Site icon ETHIO12.COM

“ከሃጂ” የተባሉ የትህነግ ጀነራሎችና ኮሎኔሎች ከነጠባቂያቸው ተመቱ፤ የተበተነው የትህነግ ሰራዊት እጁን እንዲሰጥ ታዘዘ

ዛሬ የ1997 ምርጫ ወቅት “የህዝብ ድምጽ ተዘርፏል” በሚል ህዝብ አድማ በመታበት ወቅት አድማውን ያከሸፉት አምብሳደር ቪክ ኤዲልሰን፣ የአውሮፓ ሕዝብረት አምባሳደር ቲም ክላርክ፣ የዛሬ የሶማሌ አምባሳደር ዶናልድ ያማማቶ፣ ዶክተር ኢሌኒ ገብረመድህን፣ አምባሳደር በቀለ ገለታ፣ ዶክተር ታደሰ ውሂብ፣ ኮለኒ ጃለታ፣ ወዘተ በቅንጅት ወቅት የአገር ሽማግሌ ሰብሳቢ በነበሩት ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሃቅ ሰብሳቢነት የትህነግ የአሜሪካ ወኪል በሆኑት አምባሳደር ብርሃነ ገብረ ክርስቶስ ትህነግ ስለሚመሰርተው አዲሱ የሽግግር መንግስት የተደረገ የሚስጢር ስብሰባ ይፋ በሆነበት ዕለት ነው መንግስት ታላቅ ዜና ያሰማው።

ብርሃነ ገብረክርስቶስ “ኢትዮጵያ መከላከያ የላትም ያላት ሚሊሻ ነው። ያለ ምንም ማጋነን … ” እያሉ ማብራሪያ የሚሰጡበትና ትሀንግ እንዴት ወደ አመራር እንደሚመለስ የመከሩበት ፊልም በጄፍ ፒርስ Jeff Pearce ተጠልፎ አደባባይ በሆነበትና እንደ ዶክተር ኢሌኒ ገብረመድህን አይነት ሰዎች መንግስትን ለመገልበጥ ሲመክሩ በሚሰማበት ቀን ነው ዶክተር ለገሰ ቱሉ ” አስራ ሁለት ጀነራሎችና ኮሎኔሎች ተደምስሰዋል። ተዋጊው ሃይልም ተበትኗል። የኢትዮጵያ ሃይሎች የተበተነውንና እየሮጠ ያለውን ሃይል እያጸዱ ነው” ሲሉ ያስታወቁት።

አዲስ አበባን ለመያዝ ተቃርቧል፣ ከአዲስ አበባ አርባ ኪሎሜትር ርቀት ላይ ይገኛል ሲባልለት የነበረውን ሰራዊት ሲመሩ የነበሩ ጀነራሎችና ኮሎኔሎች በተቀናጀና በቴክኖሎጂ በተደገፈ ዘመቻ እንደተመቱ መንግስት ሲያስታውቅ ዜናው ከፍተኛ ድንጋጤ የፈጠረ ሲሆን መንግስት የተበተነው ሰራዊት እጅ ከመስጠት ውጭ ሌላ አማራጭ እንደሌለው አስታውቋል።

የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሃላፊ ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ የጸጥታ ኃይሉ በባቲና ከሚሴ ግንባር በወሰደው የተቀናጀ እርምጃ ነው የጠላትን ጦር ሲመሩ የነበሩ አመራሮች መደምሰሳቸውን ያመለከቱት።

“የተደመሰሱት የአሸባሪው ህወሃት ወራሪ ኃይል አመራሮች በሀገር ክህደት ወንጀል የሚፈለጉ ነበሩ” ያሉት ሚኒስትሩ ” በባቲ ግንባር በተደረገ ልዩ ኦፕሬሽን ስድስት የአርሚና የኮር ከፍተኛ አመራሮች ተደምስሰዋል” ብለዋል።

በአንፃሩ ጠላት ሕዝብን በከፍተኛ ደረጃ ወደ ጦርነቱ በመማገድ ሕዝብን ጨራሽ ስትራቴጂን መከተሉን በማመልከት ባለፉት ሁለት ቀናት በባቲ ግንባር በተደረገ የሁለት ቀን ጦርነት አዋጊዎቹ የተደመሰሱበት የትህነግ ወራሪ ሃይል ከመደምሰስ ያመለጠው ” እግሬ አውጪኝ” በሚል ተበትኖ መፈርጠጡን አመልክተዋል። ይህ ሃይል ሊያገግም በማይቻልበት መልኩ የተመታ በመሆኑ በተበተነበት ዘረፋና ንብረት ማውደም ላይ እንዳይሰማራ ሕዝብ ተደራጅቶ እንዲከላከል መንግስት ጥብቅ ጥሪ ማቅረቡን ሚኒስትሩ አመልክተዋል። የኢትዮጵያ የተቀናጁ ሃይሎችም እግር በግር በመከታተል የማጽዳት ስራ እየሰሩ መሆኑንን አስታውቀዋል።

በተመሳሳይ በከሚሴ ግንባር በተለያየ ቦታ በተደረገ ልዩ ኦፕሬሽን የግንባሩን የጠላት ጦር ሲመሩ የነበሩ ሌሎች ስድስት “ከሐዲ” የተባሉ ከፍተኛ የጦር አመራሮች ከነጠባቂዎቻቸው መደምሰሳቸውን የኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ሃላፊ ሚኒስትር አመልክተዋል።

የቪዲዮውን ሙሉ ሪፖርት እናቀርባለን።


Exit mobile version