ETHIO12.COM

ሀሰተኛ ምስል መጠቀም በሰሜን ወሎ ሕዝብ ላይ ሌላ ጥፋት፣ እርኩስ ተግባር

በሰሜን ወሎ የደረሰውንና እየደረሰ ያለውን የከፋ ችግር ለዓለም ለማሳወቅ የትማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ተጀምሯል። ይሁን እንጂ በዚህ ዘመቻ ስም አግባብነት የጎደላቸው፣ የቶጎጂውን ሕዝብ የማይገልጹና የቆዩ ምስሎችን የተጠቀሙ አሉ። ሆን ብለውም ይህን ምስል በማሰራቸት የሕዝቡን ስቃይ ለማራከስና ” ሃሰት ነው” በሚል በሚዲያ እዲዛበቱበት ማድረግ ወንጀል ነው። ከታች ያለውን ያንብቡ።

“እነዚህ ሁለት ፎቶዎች በሰሜን ወሎ የተነሱ ናቸው?”

ባለፉት ሁለት ቀናት በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ተፈናቅለው የምግብ እጥረትን ጨምሮ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን የትመለከቱ የትዊተር ዘመቻዎች በመካሄድ ላይ መሆናቸውን ተመልክተናል። የዘመቻው ተስታፊዎች ከአጭር መልዕክቶች ጋር የተፈናቃዮችን ፎቶዎች አጋርተዋል። በስፋት ከተጋሩት መካከል ከታች የሚታዩት ሁለት ፎቶዎች ይገኙበትል።

ምንም እንኳን በሰሜን ወሎ ዞን በርካታ ሰዎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በመጠልያ ጣቢያዎች እንደሚገኙና ለችግር ስለመጋለጣቸው መግስታዊ ባልሆኑ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ሚዲያዎች የተዘገበ ቢሆንም ከላይ የተጠቀሱት ሁለት ፎቶዎች የቆዩና ከሌላ ቦታ የተወሰዱ መሆናቸውን ኢትዮጵያ ቼክ የሪቨርስ ኤሜጅ ማሰሻ መተግበሪያዎችን በመጠቀም አረጋግጧል።

የመጀመሪያው ፎቶ ታህሳስ 11 2013 ዓ.ም
በወላይታ ዞን፣ ወላይታ ሶዶ ከተማ በሚገኝ የገብያ ቦታ የእሳት አደጋ በተከሰተበት ወቅት የተነሳ ነው። በፎቶው የሚታዩት እናት ወይዘሮ የሺ ቀልቦሬ እንደሚባሉ በጊዜው በሚዲያዎች መዘገቡ ይታወሳል።

ሁለተኛው ፎቶ እ.አ.አ መስከረም 20 2011 ዓ.ም በሮይተርስ የዜና ወኪል የተነሳ ሲሆን፣ በምስሉ ላይ የሚታዩት እናትና በምግብ እጥረት የተጎዳ ህጻን ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በሶማሊያ ሆዳን ጊዜያዊ የስደተኞች ጣብያ ተጠልለው የነበሩ ናቸው።

እውነተኛ ፎቶዎችን ብቻ በማጋራት የሀሠተኛና የተዛባ መረጃ ስርጭትን ይከላከሉ።

የላይኛው ምስል ከትሩዝ ብሎግ የተወሰደ ሲሆን ትንሽ ቆኡእት ያለ ነው

Exit mobile version