Site icon ETHIO12.COM

አፋር አበላን ለመውረር ጦርነት የከፈተው የትህነግ ሃይል ተመታ፤ ምሽጉ ተሰበረ

የአፋር ልዩ ሃይል ለዳግም ወረራ የመጣውን የትህነግ ሃይል መደምሰሱ አስታወቀ። የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር የሰላም ጥሪ አድርጎ በአፋር ክልል የፈጸመው ጥቃት በሰላማዊ ዜጎችና መሰረተ ለማቶች ላይ ያተኮረና ከርቀት ምሽግ ላይ ሆኖ ከባድ መሳሪያ በመተኮስ መሆኑ ታውቋል። ይሁን እንጂ ምሽጉ ተድርምሶ በአፋር ሃይሎች መያዙና መደምሰሱ ተመልክቷል። ትንኮሳው መንግስትን ወጥመድ ውስጥ ለመክተት ያሰበ እንደሆነ ተመልክቷል።

የትግራይ ወራሪ ሃይል በተደጋጋሚ እንደሚያደርገው ዛሬ ማለዳ ላይ በአባላ በኩል በከባድ መሳሪያ የተደገፈ ጥቃት ቢሰነዝርም እስከ ማምሻው በተደረገ ጦርነት ሙሉ በሙሉ መመታቱን ወጊያውን የመሩ አስታወቁ። ይህንኑ ተከትሎ ከትህነግ ጋር ስለ ለድርድር ማሰብ ከቶውኑ እንደማይቻል እየተገለጸ ነው።  

በጀግናው የመከላከያ ሰራዊት፣ በአማራና አፋር ልዩ ሃይል፣ እንዲሁም በሚሊሻዎች ሙሉ በሙሉ ተመቶ የተባረረው ትህነግ ከፍተኛ የሰው ሃይል ጉዳት እንደደረሰበት በራሱ የተቀናቃኝ ፓርቲ ሰዎች መገለጹ ይታወሳል። ቁሳዊና ሰብአዊ ጉዳቱን ለመሸፈን “ ለሰላም ስል ከአፋርና አማራ ክልል ወጥቻለሁ” የሚል ሰበብ አቅርቧል የተባለው ትህነግ ዛሬ ማለዳ ጀምሮ ይህን ጦርነት የከፈተበት መሰረታዊ ምክንያት ባይታወቅም “ በቀለ ነው” ተብሏል።

“በአባላ የመጣው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ፍላጎቱ ረብቲን ለመያዝ ነበር። አፋር ሰለጠነም አልሰለጠነም በአገር ጉዳይ አይደራደርም። ወጣቱና ሽማግሌው ከክልሉ  ልዩ ሃይል፣ ጋር በመሆን መክተውትና ጉዳት አድርሰውበታል” ሲሉ በስፍራው ያሉ አዋጊዎች ሲናገሩ ተሰምቷል።

አቶ ቢላህ አህመድ የአፋር ክልል የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊ አክለውም ቤተ እምነቶችንና የልማት ተቋማትን ለይቶ ማጥቃት የጀመርረው የትህነግ ሃይል በመሸገበት መደምሰሱንና ሃይል ለማጠናከር ቢሞክርም እንዳልሆነለት አመልክተዋል።

ሌላው አዋጊ መኮንን እንዳሉት “የሰው ሃይል ርብርብ እያደረገ ቢሆንም ምሽጉን አፈራርሰን ሰብረናል። መሳሪያውን ከጥቅም ውጭ አድርገናል። ሂዱና ተመልከቱ” ብለዋል።

“አፋር በፍቅር እንጂ በሃይልና በድብደባ ማስቆም አይቻልም” ያሉት አቶ ቢላህ ወራሪው ሃይል ሙሉ በሙሉ መመታቱን አመልክተዋል። ከአፋር የጠራ መረጃ በመስጠት በመስጠት የሚታውቁት ክፍሎችም በቲውተር ገጻቸው በተጠቀሰው ቦታ የአፋር ሃይሎች አመሻሽ ላይ ድል ማግነታቸውን አብስረዋል።

ዶክተር ኮንቴ ሙሳ በቲውተር ገጻቸው “የሰሜን አፋር ዋና ከተማ የሆነችው አባላ ከማለዳ ጀምሮ በትህነግ ጥቃት ሲሰነዘርባት ነበር። ከአፋር አፈግፍገናል ተብዬው ማጭበርበሪያ ነው። የፖለቲካ ጨዋታው ምንም ይሁን ምን አፋር ራሱን ለመከላከል እርምጃውን መቀጠል አለበት” ሲሉ አስታውቅወዋል። እሳቸውን ተከትለው የአፋር አክቲቪስቶችም “ከትህነግ ጋር ድርድር የሚባል ቀልድ እንደማይሰራ ይህ ማሳያ ነው” ብለዋል።

መንግስት በትህነግ ወጥመድ ውስጥ ሳይገባ ቀደም ሲል ትግራይ እንደማይገባ ማስታወቁ የፈጠረው ስሜት ይህን ጥቃት እንዳመጣው ያስታወቁ ” አሁን ላለው ትህነግ የፋር ሃይል ስለሚበዛበት ለጊዜው መንግስት አቋሙን ይዞ ከአፋር ክልል አመራሮች ጋር እንደሚመክር ይጠበቃል” ሲሉ አክቲቪስቶች ተናግረዋል። ጉዳቱንም ነሚቻለው ሁሉ ኢትዮጵያ ላይ ፊታቸውን ላዞሩት ሁሉ እንዲረዱት እንደሚደረግም ተመልክቷል።

በሌላ ዜና በሱዳን በኩል የመጣ የትህነግ ሰልጣኝ አሃይል በመከላከያ ሃይል ሙሉ በሙሉ መመታቱና ከአንድ ሰዓት በላይ መዋጋት ሳይችል መደምሰሱ የተረፈውም መሸሹ ተሰምቷል። የተማረኩም አሉ።

በዚህ በሱዳን መስመር አንድ በአየር ቅኝት ላይ የነበረ ድሮን በኢትዮጵያ እየር ሃይል ተመቶ መውደቁን ለጉዳይ ቅርብ የሆኑ አመልክተዋል። መንግስት ይህንንም ሆነ በሱዳን በኩል ሰብሮ ለመግባት ጦርነት በከፈተውና በተደመሰሰው ሃይል ጉዳይ ለጊዜው ያለው ነገር የለም።

አሜሪካና አውሮፓ የሰላም መዝሙር በሚያሰሙበት፣ ትህነግን በወታደራዊ ሃይል ለመርዳት ምክንያትና ቀዳዳ ለማበጀት እየሰሩ በለበት በአሁኑ ወቅት መንግስት ስሜታዊ ውሳኔ እንደምይወስን፣ ሁሉንም ጉዳይ ወደ አየር ይዞአ እንደማይወጣ በተደጋጋሚ ማስታወቁ ይታወሳል።


Exit mobile version