ዛሬ በተከበረው 119 የአገር መከላከያ ሰራዊት ቀን ላይ “ወረን አናውቅም፣ ወደፊትም ማንንም አንወርም” ሲሉ የጦር ሃይሎች ዋና አዛዥ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ ተናገሩ። ዋና አዛዡ ይህን ያሉት ሰሞኑን ኢትዮጵያ ይፋ የባህር በር አስፈላጊነት ሳቢያ ከዚያም ከዚህም የጦርነት አሳብ እንዳለ አድርገው ለሚያስቡና ስጋት ለገባቸው ባስተላለፉት መልዕክት ነው።
መከላከያ በአዲስ መልኩ በልዩ ሪፎርም መደራጀቱን ያስታወቁት አብይ አህመድ ችግሮች በጠረጲዛ ዙሪያ ሊፈቱ እንደሚገባ አስታውቀዋል። ይህን ታላቅ ሰራዊት አዘምኖ በማደረጃቱ በኩል ሰፊ ድርሻ ላበረከቱ ታላቅ ምስጋና ያቀረቡት አብይ አህመድ ” ኢትዮጵያ ተሸንፋ አታውቅም፣ ወደፊትም አትሸነፍም። ታላቅ አገር ለልጆቻችን እናስረክባለን” ሲሉም ተሰምተዋል።
በሰራዊቱ ዘንዳ ትልቅ አክብሮትና ፍቅር እንዳላቸው የሚነገርላቸው አብይ፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አሁን ካለው በላይ እንደሚያዘምኑት ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ህዝብ ድጋፍ የማይለው የአገር መከላከያ ሃይል ኢትዮጵያን በአስተማማኝ ደረጃ እንደሚተብቅና ለማናቸውም ዓይነት ጠላት ግብረ መልስ እንዲሰጥ ተደርጎ መገንባቱን ” ሁሉም ይስማ” በሚል መልኩ ገልጸውል። ይህን ሲሉ የአገር መከላከያ ለቀጠናውና ለአፍሪካ እንደተለመደው አለኝታነቱን እንደሚያሳይ ደጋግመው ታሪክ በማጣቀስ ማስገንዘቢያ በመስጠት ነው።
በዚሁ “በተፈተነ ጊዜ ሁሉ የሚፀና የድል ሠራዊት” በሚል መሪ ሃሳብ ነው በተከበረው የአገር መከላከያ ቀን በዓል ። የጦር ኀይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዐቢይ አሕመድ መከላከያ ማለት ማንዴላን ያሠለጠነ፣ ሙጋቤን ያስደመመ፣ ከሱዳን እስከ ሊቢያ፣ ከኩባ እስከ ላይቤሪያ በመከራ ተፈትኖ በድል የጸና ሠራዊት ማለት ነው ብለዋል፡፡
ጠቅላይ አዛዡ በንግግራቸው የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሠራዊት በጦር ሜዳ ከሚያስመዘግበው ጀግንነት በላይ የኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊያን የሰላም አምባሳደር ነው ብለዋል፡፡ ሰላም አስከባሪ የኾነው ሠራዊት አጥንቱን የሚከሰክሰው ደሙንም የሚያፈሰው በሦስት መሠረታዊ ጉዳዮች ላይ ነው ያሉት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የጦር ኀይሎች ጠቅላይ አዛዥ ያለንን ሰላም ለማጽናት፣ የጠፋ ሰላምን ለመመለስ እና የመጣ ሰላምን ለማጽናት ውድ የሚባል ዋጋ ይከፍላል ብለዋል፡፡
መከላከያ ሚኒስቴር የሚከተለውን መግለጫ አሰራጭቷል።
“በተፈተነ ጊዜ ሁሉ የሚፀና የድል ሠራዊት ” በሚል መሪ ቃል ለሚከበረው ለዘንድሮ ለ116ኛው የሠራዊት ቀን እንኳን በሠላም አደረሳችሁ አደረሰን ።
እንደሚታወቀው ኢትዮጵያ የረዥም ዓመታት ሀገርን ከጠላት የመከላከል የተጋድሎ ታሪክ ካላቸው ሀገራት መካከል በጀግኖች ልጆቿ የአይበገሬነት ፊት የምትሠለፍ ታሪካዊት ሀገር ናት።
ከቀደመው ዘመን ጀምረን አሁን ላይ ያለውን እውነታ እንኳ ብንቃኝ ኢትዮጵያ በርካታ የውጪ ወራሪ ሀገራት ያሠፈሠፉባት ጥቂት የማይባሉ የውስጥ እርስ በርስ ግጭቶች የተከሰቱባት በባንዳዎች የተፈተነችበትና በየትኛውም ዘመን ያልተንበረከከች የወራሪዎችን ፈተና አልፋ ዛሬ ላይ የደረሠች ሥለመሆኗ የታሪክ ድርሳናት መዝግቧል።
በሀገራችን የጀግንነት የታሪክ መዝገብ ያልሠፈሩ ግን ደግሞ አለም ያወቃቸው ቱባ ባህሎችና ድንቅ ታሪኮች ያላት ኢትዮጵያ በታሪክ በሠራዊቷ ኮርታ እንጅ አንድም ጊዜ አፍራ እንደማታውቅ ታሪክ ህያው ምስክር ነው ።
ዛሬ ላይም በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች ሀገረ ጠል በሆኑ ባንዳዎችና የፀረ ሠላም ሀይሎች ችግሮች ቢከሠቱም ጀግንነት ባህል ልምዱ እና የዘወትር ተግባሩ ባደረገው ሠራዊታችንና ህዝባችን የሠላም እንቅፋቶችን ፈተና ተቋቁማ ሀገራችን በልማት ጎዳና ላይ ትገኛለች።
በመሆኑም በየትኛውም ጊዜ እና በማንኛውም ቦታ ለሠራዊታችን ብርታት ሞራልና የጀርባ አጥንት ከሆነው ህዝባችን ጋር ሆነን ሠላማችንን እያሥቀጠልን እንገኛለን።
116ኛው የመከላከያ ሠራዊት ቀንም ይበልጥ ቃላችንን የምናደስበት በየዘመናቱ ለሀገራችን ሉዓላዊነት ሲሉ መስዋዕት የከፈሉ ጀግኖችን የምንዘክርበትና ከመላው ህዝባችን ጋር ሆነን ለሀገራችን ሠላምና ልማት ማበብ በጋራ የምንቆምበት ዕለት ጭምር ነው።
እናም እንደ መሪ ቃላችን በተፈተን ጊዜ ሁሉ ፀንተን የድል ሠራዊት ሆነን ዛሬ ላይ እንደደረሥነው ቀጣይም ከመላው ህዝባችን ጋር ለሀገራችን መክፈል ያለብንን ሁሉ ዋጋ በመክፈል የኢትዮጵያን ሠላም እና ዕድገት አፅንተን እናሥቀጥላለን ።
“በተፈተነ ጊዜ ሁሉ የሚፀና የድል ሠራዊት”
ጥቅምት 15 ቀን 2016 ዓ.ም
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
- ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያና የደኅንነት ስጋት – አቅራቢ፣ ፈላጊ፣ ነጋዴ፣ ደላላ ተገናኙና መደበኛ ገበያ ሆነ!በፖለቲካም ሆነ በአካባቢያዊ አጀንዳ ነፍጥ ያነገቡ እና ጦርነትን አማራጭ አድርገው የሚንቀሳቀሱ ኢ -መደበኛ አደረጃጀቶች ሁሉ የጦር መሳሪያ ፍላጎት ይኖራቸዋል፡፡ የጦር መሳሪያ… Read more: ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያና የደኅንነት ስጋት – አቅራቢ፣ ፈላጊ፣ ነጋዴ፣ ደላላ ተገናኙና መደበኛ ገበያ ሆነ!
- ምን ያክል ተዘጋጅተናል? ጥድፊያ አገር አልባ ለመሆን !! ህጻናቱ ምን አጠፉ?ያለፈውን ግማሽ ምዕተ ዓመት የኢትዮጵያ ፖለቲካ እና ሥነ መንግሥት ታሪክ በጥሞና የተከታተለ ኢትዮጵያዊ የግዛት አንድነቷን እና የፖለቲካ ነጻነቷን በአንጻሩ ጠብቃ የኖረች… Read more: ምን ያክል ተዘጋጅተናል? ጥድፊያ አገር አልባ ለመሆን !! ህጻናቱ ምን አጠፉ?
- የደም ግፊት በመለካትና ክትትል በማድረግ የስትሮክ ተጋላጭነትን መቀነስአንድ ሰው የደም ግፊት መጠኑ ከፍተኛ ከሆነ እና በጊዜው ሕክምና ካላደረገ ለከፍተኛ የልብ በሽታና በደም ዝውውር ማነስ ምክንያት ለሚከሰት የአዕምሮ ሥራ… Read more: የደም ግፊት በመለካትና ክትትል በማድረግ የስትሮክ ተጋላጭነትን መቀነስ
- የስኳር ህመም አይነቶች እና ምልክቶችየስኳር ህመም በደም ውስጥ የስኳር መጠን ከሚገባው በላይ ሆኖ በሚገኝበት ሰዓት የሚከሰት ተላላፊ ያልሆነ የህመም አይነት ነው። በዋናነት አራት የስኳር ህመም… Read more: የስኳር ህመም አይነቶች እና ምልክቶች
- ማንኮራፋትና ትዳርን እስከ ማፍረስ የሚያደርሰው መዘዙ ? ማንኮራፋት መፍትሄ አለው?የማንኮራፍት መዘዙ እንቅልፍ ማሳጣት ብቻ አይደለም። ማንኮራፋት ከሚያንኮራፉት ሰዎች ጎን በሚተኙ ሰዎች አካላዊ እና አእምሮ ጤና ላይ ጉዳት ያስከትላል። ትዳርንም ሊያፈርስ… Read more: ማንኮራፋትና ትዳርን እስከ ማፍረስ የሚያደርሰው መዘዙ ? ማንኮራፋት መፍትሄ አለው?