Site icon ETHIO12.COM

መከላከያ ወቅታዊ መረጃ ሰጠ፤ ትህነግ ቀጣይ ጦርነት መቋቋም እንዳይችል ተድርጎ እየተመታ ነው

ጀግናው አየር ኃይላችንም ለምድር ኃይሉ ከሚሰጠው ድጋፍ በተጨማሪ በጥልቀት እየገባ የጠላትን የመሳሪያ ማከማቻ ፣ የጥገና ቦታዎችን ፣ ማሰልጠኛዎችን፣ የማዘዣ ጣቢያዎችን እና የሎጂስቲክ አቅርቦት የሚያቀርቡና ሃብት የሚያሸሹትን ተሽከርካሪዎች እንዲሁም ከባድ መሳሪያዎቻቸውን ማውደም ችሏል። ይህ በጥንቃቄ ተጠንቶ የተለየ ወታደራዊ ዒላማ በመሆኑ ጠላት የተለመደ ጩኸቱን እንዲያሰማ ያደረገው ስኬታማ ምት ነው።

ከመከላከያ ሕዝብ ግንኙነት የተሰጠ መግለጫ ።

ጠላት በመረጠው የውጊያ ስልት ከፍተኛ ኪሳራ እያስተናገደ ይገኛል ።

አሸባሪው ህወሃት የትግራይን ሕዝብ ከሕጻን እስከ አዋቂ ለወረራ በማንቀሳቀስ ያለ የሌለ ኃይሉን በወሎ መርሳ አቅጣጫና በሃራ ጭፍራ በኩል አሰማርቷል።

ሀገር የማፍረስ ህልሙን የገበሬ አዝመራን አጭዶ ከመውሰድና ንብረት ከመዝረፍ እንዲሁም ከማውደም በተጨማሪ ” ከፍተኛ የሰው ብዛትና የሀገር ሃብት አለበት” ብሎ በመረጠው የሐይቅ አቅጣጫን ተከትሎ ለመግባት በሁሉም ግንባር ኃይሉን አሰባስቦ ውጊያ ከፍቷል።

ጠላት ሕዝቡን ያሰለፈው በዋናነት በሦስት አሰላለፍ ከፍሎ ነው። የመጀመሪያው በግንባር የሚዋጋና በሰው ኃይል የበላይነት ወስዶ ፍላጎቱን ለማሳካት እየጣረ ሲሆን ፤ ሁለተኛው የቅርብ ድጋፍ ሰጭ ሆኖ የሚተካ፣ ቁስለኛ የሚያነሳ፣ የሕዝብ ሃብት ዘርፎ የሚያሸሽ እና የሚያወድም ሆኖ የተደራጀ ነው። ሦስተኛው ፣ ለቀጣይ ግዳጅ ተዘጋጅቶ የሚጠብቅ አድርጎ ሕዝቡን የቡድን ፍላጎቱ ማስፈፀሚያ መሳሪያ እንዲሆን ወደ ጦርነት ማግዶታል።

የወገን ኃይል ፣ የውጊያ ሂሳብ የሚወራረደው ባሰለፍከው ቁጥር ብቻ ሳይሆን በሚቀርህ ኃይልም ጭምር መሆኑን አውቆ… የጠላት ኃይል ቀጣይ ጦርነትን ሊሸከም በማይችልበት ሁኔታ እየደመሰሰው ይገኛል። ይህ የጠላት ፍላጎት በከሃዲ መሪዎቹ ቀንም ጭምር ቆርጠው ከዚህ እንገባለን፤ እንዲህ እናደርጋለን ያሉትን ፍላጎት ሠራዊታችን በከፍተኛ ተጋድሎ እያመከነው ይገኛል።

የተለያዩ የክልል የፀጥታ አካላት ተጋድሎ እና የሕዝቡ ድጋፍ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ፣ ወደ ደሴና ኮምቦልቻ ሰርገው የገቡ 17 ውዥንብር ፈጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አውሏል። የአማራ እና የአፋር ወጣቶች ከሠራዊታችን ጋር እንደ ክልል ልዩ ኃይሎችና ሚሊሻዎች ግንባር ድረስ በመፋለም ላይ ናቸው።

ጀግናው አየር ኃይላችንም ለምድር ኃይሉ ከሚሰጠው ድጋፍ በተጨማሪ በጥልቀት እየገባ የጠላትን የመሳሪያ ማከማቻ ፣ የጥገና ቦታዎችን ፣ ማሰልጠኛዎችን፣ የማዘዣ ጣቢያዎችን እና የሎጂስቲክ አቅርቦት የሚያቀርቡና ሃብት የሚያሸሹትን ተሽከርካሪዎች እንዲሁም ከባድ መሳሪያዎቻቸውን ማውደም ችሏል። ይህ በጥንቃቄ ተጠንቶ የተለየ ወታደራዊ ዒላማ በመሆኑ ጠላት የተለመደ ጩኸቱን እንዲያሰማ ያደረገው ስኬታማ ምት ነው።

ወደፊትም ጥቂቶች ለሕግ ባለመገዛት በኃይል ከውስጥና ከውጭ ኃይሎች ጋር አብረው ኢትዮጵያን ለማፍረስ ቢጥሩም ፣ እኛ ልጆቿ እንዳያፈርሷት እናደርጋቸዋለን። የሕዝባችን እንባ ይታበሳል።

ኢትዮጵያ በልጆቿ መሰዋእትነት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኖራለች!

የመከላከያ ሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

ጥቅምት 11/2014 ዓ.ም

Exit mobile version