አሸባሪው ህወሃት በአማራ ክልል ሰሜን ወሎና በጎንደር የህዝቡን የኢኮኖሚ መሰረቶች አውድሟል
አሸባሪው ህወሃት በአማራ ክልል ሰሜን ወሎና በጎንደር የህዝቡን የኢኮኖሚ መሰረቶች ማውደሙን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
ህዝቡን ለመከራና ስቃይ በመዳረግ ዳግም ወደ ፖለቲካ ስልጣን ለመምጣት አደገኛ ሙከራ ውስጥ የተዘፈቀው ላለፉት 27 አመታት ስልጣን ላይ የነበረው አሸባሪው ቡድን፤ አብዛኛው የትግራይ ክልል ህዝብን ከሴፍቲኔት ተረጅነት እንኳን ሊያላቅቅ አልቻለም፣ ቡድኑ ለክልሉ ህዝብም ደህንነት ያለውን ግዴለሽነት በተደጋጋሚ አሳይቷል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አሸባሪ ቡድኑ በወረራቸው የሰሜን ወሎና ጎንደር አካባቢዎች ያደረሰው መጠነ ሰፊ ውድመት የአማራ ህዝብ ጠላትነቱን ዳግም ያስመሰከረበት መሆኑን ገልጿል።
በወረራ ከያዛቸው አካባቢዎች የሚወጡ ሪፖርቶች እንዳመለከቱት የብዙ ቤተሰቦች የኢኮኖሚ አቅሞችን አውድሟል፤ በወረራቸው አካባቢዎች ያሉ አርሶ አደሮች የአሸባሪው ታጣቂዎች የደረሱ ሰብሎችን እየዘረፉ ማመልከታቸውን ጠቅሷል።
“አርሶአደሩ ያከማቸው እህል ተዘርፏል የቀረውም እንዲወድም ሆኗል፤ የእርዳታ እህል ማከማቻ መጋዘኖች የአሸባሪው ቡድን የዘርፋ ሰለባ ከመሆናቸው ባሻገር ከተረጂዎችም ይቀማል” ብሏል መግለጫው፡፡
ቡድኑ ያስከተለው መጠነ ሰፊ ውድመት በግለሰብ ላይ ብቻ ሳይሆን እንደማህበረሰብ የህዝብ መገልገያዎችን የህፃናት መዋያዎች፣ ትምህርት ቤቶች፣ ኮሌጆች፣ ባንኮች፣ የጤና ማዕከላት፣ ሆቴሎችና ሎሎችም ተቋማት ወድመዋል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ
- የኢትዮጵያን – “መከራዋን ካልተሸከምንላት ኢትዮጵያዊነቱ ምኑ ላይ ነው” አብይ አሕመድ“ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ” እያሉ በስሟ ሲምሉ የነበሩ ብዙዎች ነበሩ፤ ከልባቸው ለቃላቸው ታምነው ልጅ የሆኗት ግን ጥቂቶች ብቻ ናቸው። አንዳንዶች በስሟ የሚገዘቱት እንጀራዋን ለመብላት እንጂ መከራዋን ለመካፈል አይደለም፤ በተቃራኒው እንጀራዋን በልተው ተረከዛቸውን አነሡባት” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ከስቅለት በዓለና የበዓሉ እሳቤ ጋር አዛምደው መልዕክት አስተላለፉ። ኢትዮጵያ በበርካታ ችግሮች ውስጥ እንዳለችና እንደምታልፈው በማስታወቅ “እንኳን አደረሳችሁ” መልዕክታቸው ውስጥ… Read more: የኢትዮጵያን – “መከራዋን ካልተሸከምንላት ኢትዮጵያዊነቱ ምኑ ላይ ነው” አብይ አሕመድ
- አቡነ አብርሃም “እንዳይረፍድብን” ሲሉ ለመጸጸት እንኳን ዕድል እንዳይታጣ አስጠነቀቁ“ወገኖቼ እንማርና እናስተምር፣ ወንጀልን እንጸየፈው፣ እንጥላው፣ ወንጀልን ተጸይፈን ወንጌልን እንውደደው፣ በወንጌል እንኑር፣ ወንጌል ሕጓም ስርዓቷም ያማረች ናት፤ ወንጌላዊ መኾን መልካም ነው፣ ወንጀለኛ መኾን ግን ሐጥያት ነው ብለዋል፡፡ እህትና ወንድም፣ እናትና አባትን አጎሳቁሎ ገንዘብ መውሰድ ለምንም አይጠቅም፣ ከእግዚአብሔር ጋር ያጣላል” ሲሉ ነው በእለት ስቅለት አቡነ አብርሃም ለምዕመናን ያስታወቁት። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲን የጠቅላይ ቤተክህነት ሥራ አስኪያጅ፣… Read more: አቡነ አብርሃም “እንዳይረፍድብን” ሲሉ ለመጸጸት እንኳን ዕድል እንዳይታጣ አስጠነቀቁ
- ደም ማነስ—መንስኤው፣ ምልክቶቹና ሕክምናውቤት የተባለች አንዲት ሴት እንዲህ ብላለች፦ “ደም ማነስ የያዘኝ በአሥራዎቹ ዕድሜ ሳለሁ ነው። ቶሎ ይደክመኝ፣ አጥንቶቼን ይቆረጥመኝ፣ እንዲሁም ትኩረቴ በቀላሉ ይከፋፈል ነበር። ሐኪሜ የብረት ማዕድን አዘዘልኝ። ኪኒኖቹን መውሰድ ጀመርኩ፤ አመጋገቤንም አስተካከልኩ። ብዙም ሳይቆይ ጤንነቴ ተሻሻለ።” ቤት የያዛት በሽታ በጣም የተለመደ የጤና እክል ነው። የዓለም የጤና ድርጅት እንደገለጸው ከሆነ ሁለት ቢሊዮን ሕዝብ ማለትም ከዓለም ሕዝብ 30… Read more: ደም ማነስ—መንስኤው፣ ምልክቶቹና ሕክምናው
- የትግራይ አመራሮች ከፌደራል መንግስት ጋር ያደረጉት የተለየ ስምምነት አለ?ሰሞኑን በራያ አላማጣ አቅጣጫ የትግራይ የታጠቁ ሃይሎች በግጭት መሰማራታቸውን ተከትሎ ከሃምሳ ሺህ በላይ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን ገለልተኛ ወገኖች አስታውቀዋል። ጎን ለጎን የትግራይ ከፍተኛ ባለስልጣናትና የዞን አስተዳዳሪዎች የተባሉ ሁለት ዓይነት መረጃዎች እየሰጡ ነው። መንግስት ግን ስምምነት መኖሩን ዘርዝሮ እነሱ በሚሉት መልኩ ባለመሆኑ ” ትዕግስት ፍርሃቻ አይደለም” እያለ ነው።ከትናንት በስቲያ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ግንባታ ማስተባበሪያ እና… Read more: የትግራይ አመራሮች ከፌደራል መንግስት ጋር ያደረጉት የተለየ ስምምነት አለ?
በግንባታ ሂደት ላይ ያለው የአዋሽ ወልዲያ ሃራ ገበያ የባቡር መንገድ ፕሮጀክት ሃላፊነት በማይሰማው አሸባሪ ቡድን የጥቃት ሰለባ ሆኗል ፡፡
“ሽብር ቡድኑ የሚያስከትላቸው መጠነ ሰፊ ውድመቶች ለትግራይ ህዝብ የሚፈይድለት ነገር እንደሌለ ይታወቃል፤ ይልቁንም የትግራይና የአማራን ህዝብ ወደ ባሰ ስቃይና እንግልት ያስገባል” ሲል ሚኒስቴሩ አመልክቷል፡፡
የሽብር ቡድኑ በሰሜን ወሎ እንዲሁም በጎንደር የፈፀመውና እየፈፀመ ያለው ውድመት በፖለቲካው አለሁ ለማለት የሚደረግ የመጨረሻው መፍጨርጨር እንደሆነም ነው የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ያስታወቀው፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት የአለም አቀፉ ማህበረሰብ በችግር ውስጥያሉና እገዛ የሚሹ በሰሜን ወሎና ጎንደር ያሉ ህዝቦችን ትኩረት እንዲሰጣቸው የጠየቀው መግለጫው፤ ወራሪው በያዛቸው አካባቢዎች ያሉ ዜጎች የተፋጠነ የሰብአዊ እርዳታ እንዲደርሳቸው ጥሪ አቅርቧል።
Ena