ETHIO12.COM

ጻድቃን ጦርነቱ በቀናት፣ ግፋ ቢል በሳምንታት ይጠናቀቃል አሉ፤ ጦራቸው ወደ ሩቅ ገጠሮች ማፈግፈጉን አስታውቀ

የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር / ትህነግ አማጺ ሃይል መሪ የሆኑት ጻድቃን ገብረትንሳይ ጦርነቱ እንደማይራዘም አመለከቱ። አዲስ ተጀመረ የተባለውን ጦርነት “የቀናት ጉዳይ ነው፣ ግፋ ቢል በሳምንታት ውስጥ ይጠናቀቃል” ሲሉ የተናገሩት ለኒውዮርክ ታይምስ ነው። የትግራይ ሕዝብ የዕድሜ ልክ ጠላት ሲሉ የጠሩዋቸው ኢሳያስ መወገድ እንዳለባቸው ለዓለም ማህበረሰብ አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እስካሁን ማጥቃት አለመጀመሩን፣ ነገር ግን ዝግጅቱን አጠናቆ መመሪያ እየተበቀ መሆኑንና ማጥቃት ከጀመረ ” ድረሱልኝ” የሚል ጊዜ የሚሰጥ እንዳልሆነ ማመልከቱን መዘገባችን ይታወሳል። ትህነግ ያወጣውን የድረሱልኝ ጥሪ ተከትሎ መከላከያ ይህንን ቢልም የተለያኡ ሃላፊዎችና ዓለም ዓቀፍ ሚዲያዎች ደጋግመው ጥቃት መጀመሩን እያስታወቁ ነው። የአየር ሃይል አዛዥም በባንዲራ ቀን አየር ሃይል “ጠላትን እየቀጠቀጠ ነው” ብለዋል።

ጻድቃን ጦርነቱ የቀናት፣ ግፋ ቢል የሳምንታት ጉዳይ መሆኑንን ሲናገሩ ከማን ወገንና እንዴት ገምግመውት እንደሆነ ዘገባው ጥልቅ ትንተና አልሰጠም። ነገር ግን ጻድቃን “… Airstrikes took out most of the Tigrayan artillery and forced its troops to retreat into the remote countryside.” በአየርና በምድር ከባድ መሳሪያ ድብደባ የተነሳ ከባድ መሳሪያና ሰራዊታቸው ራቅ ወዳለው የትግራይ ገጠራማ አካባቢ እንዳፈገፈገ ሳይደብቁ ተናግረዋል። (ሩቅ ገጠራማ የተባለው ቆላ ተንቤን ስለመሆኑ በግልጽ አልተገለጸም)

ኒውዮርክ ታይም የኢትዮጵያ መንግስት በትህነግ ሃይል የተያዙ ስፍራዎችን ለማስለቀቅ ማጥቃት መጀመሩን “አማጺ” ሲል የሚጠራቸው የትህነግ ሃላፊዎችና የምዕራብ ዲፕሎማቶች እንዳረጋገጡለት ይገልጻል። ከመንግስት ወገን ምንም መረጃ ማግኘት እንዳልቻለና በመገናኛ እጥረት ሳቢያ በዝርዝር ማቅረብ እንዳልቻለ አመላክቷል።

የመንግስት ቃለ አቀባይ የሆኑት ቢለኔ ስዩም ” መንግስት በመላው አገሪቱ ያሉትን ዜጎቹን ከሽብር ተግባራት የመጠበቅና የመከላከል ሃላፊነት አለበት” ሲሉ ለፍራንስ 24 መናገራቸውን በርካታ መገናኛዎች መግለጻቸው ይታወሳል።

የትግራይ ሃይል ማእከላዊ አመራር ሌተናል ጀነራል ጻድቃንን በስክል ማናገሩን የጠቀሰው የኒውዮርክ ታይም ዘገባ እንደሚያስረዳው የኢትዮጵያ መከላከያ ሃይል በድሮን፣ ከባድ መሳሪያና ተዋጊ ጀቶችን ተጠቅሞ በትግራይ አማጺ ሃይል ላይ ጥቃት የጀመረው ባለፈው ዓርብ ዕለት ነው።

“ሰኞ” አሉ ጻድቃን ” በሺህ የሚቆጠሩ የመከላከያ ሰራዊት ሰኞ የምድር ውጊያ ጀመሩ”፤ አክለውም “ጠላት” ያሉት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ለወራት ሲዘጋጅ መቆየቱን አመልክተው ” መጪው ጦርነት ለአገሪቱ ወሳኝ ጊዜ ነው” ሲሉ ተንብየዋል። እነሱም በተመሳሳይ ሲዘጋጁ እንደነበር አስታውቀዋል።

ስለጦርነቱ ወሳኝነት ያነሱት ጀነራሉ፣ የጦርነቱ ውጤት ወታደራዊ ፣ ፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ እንደሚሆን አመልክተዋል ። ይህንን ሲሉ ግን ምን ለማለት እንደሆነ ዝርዝሩን ዘጋቢው አልጠየቀም። ” ጦርነቱ የሚራዘም አይመስለኝም። የቀናት ጉዳይ ነው። ምናልባትም ሳምንታት” ሲሉ ቀን ቅጥረዋል። “The ramifications (the result, the consequence) will be military, political and diplomatic,” he said. “I don’t think this will be a protracted fight — a matter of days, most probably weeks.”



የድርጅታቸው ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ልክ እንደ ጻድቃን መደብደባቸውን በተደጋጋሚ በመግለጽ ለጦርነት አመቺ የሆነ ገዢ መሬቶችን እንደያዙ ማስታወቃቸው አይዘነጋም። በሰሜን ወሎ ያሉ የአካባቢውን አስተዳደሮች ያነጋገረው የጀርመን ድምጽ እንዳረጋገጠው የትህነግ ሃይል ( በነሱ አባባል የተረፈው) ከተማ እያወደመ፣ ያልቻለም እየሸሸ መሆኑንና ጥቃቱ ተጠናክሮ መቀጠሉን ማስታወቃቸው፣ የትግራይ የጀርመን ድምጽ ባልደረባ በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዳላከለ ሚዲያውን ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ላይ በየአቅጣጫው የተከፈተውን ዘመቻ በአሉታዊ ጎኑ አሰባስቦ ለዜናው ማዳመቂያነት ኢትዮጵያ ላይ ለተከፈተው የድራማ ማስዋቢያነት ይጠቅመው ዘነድ የሰገሰገው የኒውዮርክ ታይም ዘገባ ኢትርዮጵያ ከኢራን፣ ከቱርክና ከቻይና ድሮኖችን በመግዛት በደንብ መታጠቋን ገልጿል። አንድ የምዕራብ ኦፊሳል እንደነገሩት ጠቅሶ ባለፉት ስድስት ሳምንታት ብዛት ያለው የግዙፍ ካርጎ በረራ ከአረብ ኢምሬትስ ወደ ኢትዮጵያ መጓጓዙን ኒውዮርክ ታይም አመልክቷል። አስከትሎም ጻድቃን አረብ ኢምሬትስን ቀደም ሲልም ሆነ አሁን እርዳታ ማደጓን ማውገዛቸውን አትሟል። የኢሚሬትስ ባለስልጣናት ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ እንዳልሆኑም አስታውቋል።

“… Airstrikes took out most of the Tigrayan artillery and forced its troops to retreat into the remote countryside.” የአየር ጥቃቱ አብዛኛውን ከባድ መሳሪያና ሰራዊታቸውን ወደ ሩቅ ገጠራማ ስፍራ እንዲያሸሹና እንዲያፈገፍጉ እንዳደረጋቸው ጻድቃን ለኒውዮርክ ታይም ነግረዋል።

“የትግራይ የዘመናት ጠላት” ሲሉ የኤርትራን ፕሬዚዳንት ኢሳያስን የጠቀሱት ጻድቃን “ኢሳያስና ሰራዊታቸው ለቀጣናው መርዝ ናቸው” ብለዋል። “If the international community is earnestly looking for a peaceful solution, a settlement will not happen without taking care of Isaias.” አያይዘውም ” ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ሰላማዊ መፍትሔ ለማግኘት ከልብ የሚፈልግ ከሆነ ፣ ቅድሚያ ኢሳያስን መላ/ ሊያስወግዷቸው ይገባል” የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል።

በስልክ ጻድቃንን ያናገረው የናይሮቢው ዘገቢ ስጋና ደሙን በፍለገው ቦታ እየቀላቀለ ባተመው ጥሁፍ ” አሁን ትልቁ ጥያቄ የኤርትራ ሃይሎች ዳግም ኢትዮጵያን ይረዳሉ የሚለው ነው” ሲል ይጠይቅና፣ ሁለት የምዕራብ አገር ኦፊሳል እንደነገሩት ጠቆም አድርጎ የኤርትራ ሃይሎች አሁን ላይ (ከ1983 በሁዋላ ወደትግራይ እንድትቀላቀል የተደረገችው) ሁመራ እንደሚገኙ አንዳንዶችም አማራ ክልል እንደዘለቁ ገልጿል። ዘጋቢው ይህ ቢልም ጻድቃን የኤርትራ ሰራዊትን አስመልክቶ ያሉት ነገር የለም። አቶ ጌታቸውም ” የኤርትራ ሰራዊት ስለመኖሩ እርግጠኞች አይደለንም” ሲሉ ለፍራንስ 24 አስታወቀዋል።

May be an image of text

ይህ በንዲህ እያለ የኢትዮ12 መረጃ ምንጮች ትህነግ በኤርትራ ደገኞች ላይ አዲስ አቅጣጫ ማስቀመጡን ገልጸዋል። በዚህም ካሁን በሁዋላ ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ የኤርትራን ሕዝብና ሰራዊት መንቀፍ፣ ስማቸውን በመጥፎ ማንሳት፣ በጦርነቱ ተሳትፈው አስነዋሪ ተግባር እንደፈጸሙ ማቅረብ እንዲቆም ታዟል።

የመረጃዎቹ ባለቤቶች እንዳሉት ይህ የሆነው የፈጀውን ጊዜ ፈጅቶ ከኤርትራ ደገኛው ህዝብ ጋር የነበረን ጸብና ቂም ማለዘብ አስፈላጊ በመሆኑ ነው። ለዚህ ይመላል የኤርትራ ፕሬስ ጨምሮ የኤርትራ መንግስት ደጋፊዎች ዊኪሊክስ ቀደም ሲል ይፋ ያደረገውን መረጃ በማህበራዊ ሚዲያ እየተቀባበሉት ነው።

መረጃው እንደሚለው ከሆነ ትህነግ ከሻዕቢያ ጋር የመቀላቀል ጥያቄ አቅርቦ ” ትግራይ የኤርትራ አካል አይድለችም” በሚል ጥያቄው ውድቅ መደረጉን የሚያሳይ ነው። በሌላም በኩል በባድመ ጦርነት ሳቢያ ንብረታቸውን ተዘርፈውና ተክደው በረሃ ላይ እንደተደፉ የሚያስታውሱ፣ ” የአይናችሁ ቀለም አስጠላን ብለን …” በማለት ሟቹ የትህነግ ሊቀመንበር እንዳላገጡባቸው በመጥቀስ “ጊዜው አልፏል” የሚል አስተያየት እየሰጡ ነው።

ቢቢሲ ትግርኛ ሰሞኑንን ባተመው ትንተና የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ላይ እርምጃ ከተወሰደ በሁዋላ ኤርትራ በመግባት ሻዕቢያን የማስወገድ እቅድ እንደነበር ገልጿል። ጻድቃን አሁን ዓለም ዓቀፉ ህብረትሰብ ከልቡ ሰላምን የሚሻ ከሆነ ቀድሞ ኢሳያስን መንቀል እንዳለበት፣ ይህ ካልሆነ ሰላም እንደማይታሰብ፣ ኢሳያስ ብቻ ሳይሆኑ ሰራዊታቸው የቀጣናው ” መርዝ” እንደሆነ ማማልከታቸው ምን አልባትም ትህነግ ኢሳያስን ማስወገድ ዛሬም ዕቅዱ ውስጥ መሆኑንን የሚያሳይ ነው። ሆኖም ግን የዛሬው የትህነግ ቁመና ምኞት ወይም ቢቢሲ እንዳለው የረፈደበት ሃሳብ ነው።

Exit mobile version