Site icon ETHIO12.COM

ከደባርቅ ወደ ጎንደር ተጭኖ ሊወጣ የነበረ የጦር መሳሪያና ተተኳሽ ጥይት ተያዘ

ከ7 ሺህ በላይ ተተኳሽ የብሬንና የክላሽ ጥይት፣ ልዩ ልዩ የባንክ የሂሳብ ደብተሮች፣ ሲም ካርዶች፣ በደባርቅ ከተማ ተይዟል፡፡በአዲስ አበባ በአንድ ግለሰብ የሸቀጣ ሸቀጥ መደብር ውስጥ ተቀጣጣይ ቁሳቁሶችና ኬሚካሎች ተያዙ

የብሄራዊ መረጃና ደህንነት ከሃገር መከላከያ ሰራዊት ጋር ባደረገዉ የተጠናከረ ክትትል መሳሪያዎቹ መያዛቸውተጠቁሟል ፡፡

በጎንደር ከተማ የቀበሌ 15 ነዋሪ ፍጹም ገብረ ክርስቶስ በሰሌዳ ቁጥር 03 አማ – 25162 በሆነ ሚስቱቡሽ ፒክ አፕ መኪና ለጸጥታ አካላት የትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጠሁ ነዉ በማለት በተከዜ ግንባር ከሳምንት በላይ ሲንቀሳቀስ ቆይቷል፡፡

ግለሰቡ ወደ ዛሪማ በሚመላለስበት ወቅት የወገንን ሃይል አሰላለፍና የከባድ መሳሪያዎችን አቀማመጥ ለጠላት መረጃ አሳልፎ ሲሰጥ የቆየ እንደነበርና አሁንም ከመኪናዋ ሞደፊክ ባሰራዉ የህገ ወጥ እቃዎች መጫኛ ተተኳሾችን ከዛሪማና ከደባርቅ በመሰብሰብ ወደ ጎንደር በመዉሰድ ለቅማንት ጽንፈኛ ቡድን ለማቀበል ስምምነት እንደነበረዉ ተናግሯል፡፡

በአዲስ አበባ በአንድ ግለሰብ የሸቀጣ ሸቀጥ መደብር ውስጥ ተቀጣጣይ ቁሳቁሶችና ኬሚካሎች ተያዙ

በአዲስ አበባ በአንድ ግለሰብ የሸቀጣ ሸቀጥ መደብር ውስጥ ተቀጣጣይ ቁሳቁሶችና ኬሚካሎች መያዛቸውን የከተማዋ ፖሊስ ኮሚሽን ገለጸ።

የአዲስ አበባ ፖሊሰ ኮሚሽን በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ ተቀጣጣይ ቁሳቁሶችና ኬሚካሎችን ሸቀጣ ሸቀጦችን እንደሽፋን ተጠቅሞ በመደብሩ ውስጥ ደብቆ የተገኘው በአሁኑ ወቅት ነዋሪነቱን በሳውዲ አረቢያ ያደረገ አቶ መሀመድ ሀሰን የተባለ ግለሰብ ነው።

ግለሰቡ ከመንግስት ለውጡ በፊት ለሽብርተኛው ህወሃት በርካታ ገንዘብ በመላክ ከቡድኑ አመራሮች ጋር የጥቅም ትስስር በመፍጠር “ተቀጣጣይ ቁሶችና ኬሚካሎችን ችርቻሮ ንግድ” በሚል ፍቃድ አውጥቶ ሲንቀሳቀስ እንደነበር ፖሊስ አስታውቋል።

ግለሰቡ ይሄንን የንግድ ፈቃድ ከመንግስትለውጡ በኋላ “የሸቀጣ ሸቀጥ ችርቻሮ ንግድ” በሚል ቀይሮ ሲንቀሳቀስ የቆየ መሆኑን አመልክቷል፡፡

የደህንነትና ፀጥታ አካላት ጉዳዩን በጋር ሲከታተሉ ከቆዩ በኋላ የግለሰቡ የሸቀጣ ሸቀጥ ችርቻሮ ንግድ መደብር በሚገኝበት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ቀጣና 5 አካባቢ በተደረገ ፍተሻ በርካታ ተቀጣጣይ ቁሳቁሶችና ኬሚካሎችን መገኘታቸውን ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

በተያያዘ በአንድ ግለሰብ ባንክ ደብተር ውስጥ ከነበረ 40 ሚሊዮን ብር 13 ሚሊዮን ብር በማጭበርበር አውጥተው ሲያዘዋውሩ የነበሩ ተጠርጣሪ ግለሰቦችም መያዛቸውን የፖሊስ ኮሚሽን በአስታውቋል፡፡

ግርማይ ንጉሴ ተክላይ እና ያዘው ክበበው ወርዶፋ የተባሉ ተጠርጣሪ ግለሰቦች ገዛኢ አድሃኖም በእጣ በተባለ ግለሰብ ስም በተከፈተ የቁጠባ ሂሳብ ደብተር ውስጥ ከተቀመጠ 40 ሚሊዮን ብር መቀሌ የወጣ መንጃ ፍቃድ ይዘው ጎላጎል አካባቢ ከሚገኘው አንበሳ ኢንርናሽናል ባንክ በመቅረብ 13 ሚሊዮን ብር አውጥተው እዚያው ባንኩ ውስጥ በግርማይ ንጉሴ ተክላይ ስም በተከፈተ የባንክ ደብተር በማዘዋወር ላይ እያሉ እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡

እጅ ከፍንጅ ከተያዙት ተጠርጣሪ ግለሰቦቹ ጋርም የአንበሳ እና የአቢሲኒያ ባንክ ያልተፃፈባቸው ቼኮች፣ ልዩ ልዩ የባንክ ደብተሮች፣ ሶስት ኤቲ ኤሞች በኤግዚቢትነት መያዛቸውን ፖሊስ ኮሚሽኑ ይፋ አድርጓል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በአሁኑ ወቅት በርካታ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር እያዋለና ሴራቸውን እያከሸፈ ያለው ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ጋር በመቀናጀት መሆኑን የከተማዋ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ዘገባ ያመለክታል።

EPD

Exit mobile version