Site icon ETHIO12.COM

ኦባሳንጆ መልዕክት ይዘው መቀለ ገቡ፤ ትህነግ ከገባባቸው አካባቢዎች ይለቃል

የአፍሪካ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ ሆነው በቅርቡ የተሾሙት የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሉሴጎን ኦባሳንጆ መቀለ መግባታቸው ተገለጸ። አሜሪካ ሃሳቧን መቀየሯ እየተነገረ ነው።

ሹመታቸው ይፋ እንደሆነ “ገለልተኛ ናቸው ብለን አናምንም” ያለው የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር /ትህነግ/ በማን አስገዳጅነት እንደሆነ ባይታወቅም ኦባሳንጆን ተቀብሎ በተቀመጡ የቀውስ ማቅለያና ማስወገጃ ስሌቶች ላይ እየተነጋገረ ነው።

የኢትዮ12 የአሜሪካ ተባባሪ እውቅ ዲፕሎማትን ጠቅሶ እንዳለው ኦባሳንጆ ሚሽን ይዘው መቀለ የገቡት ዛሬ ነው። ዲፕሎማቱ ዝርዝር ባይናገሩም ትህነግ በሃይል ከወረራቸው ስፋራዎች ሙሉ ለሙሉ እንዲወጣ የተቀመጠውን አግባብ ማሳወቅ የመጀመሪያ ስራቸው እንደሆነ አመልክተዋል።

ከኮምቦልቻና ደሴ ግንባር የጦርነት ዜና በሁዋላ ሰፊ ቁጥር ያለው ሃይል ወደ ግንባር መትመሙ፣ በደሴ በወገን ጦር ላይ ከጀርባ የተሰነዘረው ጥቃትና በኮምቦልቻ የተፈጸመው የጅምላ ግድያ ያስቆጣቸው በእልህ ወደ ጦር ሜዳ መግባታቸው አሜሪካንን እንዳስደነገጠ ዲፖሎማቱ አመልክተዋል። ችግሩ ወደከፋ መተላለቅ ከማምራቱ በፊት ጦርነቱ ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ እንዲቆም አሜሪካ በተናጠልና የጸጥታው ምክር ቤት በጋራ መጠየቁ ይታወሳል።

ከኢትዮጵያ ወገን ” በህዝብ የተመረጠ መንግስትና አሸባሪን እኩል ማየት ፍትሃዊ አይደለም። ተቀባይነትም የለውም” በሚል በወጣ መግለጫ ” የትግራይ ወራሪ ሃይል ወደ ክልሉ ተመልሶና ትጥቅ ፈቶ ካለሆነ በቀር ድርድር የሚባል ነገር የለም” ሲል አቋሙን ግልጽ አድርጓል። ከዚህም ጋር ጎን ለጎን ሚሊሻ፣ ልዩ ሃይል፣ ወዶ ዘማች፣ የቀድሞ ሰራዊት ተመላሽ አባለትን፣ ፋኖን እና የአካባቢ የጸጥታ አደረጃጀትን በማዋሃድ ወደ ቆቦ ዘልቆ መንገድ መቁረጡ፣ ዋግን በአብዛኛው መቆጣጠሩ፣ ከሚሴን መልሶ በመያዝ ጥቃት መጀመሩና እስከ ወልደያ የተዘረጋ ማጥቃት መጀመሩ በይፋ ባይነገርም ለትህነግ ሰራዊት ችግር እንደሆነበት እየተሰማ ነው።

በሌላ በኩል ጻድቃን በትግራይ ሚዲያ “ድርድር ብሎ ነገር የለም” ሲሉ ማስታወቃቸው ይታወሳል። እንደ እሳቸው ገለጻ አሁን ቡድናቸው እያሸነፈ በመሆኑ የብልጽግናን አመራሮችና የሚፈለጉ የሚሏቸውን ተቆጣጥሮ ወድ ፍርድ መውሰድ ቀጣዩ እቅዳቸው ነው። ጦርነቱ በቀናት ወይም ግፋ ቢል በሳምንታት እንደሚጠናቀቅ አስታውቀው ሙሉ ኦፕሪርሽን ውስጥ እየገቡት ጻድቃን ዛሬ በቀድሞው አቋማቸው ይጽኑ አይጽኑ ለጊዜው አልታወቀም።

ልክ ትግራይ ላይ እንደተደረገው ከማዕከልም ሕዝባዊ መልክ ይዞ በማዕበል ወደ “ህልውና ጦርነት” በተሸጋገርበት ወቅት የኦባሳንጆ ወደ ትግራይ መላክ ምን ዜና ይዞ እንደሚመጣ ለጊዜው ዲፕሎማቱ ያሉት ነገር የለም። ነገር ግን ትህነግ አሁን በአጁ ያሉትን የአማራና የአፋር አካባቢዎች ሙሉ በሙሉ ለቆ ለመውጣት ይስማማል የሚል ግምት እንዳላቸው አልሸሸጉም። ለቆ መውጣቱም ግን ቀላል እንደማይሆን ገልጸዋል። ምዕራብ ትግራይ የሚባለውና ትህነግ አለአግባብ ወስዶት ኖሯል የተባለው አካባቢ ጉዳይ ግን በቀጣይ የሚታይ ሊሆን እንደሚችል ተመልክቷል።

አዲስ አበባን ጨምሮ በመላው አገሪቱ ሕዝብ በትህነግ የመመራት ፍላጎት እንደሌውለውና መከላከያን ለመቀላቀል ፈቃደኛ መሆኑንን ማሳወቁን ሲሲጂ በፊት ገጹ አትሟል። ሲሲጂ ይህን ዜና በጉልህና ህዝብ ያለውም በአግባቡ በመዘገብ የመጀመሪያ ሆኗል።

የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማህማት የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሉሴጎን ኦባሳንጆ የሕብረቱ የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ ሆነው መሾማቸውን አስታወቁ።


Exit mobile version