Site icon ETHIO12.COM

ኢሳያስ መጨረሻውን ተነበዩ

ኢሳያስ አፈወርቂ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ሕወሓትን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ ወያኔ ጣእረሞት ላይ ሆኖ እየተወራጨ ነው የመሞቻው ጊዜም በጣም እየቀረበ ነው ይላሉ። እየቀረበ ነው ስንል በጣም ከበዛ ሳምንታት ለማለት ነው። የኢትዮጵያ ጦር ከትግራይ መውጣቱ ና ከዛም ቀጥሎ በነበሩት ጊዜያት ወደ አማራና አፋር አንዳንድ ቦታዎች ገብቶ መቆጣጠሩን ያዩ ሰዎች የኢትዮጵያ ጦር በጣም እንደተዳከመ አድርገው ሲያወሩና ሲያስወሩ ነበር።

ያ ግን ሆን ተብሎ የተሠራ ታክቲክ ነበር በዚህም ሰፊ ወታደራዊ ፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ ትርፍ ተገኝቶበታል ይላሉ። ከግጭቱ ቀደም ብሎ ሕወሓት አስቦና አቅዶ ተራራማና ሸለቋማ በሆኑ ቦታዎች መሣርያ በስፋት አካማችቶ ነበር።

በከፍተኛ ቁጥር የሰለጠኑ ወታደሮች ነበሩት ድንገት በከፈተውም ጥቃት በርካታ መሣርያ መያዝ ችሎ ነበር የኢትዮጵያ መከላከያንም ማዳከም ችሎ ነበር ይላል። ያ ሲቀለበስ ወደ ሌላ አዲስ ጨዋታ ገባ ይኸውም መሣሪያዎችን ገጠራማ ቦታዎች በመቅበር እና የሠው ሀይሉን በየቦታው በመበተን በአጭር ኪሳራ የኢትዮጵያን ሀይል እንደ ጨው በሟሟት አዲስ አበባን ድጋሚ መቆጣጠር ነበር።

ስትራቴጂውን ሲያረቅ የክረምት ወራት ውስጥ ያሉ እንደ ጭቃ ጉም ዝናብ ከትግራይ ገደላማና ተራራማ ገጠሮች ጋር በሚፈጥሩት ህብር የምድር ጦር ከባባድ ተሽከርካሪዎችና የአየር ሀይል ክፍሎች ለሚያደርጉት ፀረ ሽምቅ ውጊያ እንቅስቃሴ እንቅፋት መሆን፤ የደጀኑ ወቅታዊ የሞቀ ድጋፍ ከአሜሪካ አውሮፓ ከባድ ጫና ጋር በማቀናጀት ነበር ብለዋል።

ሆኖም የኢትዮጵያ መሪዎች ሁኔታውን አንብበው ጦራቸውን አራቁ በዚህ ከዲፕሎማሲያዊና ፖለቲካዊ ትርፍ ውጭ ጦራቸው ላይ የሚደርሰውን ጉዳት በከፍተኛ ደረጃ ቀነሱ። ጊዜ አግኝተው የወደፊት አላማዎችን ጭምር ታሳቢ ያደረገ ከባድ ጦር እየገነቡ ነው። በተጨማሪም የሕወሓትን ሀይል እስከ ደሴ የተዘረጋ ወጥመድ ሰርተው ሰፊ ቀጠና ውስጥ በመለጠጥ የሰለጠነ ሠው ሀይሉ ላይ ሊገመት የማይችልና ታይቶ የማይታወቅ ሰብአዊ ኪሳራ እያደረሱበት ነው። አለኝ የሚለውን ከባድ መሣርያውንም በሙሉ እያስተፉት ነው ብለዋል።

ተከቦና ታጥሮ ያለው ሕወሓት ከአጭር ጊዜ የውጊያ ጫና ውጪ የሠው ሀይሉን እያሰለጠነ መተካት ቢችል እንኳ ለረጅም ጊዜ ጦርነት ወሳኝ የሚባሉ እንደ ነዳጅ የመሣርያ መለዋወጫዎችና ተተኳሽ ነገሮችን ለመተካት የሚችልበት አማራጭ የለውም። ያ ማለት በሜካናይዝድ በብርጌድ Conventional ውጊያ መዋጋት የሚችሉባቸው ጊዜያት እየተሟጠጠ ነው።

ስለሆነም የኢትዮጵያ ጦር በሳምንታት ውስጥ አካሄዶችን ቀልብሶ መቀሌ ይገባል ያልኩት በርካታ ነገሮች ታሳቢ በማድረግ ነው ብለዋል። የኢትዮጵያ ጦር ቀጣይ መቀሌ ሲገባ እንደበፊቱ በየተራራውና ገደላገደሉ በከፍተኛ ደረጃ መሣርያ ያከማቸ ብዛት ያለው የሠለጠነ ሀይል በየቦታው የበተነ ከባድ ሀይል እንደማይገጥመው ከዛ ይልቅ ብዙም ልምድና ስልጠና የሌለው ሞራሉ የደቀቀ ከከባባድ መሣርያ ይልቅ የነፍስ ወከፍ አነስተኛ መሣርያ የያዘ ተስፋ ያጣ ሀይል ነው ሚጠብቀው። ይህም ደግሞ በቀላሉ ማሸነፍ የሚቻል ነገር ነው ብለዋል።

ሕወሓት የመቀጠል ተስፋ አለው ወይ ተብሎ ለተጠየቀው ሲመልስ ያንን በ 3 ከፍለን ማየት እንችላለን ይላሉ።

1. ሕወሓት በውጊያ አሸንፎ አዲስ አበባ ይጠጋል ብንል እንኳ የኤርትራ ሰራዊት እንደለመደው በቀናት ውስጥ መቀሌ ይገባና ያ ሁሉ ልፋቱ ይቀለበሳል ያንን እነሱም ያውቁታል።

2. ጦርነቱ ባልተፈለገ ሁኔታ ለረጅም ጊዜ ይቀጥልና ህዝቡ ተሰላችቶ ኢትዮጵያ ሳትፈልግ ሕወሓት ጋር የሠላም ውል ትፈራረማለች።

3.ሕወሓት ሁኔታዎች እንሚያመለክቱት በአጭር ጊዜ ተሸንፎ ይጠፋል ነው። በሁሉም መስፈርት ስትገመግም የሚሆነው ሶስተኛው አማራጭ ብቻ ነው ብዬ በእርግጠኝነት ልነግርህ እችላለሁ በማለት የሕወሓት ጉዳይ ከንግዲህ የአጭር ጊዜ ጉዳይ መሆኑን አብራርተዋል።

ዝግጅት ክፍል – ከማህበራዊ ሚድያ ተተርጉሞ የቀረበና ለዝግጅት ክፍላችን የተላከ


Exit mobile version