ETHIO12.COM

ለጥፋት ሃይል ሊደርሱ የነበሩ ሲም ካርዶች፣ መሳሪያ፣ ሃሰተኛ የመሳሪያ ፈቃድ አዲስ አበባ ከተማ ተያዘ

ለአሸባሪዎቹ የህውሃትና የሸኔ ቡድኖች እኩይ ዓላማ ማስፈፀሚያ ሊውሉ የነበሩ በርካታ ሲም ካርዶች፣ሀሰተኛ የመሳሪያ ፍቃድና የሽጉጥ ጥይት በህብረተሰብ ጥቆማና ፖሊስ ባከናወነዉ የኦፕሬሽን ሥራ ከ2 ተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለፀ።

አሸባሪዎቹ የህወሓትና የሸኔ ቡድኖች ሀገርን ለማፈራረስ እኩይ አላማ አንግበውና መድናችን አዲስ አበባን የጦርነት አውድማ ለማድረግ ተላላኪ ባንዳዎችን አሰማርተው እየተንቀሳቀሱ ቢገኙም ህዝቡና የፀጥታ አካላቱ ተቀናጅተው በሰሩት ጠንካራ ሥራ ሴራቸው እየከሸፈ ይገኛል።

ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ልዩ ቦታው ሸራ ተራ የካቲት 23 ት/ቤት ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ሲሆን ለሽብር ቡድኖቹ እኩይ ዓላማ ማስፈፀሚያ የሚውሉ 2 መቶ 76 ሲም ካርዶችና ሀሰተኛ የጦር መሳሪያ ፍቃዶች እንዲሁም የሽጉጥ ጥይቶች በህብረተሰቡ ጥቆማ የኢንተለጀንስና የክትትል ቡድኑ ባከናወነው የኦፕሬሽን ስራ በግለሰብ መኖሪያ ቤትና ይዘው ሲንቀሳቀሱ በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ ከአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል ት/አደጋ ምርመራ ምክትል ዳይሬክተር መረጃው መገኘቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

የአሸባሪ ቡድኖቹን እኩይ ዓላማዎች ማክሸፍና መደምሰስ የሚቻለው በተባበረ የህዝብ ተሳትፎ መሆኑን የገለፀው የአዲስ አበባ ፖሊስ ሰላም ወዳድ የሆነው ህዝባችን የአሽብር ቡድኖቹን ተላላኪ ባንዳዎችን አጋልጦ በመስጠት እንደ ከዚህ ቀደሙ ትብብሩን አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ጥሪውን አቅርቧል ሲል አዲስ አበባ ፖሊስ ዘግቧል።


READ MORE


በሌላ ዜና ህገ-ወጥ የጦር መሳሪዎቹ እና ገንዘቡ የተያዘው በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ወንድይራድ ትምህርት ቤት አካባቢ ፖሊስ ሕብረተሰቡ የሰጠውን ጥቆማ መነሻ በማድረግ ባከናወነው ፍተሻ ነው።

የኮተቤ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ሀላፊ ኮማንደር በየነ ዱሬሳ እንደገለፁት ህዳር 3 ቀን 2014 ዓ.ም ህብረተሰቡ የሰጠውን ጥቆማ መነሻ በማድረግ ፖሊስ በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ለብርበራ በሄደበት ወቅት ግለሰቡ በፍተሻ እንዳይገኝበት በማሰብ 37 ሺሕ የአሜሪካ ዶላር፣ 52 ሺሕ ብር እና የተለያዩ ሀገራት ገንዘቦችን በፌስታል ጠቅልሎ ግቢው ውስጥ ደብቆ ተገኝቶበታል፡፡

በየካ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የኮተቤ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የከተማችንን ሰላም ለማስጠበቅ እየተሰሩ እና የአሸባሪውን ህወሃት ሀገር የማፍረስ እንቅስቃሴ ለማክሸፍ እየተከናወኑ ካሉ ተግባራት ጋር በተያያዘ ከ2ሺህ በላይ የክላሽን-ኮቭ ጥይት፣ 2 ክላሽንኮቭ ጠብመንጃ፣ 4 ሽጉጥ፣ 2 የጦር ሜዳ መነፅር፣ የእጅ መገናኛ ሬዲዮ ፣ ማህተሞችን እና ሲም ካርዶችን ህብረተሰቡ በሚሰጠው ጥቆማ እንዲሁም በብርበራ እና ፍተሻ መያዝ እንደቻለ የጣቢያው ሀላፊ ኮማንደር በየነ ዱሬሳ ገልፀዋል።

ሀገርን ለማዳን የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተግባራዊ በማድረግ የፖሊስ አመራር እና አባላቱ ከሕዝብ ጋር በመተባበር ሌት ተቀን ያለ እረፍት ጠንካራ የህግ ማስከበር ስራ መስራት በመቻላቸው ጥሩ ውጤቶች ሊገኙ ችለዋል ብለዋል፡፡

ኮማንደሩ አያይዘውም ሕዝቡ በሀሰት መረጃ ሳይዘናጋና ሳይሸበር የአጥፊዎችን ሃገር የማፍረስ ዓላማ ተገንዝቦ በሀገሩ ላይ የተቃጣውን አደጋ በጠንካራ አንድነት ሊመክት እና ሰርጎ ገቦችን በመከታተል ለፖሊስ አስፈላጊውን መረጃ እና ጥቆማ እየሰጠ አካባቢውን በመጠበቅ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሀላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባ አሳስበዋል።ዘጋቢ :-ምክትል ሳጅን አምሣሉ መብራቴ

Exit mobile version