Site icon ETHIO12.COM

ከተከዜ ግድብ “ተመቷል” ዜና ጀርባ ያለው ደባ !

“የተከዜ የኃይል ማመንጫ ጣቢያ ግድብ ተመቷል” ከሚለው ዜና ጀርባ እጅግ አስደንጋጭ ደባ መኖሩና ዕቅዱ ከተሳካ ጥፋት ሊያስከትል እንደሚችል ተመለከተ። የሃሰት ዜናውን ማሰራጨት የተፈልገውም ሁን ተብሎ ለክፋት ሃሳብ ማራመጃ መሆኑ ተዘገበ። ሕዝብ ጥንቃቄ እንዲያደረግ እየተሰራ መሆኑ ተሰምቷል።

“የተከዜ የውሃ ኃይል ማመንጫ ግድብ በመንግስት ተመቷል” ሲሉ የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር / ትህነግ አፈ ቀላጤ አቶ ጌታቸው ረዳ ናቸው ያስታወቁት። ይህንኑ ዜና የሽብርተኛው የህወኃት ቡድንና በአቀንቃኞቹ እንዳናፈሱት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል በማህበራዊ ገጹ አመልክቷል። ከዚህ ቀደምም “ግድቡ ተመቷል” በሚል በጥፋት ቡድኑ ተመሳሳይ የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ተሰራጭቶ እንደነበር ያስታወሰው ተቋሙ “በመንግስት የተመታው የተከዜ ግድብ ሳይሆን ተከዜን ተሻግሮ ወረራ የፈፀመው የሽብር ቡድኑ ነው” ብሏል።

“የተከዜ ግድብ ባለፈው ክረምት ስለሞላ ውሃውን እንዲፈስ በማድረግ የሀሰት ፕሮፓጋንዳውን እውነት ለማስመሰል ጥረት ሊያደርግ እንደሚጥር ይገመታል” ሲል ያስታወቀው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል፣ “የኃይል ማመንጫ ጣቢያው ሙያተኛ ባልሆኑ ሰዎች፣ ከታለመለት ዓላማ ውጪ እንዲሰራ ከተደረገ ከፍተኛ መጠን ያለው ጉዳት ሊደርስበት እንደሚችል ይታመናል” ብሏል። ተቋሙ ባለሙያዎች መድቦ እንደተገደሉበትና ዳግም የሰው ሃይል ለማሰማራት እንደማይችል ማስታወቁ አይዘነጋም።

ግምቱን ከትነተና ጋር አስለቶ እንዳስቀመጠው ትህነግ ሆን ብሎ የያዘውን ውሃ በመልቀቅ ሰብአዊና ቁሳዊ ጉዳት የማድረስ ወንጀል ሊፈጽም እንደሚችል አስጠንቅቋል። ምንም ነገር ከማድረግ ወደሁዋላ የማይለው ትህነግ ” አማራ ላይ ሂሳብ ለማወራረድ ሲኦልም ቢሆን እወርዳለሁ” ማለቱን የሚያስታውሱ አሁን ላይ ቡድኑ በሽንፈት አፋፍ ላይ ስለሚገኝ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል የሰጠውን ማሳሰቢያ በቀላሉ እንደማያዩት፣ ካድረገውና የተፈራው ቀውስ ከደረሰ ጉዳዩ ሁሉ “በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ይሆናል” ሲሉ በቃላት ሊገለጽ የማይችል የበቀል ስሜት እንደሚወልድ አሳስበዋል። የትግራይ ተወላጆች ይህን አሳብ አሁንም ለመቃወም ጊዜው እንዳልመሸ መክረዋል።

“… የሽብር ቡድኑ ህዝብን ለማሸበርና ዓለም አቀፍ ትኩረት ለመሳብ ውሃውን ሊለቅ ስለሚችል በግድቡ የታችኛው ተፋሰስ አካባቢ በተለይም በጣንቋ አበርገሌ፣ በጠለምት፣ በቃፍታ ሁመራ፣ በጠገዴ፣ በአበርገሌና በወልቃይት አካባቢዎች የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ይህ መረጃ የደረሳችሁ የህብረተሰብ ክፍሎች መልዕክቱን በማስተላለፍ ትብብር እንድታደርጉ ጥሪያችንን እናቀርባለን” ሲል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል አስታውቋል። አደራውንም አኑሯል።

የተከዜ የውሃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ሙሉ በሙሉ በሽብርተኛ ቡድኑ ቁጥጥር ስር ከመዋሉ በፊት በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ መለዋወጫ ተሟልቶለትና ከሁለት መቶ በርሜል በላይ የተርባይን ዘይት አቅርቦት ቀርቦለት በጥሩ ሁኔታ አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደነበር ተቋሙ በመልዕክቱ መጨረሻ ላይ አስፍሯል።

አቶ ጌታቸው ” በመሞት ላይ ያለ” የሚሉትና ” ላንቃቸውን በሃይል እናዘጋቸዋለን” በሚል በተደጋጋሚ የሚያንጠለጥሉት የኢትዮጵያ መንግስት ሃይሎች በጥምር ባካሄዱት የአጭር ቀን የማጥቃት ጦርነት በርካታ ስፍራዎችን ስለመቆጣጠራቸው፣ በተለይም ጭፍራና ዳንሻን ስለመነጠቃቸው የዓለም መገናኛዎች ሲዘግቡ ያሉት ነገር የለም። ቀደም ሲል በሳተላይት ስልክ የሚያገኙዋቸው አንዳንድ ሚዲያዎች “ልናገኛቸው አልቻልንም” የሚል ሃረግ በሪፖርታቸው እያካተቱም ቢሆን ግድቡ መመታቱንና ውሃ መፍሰሱን አልገለጹም።

ዛሬ በስዳተላይት መረጃ ነገሮችን መደበቅ እንደማይቻል በርካታ መረጃዎች ይፋ መሆናቸው ምስክር እንደሆነ የገለጹ ክፍሎች ” አቶ ጌታቸው ተከዜ ተመታ” ካሉበት ሰዓት ጀምሮ እውነት መሆኑንን የሚያረጋግጥ ዜና አልወጣም። አቶ ጌታቸው ስለ ተከዜ ሃይል ማመንጫ መመታት ከመግለጻቸው ቀናት በፊት የፋኖስ ምልክት የያዙ እናት ምስል የቲውተር ገጻቸው መለያ አድርገው ነበር።

አቶ ጌታቸው ተከዜ መመታቱን ከማስታወቃቸው ቀደም ብሎ ቆየት ያለ ምስል በማሰባሰብ ” ለአዲስ የማጥቃት ስትራቴጂ እየተዘጋጀን ነው” ሲሉ የትህነግ የጦር አዝማቾችና መሪዎች ካርታ ሲያነቡ አሳይተው ነበር። በዚሁ መረጃቸው መሰረት የትህነግ ሃይል መቼ፣ በየትና በኩልና እንዴት ያለ ማጥቃት እንደሚጀምር እስካሁን የተሰማ ነገር የለም። ይልቁኑም መንግስት ” አክትሟል እጅ ስጡ” የሚል ጥሪ ያቀረበ ሲሆን፣ ወደ አዲስ አበባ እየገሰገሰ እንደሆነ የተነገረለት ሃይል እየተገፋ ሸዋ ሮቢት መድረሱና ወራሪው ሰራዊት በየጥሻው በመሸገ ሕዝብ፣ ሚሊሻ፣ የአምራ ልዩ ሃይል፣ የመከላከያ ሰራዊት በየአቅጣጫው ጥቃት እየተዘነዘረበት ከወዲያ ወዲህ ሲሯሯጡ የሚያሳይ መረጃ ይፋ እየሆነ ነው።

ትህነግ በድብረታቦር ወደ ባህር ዳር፣ በሚሌ ወደ አዋሽና ጅቡቲ መስመር፣ በማይጽብሪ ግንባር የሱዳን ኮሪዶርን ለማስከፈት ሰፊ ጥቃት ፈጽሞና ዘልቆ የገባ ቢሆንም እንዳልተሳካለት ያታወሳል። በመጨረሻ በወሎ ግንባር አዲስ አበባ ሊገባ እንደነበር የተገለጸለት ቢሆንም ፌልትስማን ሳይቀር በይፋ እንደተናገሩት አልሆነለትም።

Exit mobile version