Site icon ETHIO12.COM

በኢትዮጵያ ሕዝብ የመረጠው መንግስት ቆመ፤ አብይ አሕመድ ህጋዊ መሪ ሆኑ

መልካቸውን በሚቀያይሩ ፖለቲከኞችና በውስጥ ጉዳይ ጣልቃ በመግባት ተቀያያሪ ምክያት በማቅረብ መንግስትን ሲሞግቱ፣ ሲያንኩዋስሱና “አናውቅህም” ለማለት ሲዳዳቸው የነበሩ ሁሉ ዛሬ አጀንዳቸው ተዘግቷል። ሕዝብ በማን አንደሚመራ ወስኖ ያካሄደው ምርጫ በስኬት ተዘግቱዋል። ኢትዮጵያ መንግስቷን አቁማለች።
“ዛሬ በመረጥኩት መንግስት መመራት ጀመርኩ” በሚል በርካቶች በማህበራዊ ገጾቻቸው ደስታቸውን አየገለጹ ነው። ጌታቸው ረዳ “ሕዝብ አየተራበ” ሲሉ የመንግስት ምስረታውን አንቋሸዋል። “መንግስትን በሳምንትና ሁለት ሳምንት አስወግደን…” አያሉ ማብራሪያ ሲሰጡ የነበሩት የትሕነግ አፈቀላጤ፣ ሁሉንም ትተውት ችጋርን መከራከሪያ አድርገዋል። ሕዝብ ደግሞ ማንኛውም ዋጋ ተከፍሎ “ትህ ነግ ይነቀል” የሚል አደራ ሰጥ ቷል። በሁሉም መንገድ ድጋፍ አንደሚያደርግና ለውጪ ጫና አጅ አንደማይሰጥ ኣመልክቷል።

፮ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመክፈቻ ጉባኤ ተካሄደ፡፡ በጉባዔው ዶክተር ዐቢይ አህመድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሰይመዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩም በጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ አማካኝነት ቃለ መሃላ ፈፅመዋል፡፡

አቶ ታገሰ ጫፎ

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመክፈቻ ጉባኤ እየተካሄደ ነው፡፡በጉባዔው አቶ ታገሰ ጫፎ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባዔ ሆነው ተመርጠዋል፡፡አፈጉባኤውም በጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አማካኝነት ቃለ መሃላ ፈፅመዋል፡፡

አቶ አገኘሁ ተሻገርን

አቶ አገኘሁ የ6ኛው ፌዴሬሽን ምክር ቤት አፌጉባኤ ሆነው በሙሉ ድምጽ ተመርጠዋል፡፡ አቶ አገኘሁ ተሻገር የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድርነትን ጨምሮ በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ህዝብና ሀገርን ማገልገላቸው ተገልጿል፡፡

ወ/ሮ ሎሚ በዶን

ምክር ቤቱ በሰባት ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ ወ/ሮ ሎሚ በዶን ምክትል አፈ-ጉባዔ አድርጎ የሾመ ሲሆን፣ ቃለ መሃላ ፈጽመዋል፡፡ ወ/ሮ ሎሚ በዶ የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባዔ ሆነው አገልግለዋል፡፡

Exit mobile version