Site icon ETHIO12.COM

በአሜሪካ ታሪክ የከፋ የተባለ አውሎንፋስ ሰው ጨረሰ፣ ከተሞች አወደመ

በበኬንታኪ ከሻማ ፋብሪካው ፍርስራሽ ስር ከነበሩት 110 ሰዎች መካከል ከ40 በላይ ሰዎች ማትረፍ ተችሏል። ሌላ ተጨማሪ የሰው ህይወት ማትረፍ ስለማቻሉ ተጠይቀው የኬንታኪው ገዥ በሼር “ሌላ ሰው በህይወት ከተገኘ ተአምር ነው ” ሲሉ ነበር ገና ከጅምሩ ምላሽ ነው የሰጡት። ይህ በአሜሪካ ታሪክ የከፋ የተባለ አውሎ ንፋስ እስካሁን ከሰማኒያ ሰዎች በላይ ሲገል መንደሮችን አውድሟል።

ይህ አምስት ግዛቶችን ክፉኛ የመታው ከባድ አውሎ ንፋስ ያደረሰውን ዘግናኝ አደጋ ተከትሎ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ከአውሎ ንፋሱ አደጋ ጋር በተያያዘ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲያወጡ አስገድዷቸዋል። የተጎዱትን ግዛቶች ሙሉ በሙሉ እንደሚደግፉ ቃል ገብተዋል።

እስካሁን ከተመዘገቡት ሟቾች ውስጥ ሰባ የሚሆኑት የኬንታኪ ነዋሪዎች ናቸው። የጉዳቱ መጠን ከዚህም በላይ ሊሆን እንደሚችል የአደጋ ሰራተኞች ስጋት አላቸው። አንድ ሌሊት ይህን ያህል የአሜሪካ ክፍል ያወደመው አውሎ ነፋስ በሀገሪቱ ታሪክ ውስጥ ከተነሱ የአውሎ ንፋሶች ሁሉ ትልቁ መሆኑንን አዛውንቱ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ተናግረዋል። አክለውም የጠፉ ቤተሰቦቻቸውንና ወዳጅ ዘመዶችን ማግኘት ላልቻሉ፣ ስለ ቤሰቦቻቸውና ዘመዶቻቸው ሁኔታ እርግጠኛ መሆን ላልቻሉ በሙሉ በጸሎት እንደሚያስቧቸው ተናግረዋል።

ኢሊኖይ አውሎ ንፋሱ በቀጥታ ባያላጋትም በከባዱ ጉዳት ደርሶባታል። እዛው አማዞን ኩባንያ መጋዘን ውስጥ የነበሩ ስድስት ሰራተኞችን ጨምሮ በድምሩ አስራሁለት ሰዎች ህይወታቸው እንዳለፈ፣ ይህ አሃዝ ቁጥሩ ሊጨምር እንደሚችል ተመልክቷል። “የፌደራል መንግሥት ለመርዳት የሚቻለውን ሁሉ ያደርጋል።ይህንንን ፈታኝ ወቅት አንድ ላይ እናልፋለን” ሲሉ ፕሬዚዳንቱ ማጽናኛ ንግግር አድርገዋል።

ባይደን “የአደጋውን ተፅዕኖ ለመቀነስ የሚቻለውን ሁሉ እናደርጋለን” ብለዋል። የአየር ንብረት ለውጥ መንስኤ ሊሆን እንደሚችል ተጠይቀው ” ይህን አስመልክቶ የምለው ነገር የለም፤ ከአካባቢ ጥበቃ ኤጀንሲ ጋር እነጋገራለሁ” የሚል መልስ መስጠታቸውን ቲአርቲ ዘግቧል።


ተጨማሪ ያንብቡ

Exit mobile version