Site icon ETHIO12.COM

የማይካድራ ጭፍጨፋ በትህነግ መዋቅር መፈጸሙ በምርመራ ይፋ ሆነ

በማይካድራ አማራዎች ላይ ብሔርን መሰረት አድርጎ የተፈፀመው ጭፍጨፋ ሳምሪ በተሰኘው የሕወሓት ገዳይ የወጣት ቡድን እና በሕወሓት አመራርና ታጣቂዎች መፈፀሙን ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ጥምር የምርመራ ሪፖርት አረጋገጠ፡፡

ጥቅምት 24 ሌሊት በመከላከያ ሠራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት በመክፈት ጦርነት የከፈተው የሽብር ቡድኑ ሕወሓት ከጥቅምት 27 እስከ 30/2013 በማይካድራ የሚኖሩ አማራዎችን በመለየት የዘር ጭፍጨፋ መፈፀሙን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን እና የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ጽሕፈት ቤት በጋራ ያደረጉት ምርመራ ሪፖርት አረጋግጧል፡፡ዛሬ ይፋ የሆነው ሪፖርቱ ዘርን መሰረት አድርጎ በተፈፀመው ጭፍጨፋ ሳምሪ ከተሰኘው ቡድን በተጨማሪ አካባቢውን ያስተዳድር የነበረው የሕወሓት መዋቅር ውስጥ ያሉ የቀበሌ አመራሮችና ታጣቂዎች በቀጥታ ተሳታፊ እንደሆኑ ይፋ አድርጓል፡፡

የሽብር ቡድኑ በዘር ማጥፋት ጭፍጨፋው ከ1 ሺሕ በላይ ንፁሃንን በግፍ ገድሏል፡፡የኢትዮጵያ መንግሥት ይህን እውነቱ በተደጋጋሚ ሲያሳውቅና ገዳይ ቡድኑም ጭፍጨፋውን ከፈፀመ በኋላ ወደ ሱዳን በመሸሽ በስደተኛ መጠለያ ጣቢያ ውስጥ መግባቱ ሲገለፅ የነበረ ቢሆንም ለሽብር ቡድኑ ያደሩ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ይህን እውነት ደፍረው የዘገቡበት ወቅት አልነበረም፡፡ ይልቁንም ከዚህ ወንጀል ራሱን ለማንፃትና መንግሥትን ሲኮንን የነበረውን ሕወሓት ሲደግፉና የወንጀሉን ፈፃሚ ሲያድበሰብሱ እንደነበር ይታወሳል፡፡

@tikvahethiopia ሪፖርት

በትግራይ ግጭት ሁሉም አካላት ሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ፈፅመው መገኘታቸውን የጋራ ሪፖርቱ አመላክቷል።

ተፈፅመዋል የተባሉ ጥሰቶች ፦

• ከሕግ ውጪ ግድያና ርሸና፣

• ማሰቃየት፣

• ወሲባዊና ጾታዊ ጥቃቶች፣

• በስደተኞች ላይ የተፈጸሙ ግፎች እንዲሁም ሰላማዊ ሰዎችን በኃይል ማፈናቀል ይገኙበታል።

በጋራ የምርመራ ሪፖርቱ ከቀረቡት ክስተቶች መካካል በጥቂቱ ፦

በማይካድራ “ሳምረ” በተባለ ቡድን የተፈጸመ ጥቃት ይገኝበታል ፤ ምንም እንኳን ቁጥሩን እርግጠኛ ለመሆን ባይቻልም ከ200 በላይ ሰዎች በዚህ ጥቃት ተገድለው በጅምላ መቃብሮች መቀበራቸውን ተመላክቷል።

የመከላከያ ሠራዊት እና የአማራ ልዩ ኃይል ከተማውን በተቆጣጠሩባቸው ቀጣይ ቀናት የትግራይ ተወላጅ የሆኑ የማይካድራ ከተማ ነዋሪዎች ላይ የበቀል ግድያዎች መፈጸማቸውን እና የፋኖ ሚሊሺያዎችም በግድያው መሳተፋቸውን ሪፖርቱ ያስረዳል።

በአክሱም ከተማ የኤርትራ ሠራዊት አባላት ከ100 በላይ ሲቪሎችን መግደላቸውን፤ በወቅቱ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት ግድያዎቹ ሲፈጸሙ ጣልቃ ሳይገቡ መቅረታቸውን ሪፖርቱ ገልጿል።

በቦራ አምደውሃ ፣ በቦራ ጫማላ እና ማኢ ሊሃም ከተሞች ከ70 በላይ ሲቪሎች በመከላከያ ሠራዊት መገደላቸውን የጋራ ሪፖርቱ ገልጿል።

እነዚህን እና ሌሎች የግድያ ማስረጃዎችን በመያዝ የሕግ ትንታኔ የሰጠው የምርመራ ቡድኑ በዚህ ጦርነት ውስጥ “የጦር ወንጀሎች” ተፈጽመው ሊሆን እንደሚችል ጠቁሟል።

Exit mobile version