Site icon ETHIO12.COM

” የጦር አውሮፕላኖቹ የሩሲያን ድንበር ከመጣስ ተገትተዋል ” ሩሲያ

በጥቁር ባህር በኩል #የሩሲያን ድንበር አቋርጠው ሊገቡ የነበሩ የፈረንሳይ እና የአሜሪካ የጦር አውሮፕላኖች በSU-27 የሩሲያ ጄቶች ተጠልፈው መመለሳቸውን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

እኤአ ታህሳስ 9 የሩሲያ የኤሮስፔስ መቆጣጠሪያ ሲስተም በራሪ አካላት ጥቁር ባህርን አልፈው ወደ ሩሲያ ድንበር እየበረሩ እንደሆነ ማመላከታቸውን ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ ተጠቅሷል።

የሩሲያ ኤርክራፍት በረራ ቡድን ወደሩሲያ ድንበር አቅጣጫ ሲበሩ የነበሩት Mirage-2000 ጀትና ከፈረንሳይ አየርና ስፔስ ሃይል የመጣች የፈረንሳይ Rafale ጄት እንዲሁም የአሜሪካ ጦር CL-600 ያሳተፈ የጥናት እንቅስቃሴ ነበር ተብሏል፡፡

የፈረንሳይ KC-135 አውሮፕላን ነዳጅ የምትሞላ እና እጀባ የምታደርግ በጥቁር ባህር ላይ ሲበሩ እንደነበር መግለጫ አመልክቷል፡፡

የጦር ጄቶች አማካኝነት የጦር አውሮፕኖቹ የሩሲያን ድንበር ከመጣስ ተገትተዋል ያለው መግልጫ የሩሲያ ውጊያ ጄቶች የጦር አውፕላኖቹን ከድንበር ወደ ኋላ ከመለሱ በኋላ በሰላም መመለሳቸው ተገልጿል።

መረጃው የአል ዓይን ኒውስ ነው።

ቪድዮ : የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር

Exit mobile version