተ ልማት በምክትል ቢሮ ኃላፊው አሰፋ ሲሳይ ተፈርሞ፣ ለሁሉም ከተማ አስተዳደሮች እና ዞኖች የከተማ መሰረተ ልማት መምሪያዎች በተላለፈው ደብዳቤ መሰረት አገልግሎቱ ከጳጉሜ 2/2015 ጀምሮ መታገዱ ቢሰማም ማጣራት ስለመደረጉ የተባለ ነገር የለም።

በሌላ የሹም ሽር ዜና ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ልዩ ልዩ ሹመቶችን መስጠታቸውን አሚኮ ዘግቧል። ክልሉ የአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታውን በጥልቀት በመገምገም ወቅቱን የሚመጥን የአመራር ሪፎርም እና ስምሪት እየሠራ እንደሚገኝ ዘገባው አስታውሷል በዚህም መሰረት ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ ልዩ ልዩ ሹመቶችን የሰጡ ሲሆን፦

1.ግርማ መለሰ መንግስቱ (ዶ/ር) – በአብክመ የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ

2.ዘለቀ አንሉ ባይነስ (ዶ/ር) – በአብክመ የርዕሰ መስተዳድር ልዩ አማካሪ

3.አቶ አይነኩሉ አበበ ሳህሉ – የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር የሕዝብ ግንኙነት አማካሪ

4.አቶ ተክለየስ በለጠ አሸናፊ – የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር ምክትል አስተዳዳሪ

5.አቶ አራጌ ይመር መኮንን – የሰሜን ወሎ ዞን አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ

6.አቶ ታምራት ንጋቱ ጣሰው – የሰሜን ወሎ ዞን አስተዳደር ምክትል አስተዳዳሪና ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ

7.አቶ አብርሃም አያሌው እውኔ – የሰሜን ወሎ ዞን አስተዳደር የሕዝብ ግንኙነት አማካሪ

8.አቶ አንዳርጌ ጌጡ እንየው – የምዕራብ ጎንደር ዞን አስተዳደር ምክትል አስተዳዳሪና ግብርና መምሪያ ኃላፊ

9.ወ/ሮ ደመቅ አበባው አካሉ – የምዕራብ ጎንደር ዞን አስተዳደር የህዝብ ግንኙነት አማካሪ

10.ዲ/ን ሸጋው ውቤ አዛገ – የሰሜን ጎንደር ዞን አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ

11.አቶ ቢምረው ካሳ ታከለ – የሰሜን ጎንደር ዞን አስተዳደር ምክትል አስተዳዳሪና የንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ

See also  "ኢ-ፍትሃዊ ዓለም ውስጥ መኖራችን ያበሳጫል” አቶ አባተ ኪሾ

12.አቶ መንበር ክፈተው ታደሰ – የደቡብ ጎንደር ዞን አስተዳደር የህዝብ ግንኙነትና አደረጃጀት አማካሪ

13.አቶ ደስታ አስራቴ ካሳ – የደቡብ ጎንደር ዞን አስተዳደር ምክትል አስተዳዳሪና ትምህርት መምሪያ ኃላፊ

14.አቶ መሰረት በላይ ወንድወሰን – የደቡብ ጎንደር ዞን አስተዳደር የህዝብ ግንኙነት አማካሪ

15.አቶ አሊ ይማም ሁሴን – የደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር ምክትል አስተዳዳሪ

16.አቶ ተስፋ ዳኘው ተሾመ – የደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር የሕዝብ ግንኙነትና አደረጃጀት አማካሪ

17.አቶ ሙሀመድ አሊ ሙሄ – የደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር የሕዝብ ግንኙነት አማካሪ

18.አቶ ኑርልኝ ብርሃኑ አየለ – የምስራቅ ጎጃም ዞን አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ

19.አቶ ፈንታሁን ቸኮለ አድማሴ – የምስራቅ ጎጃም ዞን አስተዳደር የሕዝብ ግንኙነትና አደረጃጀት አማካሪ

20.አቶ ዋለ አባተ አየለ – የምስራቅ ጎጃም ዞን አስተዳደር ምክትል አስተዳዳሪ

21.አቶ ተስፋየ በላይ ተሾመ – የምስራቅ ጎጃም ዞን አስተዳደር አደረጃጀት አማካሪ

22.አቶ እድሜአለም አንተነህ እጅጉ – የምዕራብ ጎጃም ዞን አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ

23.አቶ አበባው አንተነህ ተሻገር – የምዕራብ ጎጃም ዞን አስተዳደር ምክትል አስተዳዳሪና የሰላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ

24.አቶ ዓባይ አለሙ ብርሃኑ – የምዕራብ ጎጃም ዞን አስተዳደር የሕዝብ ግንኙነትና አደረጃጀት አማካሪ

25.ወ/ሮ ቤዛዊት ውብነህ አድማስ – የምዕራብ ጎጃም ዞን አስተዳደር የአደረጃጀት አማካሪ

26.አቶ ጌትነት ሙሉጌታ አያሌው – የምዕራብ ጎጃም ዞን አስተዳደር የሕዝብ ግንኙነት አማካሪ በመሆን ተሹመዋል።


 • የበርሊን ማራቶን ባለማዕረግ ትግስት እነ ዱቤ ጂሎ ቢሳተፉ ታዝረከርካቸው ነበር
  በማራቶን ከሁለት ደቂቃ በላይ ማሻሻል እጅግ የሚደነቅና ያልተለመደ ነው። ባለሙያዎቹ ወይም አሰልጣኞቹ የሮጠችበትን ፍጥነት በሰዓትና ርቀት ከፋፍለው ቢያቀርቡት ምን አልባትም ወንዶችን የሚገዳደር ፍጥነት ተጠቅማ ሮጣለች። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቴክኒክ ዳይሬክተርና የአትሌቶች ኮሚሽን ሰብሳቢ የነበሩት የዛሬው የተከበሩ ዱቤ ጅሎ አይነቱን ሯጮችን አዝረክርኮ ማሸነፍ የሚያስችላትን ሃይል አሳይታለች። የበርሊና ባለ ማዕረግ ትዕግስት!! ተግስት … Read moreContinue Reading
 • ለወልቃይት ጠገዴ ሴቲት ሁመራ አንድ ሚሊዮን የጉልበት ሰራተኛ ይፈለጋል፤ ከአንድ ነጥን አንድ ሚሊዮን ኩንታል በላይ ሰሊጥ ይጠበቃል
  “ከየትኛውም የኢትዮጵያ ክልል አስተማማኝ ሰላም ያለው እዚህ ነው። ለሰራተኞች እንደ ቤተሰብ ዝግጅት አድርገናል። ኑ” ሲሉ የተሰሙት አምስት መቶና ሶስት መቶ ሄክታር ሰሊጥና ማሽላ ያመረቱ ባለሃብቶች ናቸው። የዞኑ ግብርና ቢሮ ሃላፊ እንዳሉት አንድ ሚሊዮን አንድ መቶ ሃምሳ ሁለት ሺህ ኩንታል የሰሊጥ ምርት ስለሚጠበቅ ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሰራተኛ ሃይል ያስፈልጋል። የዞኑ አርባ … Read moreContinue Reading
 • የጎንደርን ከተማ ምን አይነት ተኩስ እንደሌለ ተገለጸ፤ ጎንደር ተይዛለች ተብሎ ነበር
  “ጎንደር ከተማን ሙሉ በሙሉ ይዘናታል” ሲሉ ስማቸው እንዳይገለጽ ጠይቀው ለጀርመን ድምጽ መረጃ በሰጡ የአማራ ሕዝባዊ ኃይል ፋኖ ቃል አቀባይ አየር ማረፊያውን ሆን ብለው እንዳልያዙ አመልክተዋል። እሳቸው ተናገሩ የተባለው በጀርመን ድምጽ እየተሰማ በለበት ሰዓት በተመሳሳይ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ውጊያ መደረጉን ሳያስተባብል ከተማዋን ለመያዝ የገባው ሃይል መደምሰሱን አሃዝ ጠቅሶ አመልክቷል። አገር መከላከያም … Read moreContinue Reading
 • “የሞተው ባልሽ ገዳዩ ወንድምሽ፣ሀዘንሽ ቅጥ አጣ ከቤትሽ አልወጣ”
  የሞተው ባልሽ ገዳዩ ወንድምሽ (ሀዘንሽ ቅጥ አጣ ከቤትሽ አልወጣ) የሚለው የቆየ ተረት ልብን የሚያደማ ኩነትን ማሳያ ነው። እቺ መከረኛ ሚስት ባልዋ በእናቷ ልጅ ወንድሟ ተገደለ። ሟች ባል፣ ገዳይ ወንድም … ኢህአፓ “ሃይማኖት ነው” በሚል ሲገልጸው በነበረው ትግል በቀይና ነጭ ሽብር ስም እናቶች የወላድ መካን ሆነዋል። ጧሪ ያጡና ባዶ ቤት ሃዘን … Read moreContinue Reading
 • በአማራ ክልል የተነሳው ጦርነት በሰላም ሊቆጭ እንደሚችል ተሰማ
  በአማራ ክልል የተቀሰቀሰው ጦርነት በሰላማዊ መንገድ የሚቋጭበት አግባብ ተስፋ ሰጪ ደረጃ መድረሱ ተሰማ። የኢትዮ12 የዜና አቀባዮች እንዳሉት ሰላም ወደድ የሆኑ ዜጎች ችግሩን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እያደረጉ ያለው ጥረት ውጤታም እየሆነ መሆኑንን ነው ያመለከቱት። በሰላም ጥረቱ ውስጥ የሚሳተፉትን ወገኖችና የሰላም ንግግር አመቻች የሆኑትን ክፍሎች ሳይጠቅሱ የዜናው ሰዎች እንዳሉት ጥረቱ ብዙ መንገድ … Read moreContinue Reading

Leave a Reply