Site icon ETHIO12.COM

ከቱርክ ሊባረሩ የነበሩት 10የምዕራብ ሃገራት አምባሳደሮች ይቅርታ ጠየቁ

“ ከዚህበኋላ ይጠነቀቃሉ ብዬ አስባለው " ኘሬዝደንት ኤርዶጋን

(ሰላም ሙሉጌታ)

ሃገራቱ በኤምባሲዎቻቸው በኩል ባወጡት መግለጫ በቱርክ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ እንደማይገቡ አስታውቀዋል ። ሊባረሩ ከነበሩ ሃገራት አንዷ የሆነችው አሜሪካ በኤምባሲዋ የትዊተር ገፅ ላይ
” አለማቀፉ የዲኘሎማቲክ ህግ አንቀፅ 41 አክብረን እሰራለን ” ብላለች ።ይህ አንቀፅ ዲኘሎማቶች በሚሰረማሩበት ሃገር የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ እንዳይገቡ የሚከለክል ነው። ቀሪዎቹም ሃገራት ይህን አቋም እንደሚቀበሉ አረጋግጠዋል።መልዕክቱንም በማህበራዊ ሚድያዎቻቸው አጋርተዋል።

የአሜሪካ፣የጀርመን፣ፈረንሳይ፣ስዊድን፣ኖርዌ፣ዴንማርክ፣ኒውዝላንድ ፣ፊንላንድ፣ኔዘርላንድስ እና ካናዳ ኤምባሲዎች ናቸው ይቅርታውን የጠየቁት።ኤምባሲዎቹ ቱርክ በአመፅ ቅስቀሳ ጠርጥራ ያሰረችው ኡስማን ካቫላ የተባለው ሰው ከእስር እንዲፈታ የሚጠይቅ መግለጫ ማውጣታቸው ነበር ቱርክን ያስቆጣት ፤ የኤምባሲዎቹ ተግባር ጣልቃ ገብነት ነው በሚል።

አስሩ ሃገራት መግለጫ ያወጣቱ ኘሬዝደንት ሬሲኘ ጣይብ ኤርዶጋን ከቀናት በፊት አምባሳደሮቹን ሃገራቸው እንደማታስተናግድ እናእንደምታባርር ማሳወቃቸውን ተከትሎ በአፈፃፀሙ ላይ ከካቢኔያቸው ጋር ለመምከር በተቀመጡበት ወቅት ነው።
የኤምባሲዎቹን መግለጫ የቱርክ መንግስት የተቀበለ ሲሆን ይቅርታውን ተከትሎ ውሳኔውን ሽሯ፤ ተፈጥሮ የነበረው ውጥረትም ረገብ ብሏል።

በጉዳዩ ላይ አስተያየት የሰጡት ኘሬዝደንት ኤርዶጋን ” እነኚህ ተወካዮች ከዚህ በኋላ ስራቸውን በጥንቃቄ ይከውናሉ የሚል እምነት አለኝ ፤ ነፃነታችንን የማያከብሩ እና ነገር የሚያቀጣጥሉ በዚህች ሃገር ሊኖሩ አይችሉም ፤ ማንም ይሁን ማን ” ብለዋል።

Exit mobile version