Site icon ETHIO12.COM

በወታደራዊ ቋንቋ ጦርነቱ አልቋል – ጥያቄው ከዛስ? ሆኗል

አረፋፍደው የተሰሙ መረጃዎች እንደሚያሳዩት የኢትዮጵያ ጥምር ሃይሎች መቀለን እያሸተቱ ነው። አላማጣን ከያዙ በሁዋላ መስመር ላይ ያሉ ከተሞችን እያለፉ ወደ ኮረምና ማይጨው አቅንተዋል። በትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ በኩል የቀረበውን አስቸኳይ የተኩስ አቁም ጥያቄና የሰላም ውትወታ ጥምር ሃይሉ “አይሰማም” ያለ ይመስላል። ባለሙያዎች እንደሚሉት ጦርነቱ አልቋል። የሚጠበቀው “ከዚያስ?” የሚለው ጥያቄ መልስ እንደሆነ ከየአቅጣጫው እየተሰማ ነው።

“አማራ ላይ የማወራርደው ሂሳብ አለኝ” ብሎ በመንጋ ወረራ ያካሄደው ትህነግ በመሪዎቹ አማካይነት የኢትዮጵያን ሕገመንግስትና ዓለም ዓቀፍ የግኙነት መስመርን በመጣስ ለተባበሩት መንግስታት ያቀረበውን ደብዳቤ ” የድረሱልኝ ጩኸት” ሲል ስም ጠቅሶ የዘገበው የመንግስት ሚዲያ ለጥሪው መንግስት የሰጠውን ምላሽ አልገለጸም። ይልቁኑም የትህነግን ጥሪ “ሽንፈት የወለደው ለቅሶ ” ሲል ዋጋ ቢስ መሆኑንን ነው ያመለከተው። ያለ አቅሙና ህጋዊ ደርዙ እየተወራጨ መሆኑንንም እንግዳ ጋብዞ አስተያየት አሰጥቶበታል።

መንግስት በስምምነት ህገመንግስት እስከማሻሻል የሚደርስ የብሄራዊ እርቅ ማዘጃቱን፣ ይህንኑ ሰነድ ” ተወያዩበት” ብሎ ማደሉ ይፋ ሆኖ ሳለ ” የተለየ ሚስጦራዊ ሰነድ አገኘን” በሚል መንግስት ካሰበው ውጪ ከትህነግ ጋር ሊደራደር እንደሆነ አድርገው በተገኘው ወታደራዊ ድል ላይ ቁማር ለመጫወት ደፋ ቀና የሚሉትን ተከፋዮች አስመልክቶ ” ህዝብና መንግስት እየተናበቡ ነው” ሲሉ ከቁብ እንደምያቆጥሩት ከፍተኛ ሃላፊ ነግረውናል። ዝርዝር መረጃ በየደረጃው እንደሚሰጥም አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ጥምር ጦር ጥቃት መቋቋም አቅቶት በሽንፈት መውጣት የቻለው ወደ ትግራይ ማለጡን የሚያስረዱ ” ካሁን በሁዋላ ትህነግ የጥምር ሃይሉን ጥቃት ሊቋቋም የሚችልበት ምድራዊ አቅም የለውም” በማለት እየገለጹ ነው። አቶ ጌታቸው ረዳ የትህነግ ሰራዊት የጥምር ሃይሉን ጫና መቋቋም እንዳልቻለ ማመናቸውን ቢቢሲ አፍሪካ አመልክቷል።

“ስልታዊና ታክቲካል ማፈግፈግ አድርገናል፣ ሃይላችን ተጠቃሎ ወደ ትግራይ ገብቷል” ሲሉ የነበሩት አቶ ጌታቸው “ታክቲካል” ያሉት ማፈግፈግ እስከየት እንደሆነ እስካሁን አላስታወቁም። ይልቁኑም በድሮን ጥቃት መጎዳታቸውን እያስታወቁ ነው።

አዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ ከደጋፊዎቻቸው ጋር ሰርግና ምላሽ ለማከሄድ ቀናት እንደቀራቸው ” በጃችሁን ስጡ” ማስታወቂያ ሲሟሟቁ የነበሩት የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር መሪዎች ” ለቃቅመን እናጉራቸዋለን፣ መከላከያው አልቋል፣ የተረፈ ይህ ነው የሚባል፣ እዚህ የደርሳል ተብሎ ግምት የሚሰጠው ሰራዊት የለም…” ሲሉ የከረሙት ሃላፊዎች በድንገት ታክቲካል ማፈግፈግ ማድረጋቸው ሲሰማ ቅድሚያ የደነገጡት ደጋፊዎቻቸው ነበሩ።

ታክቲካል የተባለው ማፈግፈግ ይፋ እንደሆነ በጉምጉምታ የተቀበሉ አሁን ላይ ” ታክቲካል ማፈግፈጉ የት ድረስ ነው” በሚል እየጠየቁና እየተነጋገሩ እንደሆነ እዩእተሰማ ነው። በሁለት አገሮች ፍርስራሽ ላይ ” ታላቋን ትግራይ እንመሰርታለን” በሚል መጨበጫ የሌለው ህልም ስህተት አስቦ፣ ስህትተ አቅዶ፣ በስህተት አስልቶ፣ የስህተት ስሌት ተግብሮ፣ ሲመሽ ጉዞውን ወደ መቀለ ያደረገው ትህነግ በቀጣይ ከራሱ ታጣቂዎችና ከሕዝብ የሚደርስበትን ጫና መቋቋም እንደማይቻለውም እየተሰማ ነው።

ይህ ነው የሚባል ታሪካዊ ግጭት የሌላቸውን፣ አብረው ለዘመናት የኖሩትን ትግሬና አማራ እሳትና ጭድ በማድረግ ውስጥ ህይወት እየቀጠለ የኖረው ትህነግ ከከፍተኛ ኪሳራ በሁዋላ የሰላም ንግግር ጥሪ ማቅረቡ የሽንፈቱ ውጤት ሲሆን ” እንዴት ይታመናል” በሚል ከኖረ ባህሪው በመነሳት ዜጎች ስጋታቸውን ከወዲሁ እየገለጹ ነው።

” አፈር ልሰን የምነሳው እኛ ብቻ ነን። ይህን ደጋግመን አድርገነዋል” በማለት የሚናገሩትን አልሸነፍ ባዮች የሰሙ፣ አሁን የተሰማውን የሰላም ንግግር ተመልሶ ለመደራጀት ሊጠቀሙበት በመሆኑ መንግስት ሊጠነቀቅ እንደሚገባ እያሳሰቡ ነው። በተቃራኒው በትህነግ፣ በትህነግ ደጋፊዎች፣ በትህነግ ረዳት አገሮችና ሚዲያዎች የዕርቅ ንግግር እንዲጀመር ሰፊ ጫና ለመፍተር እየተሞከረ ነው።

ሽንፈቱን ” ኢትዮጵያ ድሮን ስላላትና ትህነግ ድሮን ስለሌለው የተፈጠረ የአቅም ችግር እንጂ የብቃት ማነስ አይደለም” በሚል ታዋቂ ሚዲያዎች እየተቀባበሉ ሰፊ ሃተታ እየበተኑ ነው። ይህ ለትግራይ ሕዝብ እንደ መጽናኛ ተደርጎ አፉን እንዲዘጋና አሁንም እነሱ ላቀዱት ሴራ ትህነግ የትግራይን ሕዝብ ተጠቅሞ እንዲተገብር ታስቦ እንደተዘጋጀ የሚታመነው ጽሁፍ እንደ ገና ስጦታ በቲውተር ገበታ ላይ ሲረጭ ፣ አሜሪካ በርካታ ድሮኖችንና የጦር ጀቶችን ከተወንጫፊ ሚሳይሎች ጋር አዋህዳ አፍጋኒስታንን ቀጥቅጣለች ግን አላሸነፈሽም” የሚል መከራከሪያ ወዲያውኑ ቀርቦበታል።

” ጦርነቱ አልቋል። ድብብቆሽ የለም። አዲስ አበባ እንገባለን። በሽግግር መንግስት ምስረታው ሰፊ ተሳትፎ ይኖረናል። ወደ ሞያሌ የሚያመልጡትን ኦነግ ይለቅምልናል…” እያሉ በራሳቸው ሚዲያ ሰርከስ ሲጫወቱና ” ጀጋኑ” እየተባሉ በማህበራዊ ሚዲያዎች አበባ ሲረጭላቸው የነበሩት አቶ ጌታቸው ጠላይ ሚኒስትር አብይን ለይቶ በመስደብና በማንጓጠጥ ” ያው ወደ አንድ አገር ይሄዳል ወይም ቂሊንጦ ይጣላል” ባሉበት እንደበታቸው ” አልቻልንም” ማለታቸውን ቢቢሲ አፍሪካ መስክሮባቸዋል። ብዙ ትምክህትና እብለት የተሞላበት ጽሁፍ በጻፉበት እጃቸው ” ተከበናል” ሲሉ ፊደል አወላግደው ጽፈዋል።

” ትግራይ ብቻ ናት ሰላማዊ ክልል” ሲሉ እናቶችን የገፉት ዶከተር ደብረጽዮን ” ባስቸኳይ ይተግበር” ሲሉ ባሰሙት የተኩስ አቁምና የሰላም ንግግር ጥሪ መነሻና በአቶ ጌታቸው ” ዓለም ዓቀፉ ማህበረሰ ይድረስልን” ውትወታ፣ በጥምር ሃይሉ ግስጋሴ ፍጥነት ሳምንት ሳይሆን ሲበዛ ቀን፣ ሲያንስ ሰዓታት ብዙ የግንባር አስገራሚ ዜናዎችን እያስመዘገቡ ነው።

ኮረምን እየተጠጋ ያለው ሃይል፣ በአፍር በኩል ውቅሮን ሲያሽኮረምም የከረመው የበረሃው ማእበል በዚሁ ሰዓታትና ቀን ብዙ ተለዋዋጭ ዜና በሚያሰሙበት ወቅት ላይ የሚሆነውን ከመተበቅ ውጭ ጦርነቱ ያከተመ መሆኑንን አፋቸውን ሞልተው የሚናገሩ ” ሌላ ያልተጠበቀ ስውር ሃይል ካልተነሳ በስተቀር የትህነግ ሃይል የኢትዮጵያን ጥምር ሃይሎች ሊቋቋም የሚችልበት አቅሙ ሟምቷል” ባይ ናቸው።

በሌላ ተባራሪ ወሬ ትህነግ ከሁሉም ግንባር ያሉትን ሃይሎች ወደ ማይጸብሪ ግንባር በመግፋ፣ አዲስ ሰሞኑንን ያስመረቃቸው ህጻናት አክሎ፣ ያሉትን ከባድ መሳሪያዎች አደራጅቶ የመቸረሻ የሞት ሽረት ውጊያ ሊከፍት እንደሆነ የሚናገሩ አሉ ” ይህ ለኢትዮጵያ ጥምር ሃይሎች በጸሎት የማይገኝ አጋጣሚ ነው። ከመደምሰስ ተርፎ ከየቦታው የተሰባሰበው ሃይል ወደ አንድ ግንባር ካመራ ለአፈሳጸም ያመቻል። አፈጻጸሙ ለትህነግ የጦር መሪዎች ግልጽ ነው። ያደርጉታል ብዬ አላስብም” ሲሉ ሃሳቡን ሊተገበር የማይችል ሲሉ አስተያየት ሰጪው ይገልጹታል።

በሁሉም አቅጣጫ የሰላም አግባብ የሚደገፍ መሆኑንን የሚያነሱትና በእርቅ ለበርካታ ዓመታት ያገለገሉ አስተያየት ሰጪ ቢሳካላቸው ይህንን ግልግል ተሳታፊ ሆነው ቢመሩት ደስ እንደሚላቸው አመልክተዋል። አያይዘውም “ዕርቅ ፍትህን ካጎደለ አይሆንም። እርቅና የሰላም ንግግር ፍትህ ተካቶበት ሲሆን ወንጀለኞችን እንደ ወንጀላቸው መጠን ለመቅጣት ፣ መካስ ያላባቸውን እንደጉዳታቸው መጠን ለማስታመም ይረዳል። ይህ ሲሆን እርቅ ይወርዳል። አለያ ግን እንዲህ ከተማ አውድሞና አገር አፍርሶ፣ ነጹሃንን ጨፍጭፎና ደፍሮ ፍትህ የሌለበት እርቅን መዘመር ዋጋ የለውም። የትም ይፈጸ፣ ማንም ይፈጽመው ፣ በማንም ላይ ይፈጸም … ወንጀልን ከፍትህ ለይቶ በመሳሳም ብቻ ሰላም አማውረድ አይቻልም” ብለዋል።

በትግራይ ክልል ተቃዋሚ ሆነው የሚንቀሳቀሱና ልዩ ዝግጅት እንዳደረጉ የሚናገሩ የትግራይ እናቶች ልጆቻቸውን እየጥየቁ መሆናቸውን እየገለጹ ነው። ” ለዚህ ነው የሞትነው” በሚል የሚሰማው ቅሬታ ከፍ እያለ መምታቱንና በአማራ አፋር ክልል በተፈጸመው ክብረ ነክና የትግራይ ተወላጆችን አንገት የሚያስደፋ ተርጋር የተበሳጩም ቅሬታ እያቀረቡ ነው። እነዚህ ተዳምረውና ቀደም ሲል ትህነግ ወደ መቀለ ሲመለስ ” ባንዳ” በሚል የገደላቸው ሰዎች መረጃ ለዓለም ሁሉ ይፋ የሚሆነበት መድረክ መመቻቸቱ ተሰምቷል። ይህ ሁሉ ተዳምሮ ትህነግን አታብቂኝ ውስጥ እንደሚከተው ይጠበቃል የሚሉም አሉ።


Exit mobile version