Site icon ETHIO12.COM

ጌታቸው ረዳ በትግርኛ አሜሪካ “እንደምትነዳቸው” ይፋ ማድረጋቸው ትህነግ ላይ ተቃውሞ አስነሳ -“ትህነግን አበረታትቼ አላውቅም” አሜሪካ

አቶ ጌታቸው ረዳ አሜሪካ የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባርን እንደምትነዳ በትግርኛ ማስታወቃቸውን ተከትሎ ትህነግ በውስጥም፣ በገሃድም ተቃውሞ እየተሰነዘረበት ነው። የአሜሪካ መንግስ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት “ህወሓት ወታደራዊ ዘመቻውን እንዲያስፋፋም ሆነ አዲስ አበባ እንዲገባ ዩናይትድ ስቴትስ በምንም ሁኔታ አበረታታ አታውቅም” ሲል ይፋ መግለጫ ሰጥቷል።

ትህነግ በእንግሊዝኛ፣ በአማርኛና፣ በትግርኛ በአንድ ጉዳይ ላይ የተለያየ መግለጫ እንደሚሰጥ በተደጋጋሚ የሚገለጽ ጉዳይ ቢሆንም የአሁኑ ግን በዝምታ የሚታለፍ አልሆነም።

“አማሪካ ሌሎችን አካታችሁ ወደ አዲስ አበባ ግቡ” በሚል ድጋፍ እንደምታደርግ አቶ ጌታቸው በትግርኛ እንደተናገሩ ዜናው ተተርጉሞ በንግሊዝኛና በአማርኛ ተቆርቋሪ ኢትዮጵያዊያኖች አሰራጭተውት ነበር። የመንግስት ሚዲያዎችም ዘግበውት ነበር። ዜና በከፍተኛ ደረጃ መራባቱን ተከትሎ ማርቲን ፕላውት “የአቶ ጌታቸው ንግግር ትርጉም ሲል” ትግርኛ የሚያውቁ የዓላማ ባልደረቦቹ አሽተው የተረጎሙትን በድረ ገጻቸው አተሙ። ትህርኛውንም አያይዘው አቀረቡ። አቶ ጌታቸውም አመሰገኑና ለውጭ አገር ተከታትዮች ማጣፊያ እንዲሆንላቸው በቲውተር ገጻቸው ” ውድ ማርቲን ፕላውት አመሰግናለሁ” ብለው ለጠፉ። ነገሩ ግን በዚህ የሚቆም አልሆነም።

በጦርነቱ የትህነግ የጀርባ አጥንት እንደሆነች የሚነገርላትና በግልጽ ኢትዮጵያ ላይ ዘመቻ እያካሄደች ያለችው አሜሪካ “መንግስት ለመገልበጥ አንድ ሉዓላዊ አገር ውስጥ ቁጭ ብላ አማጺውችን እየገፋች መሆኗን የአማጺ ከፍተኛ አመራር ይፋ ማድረጉ፣ ለአሜሪካ ትርጉሙ ከባድ ነው። ነጮች ህግ ተጠቅሶ መሞገትን ስለማይወዱ እጅጉኑ ተከፍተዋል” ሲሉ ዜናው እንደተሰማ የጻፉ ነበሩ።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ማስፈጸሚያ ቁስ ከሆኑት መካከል አንዱ የሆነው የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ዛሬ ከውጭ ጉዳይ ጠይቆ እንዳገኘ በመግለጽ ” “ህወሓት ወታደራዊ ዘመቻውን እንዲያስፋፋም ሆነ አዲስ አበባ እንዲገባ ዩናይትድ ስቴትስ በምንም ሁኔታ አበረታታ አታውቅም” ሲል የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቷ አስታውቋል” ሲል ዜና አውጇል።

አቶ ጌታቸው “ንግግሬ ተሳስቶ ተተርጉሞብኛል” በሚል ሲያስተባብሉ ቢቆይም የአሜሪካ ሬዲዮ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱን ምላሽ ሲዘግብ አቶ ጌታቸው በትግርኛ የተናገሩትን እንዳለ አቅርቧል። ቃል በቃል ተርጉሞ ሲያበቃ ነው ምላሹን ያቀረበው።

አቶ ጌታቸው “የአሜሪካንን አቋም ለማወቅ ያስቸግራል።አንዳንዴ ሁላችንንም ያስፈራራሉ። ሰላም እንድናወርድ ያስገድዱናል። መልሰው ህወሃት አዲስ አበባ ቢገባ ደም መፋሰስ ይኖራል ይኖራል” ያላሉ። እንደወረደ በቀረበው የቃል በቃል ትርጉም ይናገሩና አስከትለው “በሌላ ጊዜ ደግሞ አዲስ አበባ ስትገቡ የሚፈጠረው የደም መፋሰስ መቀነስ እንዲቻል ሌሎች ፓርቲዎችን ጠርታችሁ አንድ ላይ ሁኑ ይሉናል” ሲሉ አሜሪካ እንዴት ቅንብሩን እንደምትመራው ይፋ አድርገዋል። ድጋፍ እንደምታደርግላቸው የዕምነት ቃላቸው ሰጥተዋል።

“በዚህ መልኩ የቀረበው የአሜሪካ አካሄድ፣ አቶ ጌታቸው ባይናገሩትም በፕሬስ ሃውስ ከትህነግ በቀር በውል እንኳን የማይታወቁ፣ የት እንዳሉና በስም ደረጃ ያልተሰሙ፣ ቢኖሩም ለመኖር ያህል እንጂ ይህ ነው የሚባል ነገር የሌላቸው የጎሳ ድርጅቶችን ለቃቅማ በፕሬስ ሃውስ መግለጫ እዲሰጡ ስትፈቅድ ዕውቅና ለመስጠቷና ፈቃድዋ እንዳለበት አመልክታ በሕዝብ የተመረጠ መንግስት ለመናድ እየሰራች መሆኑንን ያረጋግጣል” ሲሉ ገነት ዘውድ ሃይሌ በግል አስተአየታቸውን አስፍረዋል።

የትህንገ አፍ የሆኑት አቶ ጌታቸው እውነቱን ስላሉት ማስተባበል ግድ እንደሆነ ገነት ዘውዱ ገልጸዋል። ዛሬ የአሜሪካ ሬዲዮ አማርኛ ክፍል ከውጭ ጉዳይ ያገነውን መልስ ሲያስታውቅ እንዳለው አሜሪካ ከቶውንም ትህነግን አበረታታ አታውቅም።

የአሜሪካ አቋም በግል ደረጃም ሆነ በአደባባይ የሚናገሩት ወታደራዊ አካሄድ መፍሄ እንደማይሆን፣ ያለው ብቸና አንድ አማራጭ ዲፕሎላማሲያዊ መፍትሄ መፈለግ እንደሆነ፣ ፍላጎታቸው ትህነግ ወሮ ከያዛቸው ስፋራዎች ወጥቶ የሰብአዊ ዕርዳታ ያለገደብ እንዲለቀ እና የመሳሰሉት ጉዳዮች አቋማቸው እንደሆነ በዜናው ተመልክቷል።

ሁሉን ያሳተፈ ውይይት ወይም ንግግር ላይ ዛሬም አጽንዖ ሰትቶ የቀረበው ማስተባበያ አተኩሯል። መንግስት ገለልተኛ ኮሚሽን አዘጋጅቶ፣ ኮሚሽኑ ህጋዊ ህልውና ያለው አካል መሆኑንን ባስታወቀበትና ወደ ስራ ለመግባት ዳር መድረሱን እያስታወቀ ባለበት ወቅት አሜሪካ አሁንም ሁሉንም ያካተተ ንግግር ስትል ምን ማለቷ እንደሆነ ዜናው አላብራራም።

አውሮፓ ሕዝብረትና አሜሪካ ንግግሩ ” የሽግግር መንግስት” የሚል ዝንባሌ ያለው፣ አሳቡ በተደጋጋሚ በትህነግ የሚቀነቀን መሆኑ ሲገለጽ መቆየቱ ይታወሳል። ኢትዮጵያዊያን የመረጡትና በዚህ አስከፊ ጊዜ ሙሉ ድጋፋቸውን እያደረጉለት ያለውን መንግስት አሜሪካም ሆነ የአውሮፓ አንዳንድ መንግስታት እንዲፈርስ የሚመኙበትን አግባብ ሕዝብ እንዳልተቀበለው በርካታ ማሳያዎች አሉ። ይሁን እንጂ ” እኛ ያልነው” በሚል በተለያዩ አግባቦች ጫና እያደረጉ ይገኛሉ።

መንግስት ለተወሰኑ አገሮች ፍላጎት ሲባል ዓለም ዓቀፍ ተቋማትና ድርጅቶችን ሳይቀር በመጠቀም ኢትዮጵያ ላይ ዘመቻው የተቀነባበረ እንደሆነ በገሃድ ተደጋጋሚ ለሕዝብ ይፋ እያደረገ ያለው። ራሳቸውን ለጥቅም አሳልፈው የሰጡ ለውደፊት በታሪካና በትውልድ ተጠያቂ እንዳይሆኑ ማሳሰቢያ እየሰጠ ያለው።

የአሜሪካ ሬዲዮ “ህወሓት ወታደራዊ ዘመቻውን እንዲያስፋፋም ሆነ አዲስ አበባ እንዲገባ ዩናይትድ ስቴትስ በምንም ሁኔታ አበረታታ አታውቅም” ሲል የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቷ አስታውቋል” ሲል ያስተላለፈውን ዜና አስመልክቶ ከትህነግ ወገን የተሰማ ነገር የለም። ዜናውን ያቀረቡት ክፍሎችም ይህን አስመልክቶ ለጊዜው ያሉት ነገር የለም። ምን አልባት አቶ ጌታቸውን የትግራይ ወኪላቸው አነጋገሮ ምላሽ የሚሰጥ ከሆነ ቃላቸውን እንዴት እንደሚቀይሩ ይደመታሉ ማለት ነው።

“ህወሓት ወታደራዊ ዘመቻውን እንዲያስፋፋም ሆነ አዲስ አበባ እንዲገባ ዩናይትድ ስቴትስ በምንም ሁኔታ አበረታታ አታውቅም” ሲል የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቷ አስታውቋል” የሚለው ዜና ከመሰራጨቱ በፊት አቶ ጌታቸው አሜሪካ አዲስ አበባ እንዲገቡ ግፊት ማድረጓን ገልጸው መናጋራቸው ይፋ እንደሆነ ክፉኛ መወቀሳቸው መገለጹ አይዘነጋም።


ተጨማሪ ያንብቡ

Exit mobile version