ETHIO12.COM

አሜሪካና አውሮፓ ሕብረት ያበሳጨው ክተትና አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ

ብሉምበርግ የሚባለው አንዱ የሳይበር የመረጃ ጦረኛ የአዲስ አበባ ሕዝብ በነፍስ ወከፍ መሳሪያ እንዲታጠቅ መታዘዙን ገለጸ። “መሳሪያ ያልችሁ በሃያ አራት ሰዓት አስመዝግቡ” መባሉን ነው ያዞረው። ” ስንዴ መለመን መቆም አለበት” ሲባል ” እርዳታ ወደ አገር ውስጥ እንዳይገባ ተባለ” የእንግሊዝ ሚዲያዎች ዘገቡ። ቢቢሲ ቦታ ሳይጠቅስ ሸኔ በርካታ ቦታ ያዘ አለ። አመሪካና አውሮፓ ” ኦነግና ትህነግ ወደ አዲስ አበባ እንዳታመሩ” ሲሉ አዛኝ መስለው ሕዝብን አስጨነቁ።

ልክ መንግስት ከተት ሲያውጅና ሕዝብ ሲነቃነቅ፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንደሚታወጅ ሲታወቅ አሜሪካ ከመጪው የነጮቹ አዲስ ዓመት ጀመሮ ኢትዮጵያን ከአጎዋ ማገዷን ይፋ ያደረገችው። ገና ሁለት ወር እያለ ለምን ዛሬ እገዳው እንዲነገር ተፈለገ? ይህ ሽብር መንዣ ነው። እሱ ብቻ አይደልም የኢትዮጵያን ባለስልጣኖች በጄኖሳይድ ለመክሰስና ለመወንጀልም ስራው መተናቀቁን ኤቢሲ ዘግቧል።

በአማራ ክልል በጅምላ ያለቁትን ወገኖች፣ የተደፈሩ፣ ንብረታቸው የወድመና የተፈናቀሉ፣ ከሁሉም በላይ የጅምላ መቃብራቸው በአደባባይ የታየ፣ ሰሞኑን በኮምቦልቻ. እንዲሁም በአፋር ጋሊኮማ የረገፉ ዜጎች ለአሜሪካ ነብስ የላቸውም። የዚህ ምክንያቱ ምን ይሆን? ለምንስ ይሆን በዚህ ደረጃ ጥርስ የተነከሰው?

የአውሮፓ ህብረት ከፍተኛ ባለስልጣን ኃላፊ ጆሴፕ ቦሬል ትህነግና ሸኔ ወደ አዲስ አበባ እንዳያቀኑ ሲሉ ያስጠነቀቁት አስቸኳይ አዋጁ እንደታወጀ ነው። ከተቱ ሕዝብ አነቃንቆ ፈረሰ የተባለው የአገር መከላከያ በአንዳንድ ቦታዎች ስልት ቀይሮ ማጥቃት በጀመረበትና አንዳንድ ውጤቶች መታየት በጀመረበት ወቅት ላይ ነው። የኢትዮጵያ መንግስት በሀገሪቱ “ህልውና እና ሉዓላዊነት” ላይ ተደቅኗል ያለውን “አደጋ ለመከላከል” የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በደነገገበት ቅጽበት ቦሬል አዛኝ መስለው አዲስ አበባ እንደተከበበች የሚያሳይ የስጋት ነገር ግን የሽብር ቲውት አደረጉ።

“አዲስ አበባን ለማጥቃትም ሆነ ለመክብብ በህወሓት ወይም በኦሮሞ ነጻነት ጦር የሚደረግ ማንኛውንም እርምጃ እንቃወማለን” በማለት የአውሮፓ ህብረት አቋም ነው ያሉትን አስፍረዋል። አክለውም በግልጽ ቋንቋ “በኢትዮጵያ በተደነገገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የአውሮፓ ህብረት ደንግጧል” ሲሉ ቦሬል፤ ሰላምን ለመቀበል ሁሉም ወገኖችሽ እድል እንዳላቸው አመላክተዋል። በኮምቦልቻ ስለተጨፈጨፉት ንጹሃን ግን ያሉት ነገር የለም። አገሪቱ ግን ሃይሏን አስተባብራ ዜጎቿን አምርራ ለመከላከል ስትነሳ ጩኸት ይበረክታል። አማራን እንደ ሕዝብ ከምድር ላይ ለማጥፋት ሲነሱ ምንም ያላሉ ዛሬ አማራም ሆነ ሌላው ሕዝብ ራሱን የሚከላከልበትና በወረራ የተያዘውን አካባቢውን ለማስለቀቅ ሲተም “ዋ” ይባላል።

አዲስ አበባ ያለው የአሜሪካ ኤምባሲም ሽብር በመንዛት ዜጎቹንና የአሜሪካን ፓስፖርት የያዙትን አገር ለቀው እንዲሄዱ ወይም እንዲያስቡበት አመልክቷል። ይህንኑ ጥሪውን በሚከፍላቸው ሪፖርተሮቹ አማካይነት አራብቷል።

የጀርመን ድምጽም በተመሳሳይ አስቸኳይ አዋጁ መታወጁን ተከትሎ ሽብር እየነዛ ነው። ከዛ በፊትም ቢሆን የቀላቢዎቻቸውን አቋም እያራመዱ ነው። የሚገርመው እነዚህ ወገኖችም ሆኑ ሌሎች ኢትዮጵያውያን የሚዲያ ሰራተኞች አማራ ምን በድሏቸው ይሆን? አማራ ምን ስህተት ፈጽሞ ይሆን? አሜሪካም ሆኑ አውሮፓውያኖቹ አማራ ምን አድርጓቸው ነው እንዲጠፋ የፈረዱበት … ልብ ያለው ልብ ይበል። ቁጭ ብለህ ከምታልቅ ታገል። እኔ ትግል ውስጥ ነኝ።

ያለው ዳኜ ከመሃል

Exit mobile version