Site icon ETHIO12.COM

ኢትዮጵያ በራሷ ዜጎች ላይ ጥቃት አልሰነዘረችም!

ኢትዮጵያ በአሸባሪው ህወሓት የጦር ማሰልጠኛና መሳሪያ ማከማቻ ስፍራ ላይ እንጂ በራሷ ዜጎች ላይ ጥቃት አልሰነዘረችም ሲል ዋን ወርልድ አስገነዘበ።

የኢትዮጵያ አየር ሃይል አሸባሪው ህወሃት በሚጠቀምባቸው የጦር ማሰልጠኛዎችና መሳሪያ ማከማቻዎቸ ላይ የወሰደውን እርምጃ ተከትሎ አንዳንድ የውጭ መገናኛ ብዙኋን ዜጎች ላይ ጉዳት ደርሷል በሚል የሚያቀርቡትን ዘገባ ሐሰተኝነት ዋን ወርልድ ባወጣው ሀተታዊ ጽሑፍ አጋልጧል።

አንዳንድ የምዕራባውያን ሚዲያዎች አየር ሃይሉ የሽብር ቡድኑን ማሰልጠኛዎችና የጦር ማከማቻ ስፍራዎች ላይ ያደረገውን ጥቃት “የራሱን ዜጎች አጠቃ” በሚል የሚዘግቡት “አሜሪካና ምእራባውያን በሊቢያና ሶርያ ያካሄዱትን የውክልና ጦርነት ለመድገም ነው” ብሏል።
“አትዮጵያ በራሷ ዜጎች ላይ ጥቃት አትሰነዝርም አየር ሃይሏ አሸባሪው ህወሓት የሚጠቀምበትን የጦር ማሰልጠኛና መሳሪያ ማከማቻ ስፍራ ላይ እርምጃ ወስዷል እንጂ” በማለት አስገንዝቧል።

ምዕራበውያኑ ይህንን ክስ የሚያሰሙት በጥቃቱ የጅምላ ጭፍጨፋ ተከስቷል በማለት በመንግስት ላይ አለም አቀፍ ጫና ለመፍጠር ነው በማለት አብራርቷል።

ጫናቸው እንዲሳካና በእጅ አዙር የሚመሩትን መንግሰት ለመቋቋም ይህን የመሰሉ ክሶችና ሰብአዊነት የተባለ ጭምብል ያጠልቃሉም“ ሲል ነው ጽሑፉ ያተተው።

የኢትዮጵያ መንግሰት የተናጠል ተኩስ በማድረግ ለሰላም ሰፊ ርቀት ቢጓዝም አሸባሪው ቡድን በሽብር ድርጊቱ በመቀጠሉ መንግስት በራሱ ሉዐላዊ ግዛት ውስጥ የአሸባሪ ድርጅትን እንቅስቀሴ የመግታትና እርምጃ የመውሰድ ሙሉ ስልጣንና ሀላፊነት አለው ሲል አመልክቷል።

“በአንዳንድ የተመድ የስራ ሃላፊዎችና ምዕራባውያን ድጋፍ የሚደረግለት አሸባሪው ቡድን በደጋፊዎቹ አማካኝነት የምዕራባውያንን ጥቅም ለማስጠበቅና ቡድኑን ወደ ስልጣን ለመመለስ ብዙ ጥረት ተደርጓል” ሲል አብራርቷል።

አሁን ግን የኢትዮጵያ መንግሰት በውስጥ ጉደዩ ጣልቃ የሚገቡ አካላትን ከአገር በማስወጣቱና ለምዕራበውያን ጫና እጅ ባለመስጠቱ የሚፈልጉት አካሄድ እንደማይሳካ አውቀውታል ብሏል ዘገባው።

(ኢዜአ)

Exit mobile version