ETHIO12.COM

ቡርኪናፋሶዎች ከ 34 አመታት በኋላ አደባባይ ላይ ሀውልት በማቆም ጀግናቸውን አስበውታል !!


“ድሃ ሆኖ ስልጣን ይዞ ድሃ ሆኖ የሞተው” በአፍሪካ ምድር እንደ ደማቅ ኮከብ ድንገት ብልጭ ብሎ የጠፋው አፍሪካዊው ቼጉቬራ (ቶማስ አሲዶር ኒኦል ሳንካራ)

ሳንካራ ስልጣን ላይ የቆየው ለአራት አመታት ብቻ ቢሆንም ስምና ዝናው ግን ከሀገሩ አልፎ እስካሁን ድረስ በመላው አፍሪካ እንደናኘ ነው። የአፍሪቃ ቼ ጉቬራ ተብሎ የሚሞካሸው ሳንካራ ለድሆች የሚቆረቆር ፣ እኩልነትን የሚያቀነቅን ፣ ቅኝ ገዢዎችን እና ጨቋኞችን አጥብቆ የሚቃወም ፣ ህዝብን ለመብቱ እንዲታገል የሚያነሳሳ ፣ በአንድ ሳምንት ውስጥ 2.5 ሚሊዮን ህፃናት የማጅራት ገትር ፣ የወባ እና የኩፍኝ ክትባት እንዲወስዱ ፣ መሬት ከባላባቶች ወስዶ ለገበሬዎች ያስተላለፉ፣ በረሀማነትን ለመከላከል በአራት አመት የስልጣን ዘመኑ 10 ሚሊዮን ዛፎችን ያስተከለ ፣ ይህንን እና ከዚህም በላይ የሚቆጠሩ ተግባራትን የፈፀመው አፍሪቃዊው ቼ ጉቬራ ይህንን ያደረገው በአራት አመታት በተወሰነ የፕሬዝዳንትነት እድሜው ብቻ ነበር።

በ33 ዓመቱ ስልጣን ይዞ ለአራት ዓመት አገሩን መርቶ በስራዎቹ አለምን አጃኢብ ያሰኘው አፍሪካዊው ቼ
✔ አገሩ በፈረንሳይ ቀኝ ግዛት ስር በነበረችበት ወቅት ትጠራበት የነበረውን “አፐር ቮልታ” የተሰኘው ስሟን ፥ ቡርኪናፋሶ (ክብር ያለው ሰው ምድር) ብሎ ቀይሯል ፤
✔ “የሚመግብህ ይቆጣጠርሀል” በሚለው ቆራጥ ንግግሩ የውጪ እርዳታን በማስቀረት ሀገሬውን በምግብና ውሀ ራሱን አስችሏል
✔ ዜጎቹን የሀገራቸውን ምርት እንዲወዱና እንዲጠቀሙም አድርጓል
✔ የሴት ልጅ እኩልነትን አወጆ አስተግብሯል
✔ ትምህርት በመላው ቡርኪናፋሶ እንዲስፋፋ ብዙ ሰርቷል
✔ ከፍተኛ ደሞዝ ተከፋይነትን ፣ በህዝብ ንብረት መጨማለቅን አስቀርቷል
✔ ከ10 ሚልዮን በላይ ዛፎችን አስተክሏል

የብዙ ወጣቶች፣ ሰራተኞችና አርሶ አደሮች ተስፋ የነበረው የቡርኪናፋሶው የነፃነት ምሳሌ ቶማስ ሳንካራ ከ12 የግል ረዳትና ጠባቂዎቹ ጋር ከራሱ በላይ በሚያምነው በምክትሉና አብሮ አደጉ በሆነው ብሌስ ኮምፓወሬ የተገደለው በOctober 15/1987 ወር ነበር።

አፍሪካዊው ቼጉቬራ ቶማስ ሳንካራ ብዙ የሚነገርለትን ገድል የፈፀመ ታሪካዊ መሪ ነው።በተለይ ረሃብተኛ አገሩን ቡርኪናፋሶን ከኢምፔሪያሊስቶች ተመፅዋችነት አውጥቶ በአራት አመት ብቻ በምግብ ራሷን ያስቻለበትን ታሪክ
ብዙዎች ያነሱለታል። “ድሃ ሆኖ ስልጣን ይዞ ደሃ ሆኖ የሞተ” ነው ይሉታል። የግል ንብረቶቹ አንድ አሮጌ መኪና፣አንድ ብስክሌት ፣ በረዶ ቤቱ የተሰበረ ፍሪጅ ፣ አልጋና ቁም ሳጥን እንዲሁም አሮጌ ወንበሮች ብቻ ናቸው። ወደ ስልጣን ከወጣ በኃላ የልጆቹን ትምህርት ቤት እንኳን ያልቀየረ ሰው ነው ቶማስ ሳንካራ። መኖሪያ ቤቱ ነው። ቤተ መንግስቱን ከስራ ውጪ አይጠቀምበትም። እንደ አብዛኞቹ የአፍሪካ መሪዎች በሚሊዮን ዶላር ላሽቆጥቁጠውም አላለም። የሚጠቀመውም እንደ ቢሮው ብቻ ነበር። ቤተ መንግስት የስራ ቦታ እንጂ መንፈላሰሻ እንዳልሆነ ሁሌም ይናገራል። ፕሬዝዳንት ሆኖ የሚኖረው ተራ ሻምበል እያለ በሚኖርበት ቤት ውስጥ ነው። ሲለው በአሮጌ መኪናው፣ሌላ ጊዜ በሳይክሉ ራሱ እየነዳ ከቤቱ ወደ ስራው ይሄዳል።

(የምትመራው ህዝብ ምንነት እና ኑሮ ሲገባህ እንደ ሳንካራ ሲገባህ የሚቀድመውን እያስቀደምክ የሚያድረውን እያሳደርክ ሀገር በብልሀት ታስተዳድራለህ።

የዕድሜ ቁልል ተሸክመው ባዶ ለሆኑትና ሀያቱ ለሚሆኑት የአፍሪካ መሪዎች ተቆጪና ገሳጭም ነበር……. #ቶማስአሲዶርኒኦል_ሳንካራ

Via – Fitsum Gosaye

Exit mobile version