ETHIO12.COM

ጦር ግንባር ገደብቶ መዘገብ እግድ ተጣለበት፤ ያለፈቃድ ግንባር መግባት ተከለከለ

የጦርነት ዜና የዩቲዩብ ቁርስና እራት ሊሆን አይገባም፤ “

ሰሞኑን የመከላከያ ሰራዊትን እንቅስቃሴ አስመልክቶ መረጃ መጥፋቱን፣ ቀደም ሲል ” አንድ ጀነራል ነገሩኝ” የሚሉ ወገኖች አሁን ምንም መረጃ ማግኘት ያልቻሉበትን ምክንያት ያውቁ እንደሆነ እንዲያስረዱ የጠየቅናቸው አንድ ከፍተኛ ባለስልጣን እንዳሉት ” ሁሉም ነገር ክፍት ሲሆን አጠቃቀሙን ባለመረዳትና ሆን ብለው በሚቀሳቀሱ ክፍሎች ሳቢያ ጉዳቱ ስላመዘነ ገደብ ተጥሏል” ብለዋል።

የመንግስት መገናኛው ውስጥ ከሚሰሩ ሃላፊዎች የአዲስ አበባ ዘጋቢያችን ያነጋገራቸው እንዳሉት ወደ ጦር ግንባር ሄዶ ለመዘገብ እንደቀድሞ ዝም ብሎ ዘው ማለት ተከልክሏል። መከላከያ ሳይፈቅድና ፍኖተ ካርታ ሳይሰጥ ግንባር ገብቶ መዘገብ ተከልክሏል። በዚህም ሳቢያ በየግንባሩ ያሉ የመንግስት ሚዲያ ሰራተኞች ከጦር ቀጠናዎች እንዲወጡ ተደርጓል።


ትህነግ – በሰሜን ወሎና በጎንደር የህዝቡን የኢኮኖሚ መሰረቶች በሙሉ ማውደሙና መዝረፉ ይፋ ሆነ

የሽብር ቡድኑ በሰሜን ወሎ እንዲሁም በጎንደር የፈፀመውና እየፈፀመ ያለው ውድመት በፖለቲካው አለሁ ለማለት የሚደረግ የመጨረሻው መፍጨርጨር እንደሆነም ነው የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ያስታወቀው፡፡


“የስነ ምግባር ችግር ያለባቸው የመንግስት የሚዲያ ባለሙያዎችና ግንባር ሆነው አጭር ቪዲዮና ፎቶ በክፍያ ለአንዳንድ የዩቲዩብ መገናኛዎች እንደሚያቀብሉ ተደርሶበታል” ሲሉ የአንድ የመንግስት ሚዲያ ሃላፊ ለተባብሪያችን ነግረውታል። ይህንኑ አጭር መረጃ በማስፋትና በመለጠጥ ለጠላት መረጃ ከመስጠት ጀምሮ የተጋነነ፣ የተሳሳተና ለመነገር ጊዜውን ያልጠበቀ መረጃ በማሰራጨት ጉዳቱ በማመዘኑ መከላከያ እዚህ ውሳኔ ላይ ሊደርስ እንደቻለና ውሳኔውም በመንግስት መደገፉን አመልክተዋል።

እሳቸው ለሚመሩት ተቋምና ለሌሎች ሚዲያዎች መመሪያ መተላለፉን ሃላፊው አስታውቀዋል። ቀደም ሲል ማንም ጋዜጠኛ መከላከያ እየደወለ መረጃ ይቀበል እንደነበር ያወሱት ሃላፊው፣ አሁን ግን የመመሪያ ወይም ከዚያ በላይ ሃላፊነት ያላቸው ብቻ ለመከላከያ ሃላፊዎች ደውለው መረጃ እንዲወስዱ ወይም ለሪፖርተሮች እንዲያመቻቹ መታዘዙን፣ ይህም ትዕዛዝ ለአሳቸው ተቋም ጭምር መድረሱን አመልክተዋል።

አቶ ሰውነት የተባሉ የህግ ባለሙያ ስለመመሪያው እውቀት እንዳላቸው አመልክተው ሚዲያዎችና ባለሙያዎቻቸው ዝርፊያን፣ ህገወጥ ተጋባርን በማጋለጥ ለጸረ ሙስናው ዘመቻ ድጋፍ በመስጠት የሌላው ትግል ወታደር በመሆን ሊሰሩ እንደሚገባ መክረዋል። መንግስት እስካሁንም የጦር ግንባሩን መረጃ በሩን ከፍቶ ልቅ ማድረጉ ያስገርማቸው እንደነበርም አመልክተዋል።

በተለይም ” አንድ ከፍተኛ ጀነራል ነገሩኝ” እየተባለ በየቀኑ ማብራሪያ ሲሰጥ ” እኚህ ጀነራል፣ ወይም እነዚህ ጀነራሎች ዲሲፒሊን የላቸውም? እንዴትስ ዝም ይባላሉ? በየስርቻው ማውራት ክብራቸውን ይመጥናል?” የሚሉ ጥያቄዎችን ይጠይቁ እንደነበር ያወሱት የህግ ባለሙያው፣ አሁን መልሱን ማግኘታቸውን ተናግረዋል። የጦርነት ዘገባ እጅግ ጥንቃቄ የሚያሻው ጉዳይ በመሆኑ ሁሉም ወገኖች ውሳኔውን በበጎ እንደሚመለከቱት ገልጸዋል።

የመንግስት ሚዲያዎች፣ ከግል ኢሳትን ጨምሮ ሌሎችም ዋጋ በሚያስከፍለው፣ ጊዜ በሚወስደውና ትጋትን በሚጠይቀው የጋዜጠኛነት ስራ ላይ በማተኮር የሕዝብን ብሶት፣ የመብት ረገጣ፣ የድሆንችን እንግልት፣ የመብት መሸራረፍ፣ በተደራጀ መልኩ የሚፈጸም የንግድ አሻጥርን በማጋለጥ ስራ ላይ ሊያተኩሩ እንደሚገባ በተደጋጋሚ “እውነቱ ያለው” የሚባሉ ጸሃፊ አስተያየት ሲሰጡ መቆየታቸው ይታወሳል።

360 እንደ ምሳሌ የሚያነሱት እኚሁ ሰው ሲነጋ ነገር በመጎንጎን ሲመሽ አንድ ሰው ላይ ዕለት ዕለት መዝፈን ሙያዊም ሆነ ሞራላዊ ልኬቱ ከዜሮ በታች አስታውቀው ነበር። መረጃና ማስረጃ ላይ የተደገፈ፣ አገርን የሚያቀና፣ ሕዝብን የሚጠቅም ትችት አጋብብ ቢሆንም፣ ሁል ቀን አንድ ሰው ላይ የቦንብ ናዳ ሲያወርዱ የሚኖሩ አካላትም ወደራሳቸው ቀልብ ሊመለሱ እንደሚገባ አመላክተው ነበር።

” የመከላከያ ሰራዊት በ…. አቅጣጫ ተላትን ሊደመስስ ተነቃነቀ” በሚል ግንባር ካሉ ወዳጆች እየሰሙ በሰበር ዜና አጅበው የሚያቀርቡ ክፍሎች ሰሞኑንን መቀዛቀዛቸው የዚሁ መመሪያ ውጤት የተነሳ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።

መከላከያም ሆነ መንግስት እንዲሁም ሕዝብ በከፍተኛ ደረጃ ዋጋ በመክፈል መረጃ ለህዝብ በማቅረብና አገር በማስቀደም የሚሰሩትን ሚዲያዎችና ባለሙያዎች ለይቶ እንደሚያውቃቸው ያስታወቁት ከፍተኛ ባለስልጣን ደንቡ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ እነዚህ ሚዲያዎችና ባለሙያዎቹ ከማንም በላይ ስለሚረዱት፣ አስቀድመውም ለጠላት መረጃ በመስጠት በኩል ተሳታፊ ባለመሆናቸው፣ ከኪሳቸው በላይ አገርና ሕዝብን ስለሚያስቀድሙ ውሳኔውን በበጎ መልኩ እንደሚያዩት እምነታቸው መሆኑንን አመልክተዋል። ባለስልጣኑ ይህን ያሉት ምን አልባት ገደቡ ቅሬታ ሊያስነሳ እንደሚችል ተጠይቀው ነው። ሲያጠቃልሉ እንዳሉት ሁሉም የመንግስት ሚዲያዎች የክልልን ጨምሮ እግድ ስለሚመለከታቸው ከተፈቀደው ፍኖተ ካርታ ውጭ ወደየትም በፈቃዳቸው እንደማይነቀሳቀሱ አመልክተዋል።

Exit mobile version