Site icon ETHIO12.COM

ኤርዶጋን – ከሱቅ በደረቴ እስከ ፕሬዚደንትነት

የቱርክ 25ኛው ጠ/ሚኒስትር እና 12ኛው ፕሬዚደንት
ረጀብ ጠይብ ኤርዶጋን

ረጀብ ጠይብ ኤርዶጋን በኢስታንቡል የድሆች ሰፈር ካሲምፓሻ (ቃሲም ፓሻ) ውስጥ እ.አ.አ በፌብሩዋሪ 26/1954 ተወለደ:: ከወላጆቹ አህመት ኤርዶጋን እና ቴንዚል ኤርዶጋን በኢስታንቡል የድሃ ሰፈር ውስጥ የተወለደው የዛሬው የቱርኩ ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን እስከ 13 አመቱ የልጅነት ሕይወቱን ያሳለፈው አባቱ በቱርክ የባህር ጠረፍ ጠባቂ በነበረባት “ሪዝ” በምትባለው በጥቁር ባህር ምስራቃዊ የባህር ዳርቻ ላይ በምትገኘው የወግ አጥባቂዎች ከተማ ውስጥ ነበር።

ኤርዶጋን በ 13 ዓመቱ እንደገና ወደ ኢስታንቡል ተመለሰ:: ከድሃ ቤተሰብ የተወለደው ኤርዶጋን ገና በልጅነቱ ሱቅ-በደረቴ በመስራት ቤተሰቡን መደጎም ግዴታው ነበር:: ኤርዶጋን የልጅነቱን ጊዜ በኢስታንቡል ኢማም ሀቲፕ ት/ቤት እየተከታተለ በጎን ደግሞ በኢስታንቡል የከተማዋ ጎዳናዎች ላይ ሀብሐብ ፣ ሎሚ እና ሲሚት (የሰሊጥ ቀለበቶች) በመሸጥ ተጨማሪ ገቢን ለቤተሰቡ በማምጣት አሳልፏል!!!

ኤርዶጋን ይህ የህይወት ፈተና ሳይበግረው ሱቅ በደረቴ እየሰራ ቤተሰቡን እያገዘና ትምህርቱንም እያሰለጠ የ 15 አመት ታዳጊ ሲሆን የፖለቲካውን ዓለም መቃኘት ጀመረ:: ፍላጎትም አደረበት::

የፖለቲካውን አለም እየቃኘ ከትምህርቱ ሳይዘናጋ እዛው ኢስታንቡል እስከ 12ኛ ክፍል አጠናቀቀ:: ቀጥሎም ከማርማራ ዩኒቨርሲቲ በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን ተመረቀ:: በተወሰነ ደረጃም የፕሮፌሽናል እግር ኳስን ይጫወት ነበር:: የውትድርና አገልግሎትም ሰጥቷል::

የዩኒቨርሲቲ ተማሪ በነበረበት ወቅት የልጅነት የፖለቲካ ፍላጎቱ አድጎ የቱርክ ተማሪዎች ህብረት አባል ሆነ:: ከዚያም ይህ የፖለቲካ ፍላጎቱን በተግባር ያሳየው የናሽናል ሳሊቬሽን ፓርቲ የወጣቶች ቅርንጫፍን ለመምራት በ 1976 እድሉን ሲያገኝ ነው:: መሪነትን “ሀ” ብሎ ጀመረ:: ይሄውና እስከዛሬ ድረስ ተከተለው::

ኤርዶጋን አሁን ላለበት ደረጃ ያበቃውን የህዝብ ተወዳጅነት ያተረፈው ለ4 ዓመታት የኢስታንቡል ከንቲባ ሆኖ በሰራበት ወቅት ነበር:: ያኔ ከፍተኛ ባለስልጣናት ይጠሉት ነበር:: ለምሳሌ አንድ ወቅት ላይ… በ20ኛው ከፍለዘመን የቱርክ ጦማሪ የፃፋትን ግጥም በአደባባይ አንብበሃል ተብሎ ለ4 ወራት ታስሮ ነበር::

ኤርዶጋን ብዙ የህይወት ውጣ ውረዶችን አልፏል:: ሁሌም ግን ወደፊት ይሄዳል:: በዚህ ፅናቱም ወደ አዲስ ምዕራፍ ተሸጋገረ:: የ”ፍትህና ልማት ፓርቲ” ወይም “AKP” የሚባል ፓርቲን በ2001 መስርቶ በሊቀመንበርነት ሲያገለግል ቆየ:: በ2002 በቱርክ በተደረገ ምርጫ 363 የህዝብ ተወካዮች መቀመጫን በማሸነፍ የቱርክ ፕሬዚደንት ሆነ::

እነሆ ዛሬ ላይ ሃገሩ ቱርክን በዓለም አደባባዬች ቀና ማድረግ የቻለ የዘመኑ ድንቅ ሰው መሆን ቻለ!!!! ልክ ዛሬ ኢትዮጵያ እያለፈችበት እንዳለው የምዕራባውያኑ ጫና ቱርክም ለበርካታ አመታት በምዕራባዊያኑ ጫና ውስጥ አልፋለች:: ሆኖም ኤርዶጋን እና የቱርክ ህዝብ በአንድነት በመቆም ፈተናዎችን እየተሻገሩ ዛሬ ቱርክ ለደረሰችበት ደረጃ አብቅተዋታል!!!! የቱርክ ህዝብ የኤርዶጋን ቀኝ እጅ ነው!!!! እሱም በህዝቡ እንደተወደደ በፕሬዚደንትነት ቀጥሏል!!!! ቱርክም ተሻግራለች!!! ተገዳዳሪ ሃይል ሆና እየመጣች ነው!!!!

ኤርዶጋን ከወራት በፊት በቱርክ በተካሄደ ኮንፈረንስ ላይ “ዓለም ከአምስት በላይ ናት” የሚል ንግግር በማድረግ የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት አወቃቀርን ተቃውሟል!!!እነሆ አሁን ደግሞ በአሜሪካ በተካሄደው የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ “A fairer world is possible.” (ፍትሃዊ ዓለምን መገንባት ይቻላል) በማለት የምዕራባዊያኑን አድልዖ እና ኢፍትሀዊነት ተችቷል!!!!

ኢትዮጵያም እንደ ቱርክ…
አብቹም ከኤርዶጋን….
የሚመሳሰል ነገር ይኖራቸው ይሆን ብዬ እጠይቃለሁ:: ካላቸው እሰየው:: ካልሆነም ችግር የለውም:: ቁምነገሩ የመሪያችን ቁርጠኝነት ነው!!!! ቁምነገሩ የህዝባችን በአንድነት መቆም ነው!!!!! በፈተና ወቅት ህዝብ እና መንግስት አንድ ሲሆኑ ውጤቱ ማሸነፍ ውጤቱ ሰብሮ ማለፍ ነው!!! ቱርክ የቅርብ ጊዜ አብነት ነች!!! ወገኔ ከፈተና በኃላ ክብር አለ!!!! ኢትዮጵያ ትሻገራለች!!!!! አምላኳም ፈፅሞ አይተዋትም!

Via – Dejene Assefa

Exit mobile version