ETHIO12.COM

አብይ አሕመድ ድል አበሰሩ ” በርካታ ድል አለ፤ በርቱ”

ዛሬ የተለየ ቀን ነው። በደብረ ብርሃን በኩል ከተበተነ ሰርጎ ገብና፣ መውጫ ካጣና በየገጠሩ እየተለቀመ ካለ ትርፍራፊ ሃይል ሌላ ውጊያው ወደ 360 ኪሎሜትር እርቆ ኮምቦልቻ አፋፍ ዘልቋል። ይህ በተሰማበት ቅጽበት ነው የኢትዮጵያ ጦር ሃይሎች አዛዥ አብይ አሕመድ ድምጻቸውን በድል ያሰሙት። ” በአንድ ቀን ጦርነት ካሳጊታን ያዝን። ዛሬ ጭፍራና ቡርቃን እንቆጣጠራለን። ሞተን ኢትዮጵያን ማቆየት ብቻ ነው ዓላማችን…” ሲሉ ደምን በስሜት የሚያግል፣ ቁጭት በመላ ሰውነት እንደ ንዝረት እንዲነሳ የሚያደረግ፣ እልህ እንደነበልባል ግሞ እንዲወጣ የሚያስችል መልዕክት ከግንባር ያስተላለፉት።

“እዘምታለሁ” ሲሉ የአገር ወዳድ ዜጎችንና የመላው መለዮ ለባሽ ጀግኖችን ሃይል እንደ ነዳጅ ያቀጣጠሉት አብይ አህመድ በዛው መጠን ለአጉል ፕሮፓጋንዳ ሚሳይል ሊያዘንቡ ሲዘጋጁ የነበሩትን ሁሉ አምክነዋቸዋል። በአፋር ግንባር ጭፍራና ቡርቃን በዛሬው ዕለት እንደሚይዝ ያስታወቁት ፍልቅልቁ የኢትዮጵያ መሪ፣ ። ካሳጊታን በጃቸው እየሳዩ፣ በዱካቸው ቆመዋባት፣ በነበልባል ጀግኖች ታጅበው ” በአንድ ቀን ጦርነት ይዘናታል” ሲሉ በሰበት ዋዜማ በሃሰት ፕሮፓጋንዳ ስጋት የገባው የኢትዮጵያ ህዝብ አምላኩን እንዲያመሰግን፣ ቀና ብሎ እንዲተነፍስና አገሩን ለመጠበቅ ያለውን ቁርጠኛነት እንዲያጎላ የሚያደርግ ታላቅ ዜና አሰራጭተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ “የምንፈልገው እኛ ሞተን የምትቆይ ኢትዮጵያን ማየት ነው። የምንፈልገው ወይም ኢትዮጵያዊ መሆን ነው፤ ወይም ኢትዮጵያ መሆን ነው። ይሄን ደግሞ በድል እንደምናሳካ እርግጠኛ ነን” ብለዋል። በዚህ ልብን በሚሞላ መልዕክታቸው ሕዝብ ከዳር እስከዳር ደስታውን እየገለጸላቸው ሲሆን ” ጠፍተዋል፣ ተሸሽገዋል፣ ፎቷቸውን አሳዩን …” እየሉ የሃሰት መረጃ ሲያስተላለፉ ለነበሩ ቅጥረኛ ተከፋይ ሚዲያዎች፣ ተናበው ከነጭ የትህነግ አባላት ጋር ከሚሰሩ ጋር አጋር ለሆኑ “ኢትዮጵያዊ ተንታኝኞችና” የመርዝ ፖለቲካን በከርሳቸው እየለኩ በቋንቋችን ለሚግቱን ባንዳዎች መልስ ሰጥተዋል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ከጎናቸው በመሆኑን አክብሮት ሰጥተው ” በርቱ” ሲሉ ይህ አገር ሊበትን የተነሳ ተላላኪ ሃይል በቀርቡ እንደሚያበቃለት አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ አብይ አሕመድ ወደ ግንባር ለመዝመትና ወራሪውን ሃይል ለመፋለም መወሰናቸውን አስታውቀው ወደ ግንባር ካቀኑ በሁዋላ በቴሌቪዥንየታዩት ዛሬ ነው። በሚታወቁበት ፈገግታቸው ፉከራና ነገር ሳያበዙ ያስተላለፉትን መልዕክት የድል ዜና ተከትሎ ሕዝብ በከፍተኛ ደረጃ መደሰቱን ተባባሪ ዘጋቢያችን አመልክቷል።

ኮምቦልቻ ጫፍ ላይ የደረሰው ሃይል የድል ዜና በደጅ ላይ እንደሚገኝ፣ ይሁንና መንግስት ባስተአለፈው ውሳኔ መሰረት አግባብ ባለው አካል እስኪገለጽ መጠበቅ ግድ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።

Exit mobile version