Site icon ETHIO12.COM

የህወሓት የሽብር ቡድን በአዲስ አበባና በዙሪያው ለሽብር ተግባር ያሰማራቸው ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የህወሓት የሽብር ቡድን በአዲስ አበባ እና በዙሪያው ለሽብር ተግባር ያሰማራቸው ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አስታወቀ።

በከተሞች በህብረተሰቡ ውስጥ በተለያዩ መንገዶች በመመሳሰል እንዲገቡ በማድረግ አዲስ አበባ እና በዙሪያው ተልእኮ ሰጥቶ በማስገባት ለሽብር ተግባር እየተንቀሳቀሱ መሆኑን እንደተደረሰበት የፌዴራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር መላኩ ፈንታ ገልጸዋል።

የሽብር ቡድን አባላቱን በንግድ ተቋማት፣ በመንግስት መስሪያ ቤቶች እና በሌሎችም የሙያ ስራዎች ህብረተሰቡ ውስጥ ተሰግስገው እንዲገቡ በማድረግ አዲስ አበባን እና አካባቢውን ለማተራመስ አቅዶ እየሰሩ መሆኑ ተደርሶበት እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።

በዚህም ቡድኑ ለሽብር ተልእኮ ያሰማራቸው በርካታ ግለሰቦች በርካታ ተተኳሽ ጥይቶች ከነፍስ ወከፍ እና የቡድን የጦር መሳሪያ ማለትም ቦንቦች ተቀጣጣይ ፈንጂዎች እንዲሁም የሀገር ውስጥና የውጭ ገንዘቦችን ይዘው በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም አብራርተዋል።

የተለያዩ የክልል እና የፌዴራል የፀጥታ መዋቅራት አልባሳትን ከነአርማው በማልበስና የተለያዩ የጦር ሜዳ ንድፍ መነፅር እና ሌሎችንም ቁሳቁሶችን በመጠቀም አሳሳስቶ ለመልበስ መሞከሩን ፖሊስ ባደረገው ፍተሻ ማገኘቱን ገልጸዋል።

ሀሰተኛ መታወቂያ ለማዘጋጀት የሚያገለግሉ ማህተሞችንና ቁሳቁሶችም ተይዘዋል ተብሏል።

ይሄንን ሃይል መንጥሮ ማውጣቱ የፀጥታ ግብረ ኃይሉ ዋነኛ ተግባር ቢሆንም የከህብረተሰቡ ድጋፍ አሁንም ከተጀመረው በላይ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ማለታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።

ህብረተሰቡ ፀጉረ ልውጠችን ሲያይ በመጠቆም የያዘውን መታወቂያ ትክክለኛነት ማጣራትም አለበት በማለት ምክትል ኮሚሽነር መላኩ ፈንታ አክለዋል።

(ኢ ፕ ድ)

Exit mobile version