Site icon ETHIO12.COM

የፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ የሁለት ዳኞችን ያለመከሰስ መብት አነሳ

የፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ የሁለት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞችን ያለመከሰስ መብት እንዲነሳ ውሳኔ ማሳለፉን የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ጽህፈት ቤት ገለጸ፡፡

የጉባዔው ጽህፈት ቤት እንደገለጸው÷ የኢፌዴሪ ፍትህ ሚኒስቴር ሁለት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች በወንጀል መጠርጠራቸውን በመጥቀስ ምርመራ ለማድረግ ያስችል ዘንድ ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ ለጉባዔው ጥያቄ አቅርቧል፡፡

ይህን ተከትሎ የፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ጥቅምት 12 ቀን 2014 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በቀረበው ጥያቄ ላይ ተወያይቶ በአዋጅ ቁጥር 1233/2013 አንቀጽ 34 (2) መሰረት የሁለቱንም የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች ያለመከሰስ መብት እንዲነሳ መወሰኑን ከፍትህ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

(ኤፍ ቢ ሲ)

Exit mobile version