Site icon ETHIO12.COM

በኢትዮጵያ የተመድ የስደተኞች ኤጀንሲ ሃላፊ እውነት በመናገራቸው በዕረፍት ስም መጠራታቸው አነጋጋረ

ተመድ – የአሸባሪውን ህወሃት ገመና የሚገልጥ ሁሉ ሰለባ የሚሆንበት ተቋ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ አሉታዊ ጫና ለመፍጠር የጸጥታ ምክር ቤቱ ተደጋጋሚ ስብሰባ አድርጓል።

በስብሰባዎቹ የተለየ ፍላጎት ያላቸው አገሮች የኢትዮጵያን መንግስት ለመወንጀል የሀሰት መረጃን አግዝፈው ሲያቀርቡ፤ የኢትዮጵያን እውነት የሚገነዘቡ አገሮች በበኩላቸው የኢትዮጵያን ጉዳይ ለኢትዮጵያ መተው እንደሚገባ በመግለጽ የሚደረገውን ጫና ለማምከን ሙከራ አድርገዋል።

ያም ሆኖ ግን ተመድና አንዳንድ ምዕራባውያን አሸባሪው ህወሃት በኢትዮጵያ ውስጥ እያደረሰ ያለውን ጥፋት በመሸፈን መንግስትን ከመወንጀል ወደ ኋላ ለማለት አልፈቀዱም።

መንግስት የውጭ ሃይሎች በተለይም በሰብዓዊ ድጋፍ ስም በአገር ውስጥ ጉዳይ ጣልቃ የሚገቡ አካላት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ በተደጋጋሚ ቢያስገነዝብ፣ ቢያሳስብና ከአገር ቢያሰናብትም ጣልቃ የመግባት ዝንባሌው እየጨመረ መጥቷል።

በተለይም የተመድ ሰባት ሰራተኞች በውስጥ ጉዳይ ጣልቃ በመግባታቸው ከአገር እንዲወጡ መደረጋቸው የድርጅቱን ዋና ጸሐፊ ጨምሮ ብዙዎቹን ያስደነገጠና ያልተጠበቀ በመሆኑ ጫናውን ለማበርታትና በሃሰት ኢትዮጵያን ለመወንጀል የሚያደርጉትን ጥረት እንዲያጠናክሩ አድርጓቸዋል።

ከሰሞኑ የታየው የተመድ የስደተኞች ኤጀንሲ የኢትዮጵያ ሃላፊ የሰጡትን ቃለ-መጠይቅ ተከትሎ በአስተዳደራዊ እረፍት ስም መጠራታቸው የዚህ ማሳያ ነው።

ሃላፊዋ በሰጡት ቃለ መጠይቅ የአሸባሪውን ህወሃት ትክክለኛ ገጽታ አሳይተዋል።

ሃላፊዋ ማውሪን አቺንግ ከኢትዮጵያ መጠራታቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ እንደደረሳቸው የኤኤፍፒ ዘገባ አመላክቷል።

የዚህ ውሳኔ ዋና መነሻው ሃላፊዋ የኢትዮጵያን እውነት በመያዝ የተለያየ ጽሁፍ በማውጣት እየሞገተ ለሚገኘው ጸሐፊ ጄፍ ፒርስ ቃለ-መጠይቅ በመስጠታቸው እንደሆነ ተገልጿል።

በቃለ-መጠይቁ የኢትዮጵያን እውነት አጉልተው በማውጣት የአሸባሪውን ህወሃት ትክክለኛ ገጽታ ለአደባባይ አስጥተዋል።

ቡድኑ እጅግ የቆሸሸ ድርጊት የሚፈጽምና በጭካኔ የተሞላ መሆኑን ይፋ አድርገዋል።

ለአብነትም ከዚህ ቀደም ቡድኑ ከሳዑዲአረቢያ አገር ለቀው እንዲወጡ የተደረጉ የትግራይ አካባቢ ተወላጆች ወደ ርዋንዳ እንዲላኩ ማድረጉን አስታውሰዋል።

ይህ ገመናውን የማውጣት ድርጊታቸው ደግሞ ኢትዮጵያን በሐሰት እየወነጀሉ ለሚገኙ ሃይሎች የሚዋጥ አልሆነም።

የስደተኞች ኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አንቶንዮ ቪቶሪኖ የኢትዮጵያ ሃላፊዋ አቺንግ አስተያየት ተቋሙን የማይወክል መሆኑን በመግለጽ፤ የድርጅታቸውን መርህና እሴት የጣሰም ስለመሆኑ ተናግረዋል።

ይህንን የዋና ዳይሬክተሩን አቋም የኤጀንሲው የቀጣናው ሃላፊ ሞሐመድ አብዲከር አጠናክረውታል።

“ለማንኛውም አካል ሳንወግን ገለልተኛ በመሆን ስራችንን እንሰራለን” በማለት ቢገልጹም የተፈጸመው ድርጊት ግን ይህንን አያረጋግጥም።

የአሸባሪውን ህወሃት ገመና የሚገልጥ ሁሉ ሰለባ መሆኑን የሚያሳይ ውሳኔ እያሳለፉ ለመርህና ለእሴት እንገዛለን፤ ገለልተኛ ሆነን እናገለግላለን ማለት ያስተዛዝባል።

ENA

Exit mobile version