Site icon ETHIO12.COM

ኢትዮጵያ ከመጪው ጥቅምት ጀምሮ የግብጽ ኤምባሲዋን በጊዜያዊነት ልትዘጋ ነው

ኢትዮጵያ በካይሮ የሚገኘውን ኤምባሲዋን ከጥቅምት ወር ጀምሮ በጊዜያዊነት እንደምትዘጋ በግብጽ የኢትዮጵያ አምባሳደር ማርቆስ ተክሌ መናገራቸው ቢቢሲ አረብኛ ዘግቧል።

ኤምባሲው ከሶስት እስከ ስድስት ወራት እንደሚዘጋ የተናገሩት አምባሳደሩ ዋና ምክንያቱ ከኢኮኖሚ ጋር የተያያዘ ነው ብለዋል፡፡ኢትዮጵያ በአልጀርስ የሚገኘውን ኢምባሲዋን እንደምትዘጋ አስታወቀች።

“ኤምባሲው አንዳንድ ወጪዎች ለመቀነስ በሚል ከጥቅምት ወር ጀምሮ ለሚቀጥሉት ሶስት እስከ ስድስት ወራት የሚዘጋ ይሆናል”ም ነው ያሉት አምባሳደሩ፡፡

አምባሳደሩ የኤምባሲው መዘጋት በሶስቱም ሀገራት ማለትም በኢትዮጵያ፣ግብጽ እና ሱዳን መካከል ካለው የህዳሴ ግድብ ጉዳይ ጋር የሚገናኘው አንዳች ነገር እንደሌለም አስረድተዋል፡፡

ኤምባሲው ዝግ በሚሆንበት ወቅት የኤምባሲው ኮሚሽነር ጉዳዮቹን እንደሚከታተልም ገልጸዋል፡፡

Exit mobile version