Site icon ETHIO12.COM

ህይወታቸው ካለፈ ሰባት ዓመት በሁዋላ የፕሬዚዳንቱ ሰምንት ቤተሰቦቻቸው ተገደሉ ? ትህነግን ለማንገስ ስንት ኦሮሞ ይገደል?

በኦሮሚያ መሳሪያ ይዞ ጫካ የሚያስገባ አጀንዳ የለም የሚሉት የክልሉ ተወላጆችና ፖለቲከኞች እጅግ በጣም በሚባል ደረጃ ይበዛሉ። ከተወሰነ አካባቢ ከሚነሳ መራወጥ ውጪ አብዛኛው ኦሮሚያ ሃሳቡና እምነቱ ልማት እንደሆነ ነው የሚሰማው። ለዚህም ይመስላል “ተነዳለች” ተብላ ሟርት ሲወርድባትና ነዳጅ ሲርከፈከፍባት የነበረችው ኦሮሚያ እንደተባለው ሳትሆን የቀረችው። እንደተፈራው ባይሆንም አልፎ አልፎ የሚሰማው ሃዘን ግን ዜጎችን እያስደነገጠና እያስገረመም ነው።

ትናንት በቀድሞ የኦሮሚያ ፕሬዜዳንት ዓለማየሁ አቶምሳ ቤተሰብና ጎረቤት ላይ የተፈጸመው ግድያ ከላይ የተነሳውን ጥያቄ ጎልቶ እንዲወጣ አድርጎታል። የተረፉ የቤተሰቡ አባል “ምክንያቱ ሊገባን አልቻለም” ሲሉ ለጀርመን ድምጽ ተናግረዋል። እሳቸው ብቻ ሳይሆኑ በርካቶችን ግራ ያጋባ ጉዳይ ነው።

አቶ አለማየሁ ትህነግን በመጋፈጥ የሚታወቁ፣ ሞት ባይቀዳምቸው ኖሮ ለውጡን ካመቻቹ መካከል ተብለው ይወደሱ የነበሩ የትህንግን ስንብት ከጠነሰሱ መካከል አንዱ የነበሩ፣ በክልሉ ያለውን የመሬት ወረራና የኔት ዎርክ ሙስና ለማክሸፍ ቆርተው የነበሩ፣ ባልስልታን ስለሆኑ ለቤተሰቦቻቸው ምንም ያላደረጉ የህዝብ ተሟጋች በመሆናቸው ፕሬዚዳንት በሆኑ ማግስት ጀምሮ በትህነግ የተጠሉና እስከሞቱ ድረስ ጥርስ የተነከሰባቸው ሰው ነበሩ። ይህ ጥላቻ ገሃድ እየሆነ በሚነገርበት ቅጽበት ህመማቸውና ሞታቸው የልዩነቱን ዜና ሸፍኖት የተለዩ አመራር እንደነበሩ የሚያውቋቸው ወዲያው ይፋ አድርገዋል። ታዲያ አቶ አለማየሁ እንዲህ አይነት ስብዕና ካላቸው ለምን ሸኔ ዘር ማንዘራቸው ሊያተጠፋ ወሰነ? አጀንዳውስ የማን ነው? የሚል ጉዳይ መነጋገሪያ ሆኗል።

በግድያው አባታቸውን ያጡት አቶ አዲሱ አዳባ ቤተሰቦቻቸው የተገደሉት በጥይትና ስለታማ ቁሶች ጭካኔ በተሞላበትም መንገድ መገደላቸውን አስታውቀዋል። “አሳዛኝ የግድያ ድርጊቱ የተፈፀመው ባለፈው ዓርብ ማለዳ ላይ ነው፡፡ አንድን ቤተሰብ ሳይመርጡ ነው ያገኙትን በሙሉ የፈጁት፡፡ ባንድ ጊዜ በተፈፀመ በዚሁ ጥቃት 8 የቤተሰቦቻችን አባላት አጥተናል፡፡ ሁለቱ ሰዎች ደግሞ ተጎድተው ሆስፒታል ነው የሚገኙት፡፡ ይህ በአንድ መንደር በአንድ ቤተሰብ ላይ የተፈጸመው ጥቃት ታጥቀው በአከባቢው አጎራባች ወረዳዎች በሚንቀሳቀሱት ኦነግ ሸኔ መሆኑን ነው እኛ የምናውቀው፡፡ የ75 ዓመት አጎታችን አባቴ እንዲሁም የ12ኛ ክፍል ፈተና ወስዳ ውጤቷን የምትጠባበቅ ወጣት ልጅ ከእናቷ ጋር ከተገደሉት 8 ሰዎች ናቸው፡፡” ሲል ለዶይቼ ቬለ ከተናገረው ለመረዳት ተችሏል።

እንግዲህ የአቶ ዓለማየሁን ቤተሰብ እሳቸው ከሞቱ ከሰባት ዓመት በሁዋላ ከላይ በተባለው መልኩ መጨረስ ምን የሚሉት ትግል ነው? ለኦሮሞ ሕዝብስ ምን ይጠቅማል? ኦሮሞ ኦሮሞን የሚገለውስ ማንን ለማስደሰትና ለማንገስ ይሆን? ሰለባዎቹ ግድያው ብቻ ሳይሆን ሃዘናቸውን እንኳን መቀመጥ እንዳይችሉ መደረጋቸውም ሌላው ግፍ ነው።

“… ታጣቂዎቹ የዓለማየሁ አቶምሳ ወንጅሞች ቤት የት ነው ብለው ጠይቀው መምጣታቸው ታስቦበት የተፈጸመ ግድያ አድርገን እንድንረዳ ያስገድደናል፡፡ እኛ እንደሚገባን አቶ አለማየሁ ህዝብን በአንድ አይን ያገለገሉና ቤተሰብም ምንም የተለየ ጥቅም ያላገኘበት ነው፡፡ አሁን አከባቢው ላይ ቤት ንብረቶች በመቃጠላቸው ሀዘን እንኳ መቀመጥ አልተቻለም፤ ሰው ሁሉ ተፈናቅሎ ሄድዋል” ሲሉ ለጀርመን ድምጽ በደላቸውን አመልክተዋል። ሰዎቹ ተገደሉ የአንድ መንደር ንብረት ማቃጠልና ሰብል ማውደም መዝረፍ የየትኛው ዘመን ትግል ይሆን?

ይህን ዜና የሰሙ “ቢቻል ሃሳብን በመሸጥ ላይ ተመስርቶ ለኦሮሞ ሕዝብ የተሻለ ህይወት መታገል አግባብ ነው። ትህነግን መልሶ ኦሮሚያና ኢትዮጵያ ላይ ለመትከል ኦሮሞ ኦሮሞን መጨረሱ በየትኛውም ዘመን ከግብ የማያደርስ ሩጫ ነው። የዚህ ሃሳብ አደራጆችና ከትህነግ ጋር በመሆን ኦሮሞ ኦሮሞን እንዲበላ የሚደራደሩት የሚታወቁ ናቸው” ሲሉ አካሄዱን በጥቅል ይነቅፋሉ። “ኦሮሚያ ላይ አካባቢያዊ የበላይነትን ለማስፈን የበላይ ካልሆንኩ ብሎ ከሚቃዠው ትህነግ ጋር ገጥመው የእሱኑ አጀንዳ ለማስፈጸም ምስኪን ኦሮሞዎችንም ሆነ ለዘመናት አብረው የኖሩትን የሚያስጨርሱ አካላት ቆም ብለው እንዲያስቡና ድርጊቱ ገዢ ያጣ መሆኑንን በማመን ወደ ሰላማዊ መንገድ ሊመለሱ ይገባል” በማለት ያክላሉ።

የጀርመን ድምጽ ይህንን ዘግቧል። እንዳለ ከስር ያንብቡ

የቀድሞ የኦሮሚያ ፕሬዝዳንት ዓለማየሁ አቶምሳ ቤተሰቦች ላይ አነጣጥሮ በተፈጸመው ግድያ የስምንት ሰዎች ህይወት ማለፉን የሟቾች ቤተሰቦች እና የአከከባቢው ባለስልጣናት ገለፁ። ባለፈው ዓርብ ማለዳ የተፈፀመው ጥቃት የቀድሞው ባለስልጣን ሶስት ወንድሞችን ጨምሮ በአንድ መንደር የሚኖሩ ሰባት ዘመዶቻቸውና አንድ ተጨማሪ ሰው ህይወት ሲቀጠፍ ድርጊቱንም የፈፀሙት መንግስት በአሸባሪነት የሚከሰው የኦሮሞ ነጻነት ጦር ነው ተብሏል።  

ዓርብ ታህሳስ 15 ቀን 2014 ዓ.ም ጠዋት 4 ሰዓት ገደማ በጅማ ዞን ኖኖ ቤንጃ ወረዳ ተፈጽሟል በተባለው በዚህ ጥቃት ስምንት ሰዎች ተገድለው ሁለቱ እስካሁን በሆስፒታል እርዳታ እያገኙ መሆኑ ነው በተገጂ ቤተሰቦች የተገለጸው፡፡ ከስምንት ሟቾች ሰባቱ የቀድሞው የኦሮሚያ ፕሬዝዳንት አቶ ዓለማየሁ አቶምሳ ዘመዶች ሲሆኑ አንዱ የነዚህ ቤተሰቦቻቸው ጎረቤት ናቸው፡፡ ከሟቾች ሶስቱ የቀድሞው ባለስልጣን ወንድሞች መሆናቸውን ነው ቤተሰቦቻቸው ለዶይቼ ቬለ የተናገሩት፡፡ ህይታቸው ያለፈው ሶስቱ ወንድማማቾች አቶ ሙላቱ አቶምሳ የተባሉት የ75 ዓመት አዛውንት፣ የ70 ዓመቱ አቶ ጢንቲ አቶምሳ እና የስምንት ልጆች አባት የ50 ዓመት ጎልማሳ አቶ አዳባ አቶምሳ ናቸው፡፡ በግድያው አባታቸውን ያጡት አቶ አዲሱ አዳባ ለዶይቼ ቬለ እንተናገሩት ቤተሰቦቻቸው የተገደሉት በጥይትና ስለታማ ቁሶች ጭካኔ በተሞላበትም መንገድ ነው፡፡

“አሳዛኝ የግድያ ድርጊቱ የተፈፀመው ባለፈው ዓርብ ማለዳ ላይ ነው፡፡ አንድን ቤተሰብ ሳይመርጡ ነው ያገኙትን በሙሉ የፈጁት፡፡ ባንድ ጊዜ በተፈፀመ በዚሁ ጥቃት 8 የቤተሰቦቻችን አባላት አጥተናል፡፡ ሁለቱ ሰዎች ደግሞ ተጎድተው ሆስፒታል ነው የሚገኙት፡፡ ይህ በአንድ መንደር በአንድ ቤተሰብ ላይ የተፈጸመው ጥቃት ታጥቀው በአከባቢው አጎራባች ወረዳዎች በሚንቀሳቀሱት ኦነግ ሸነ መሆኑን ነው እኛ የምናውቀው፡፡ የ75 ዓመት አጎታችን አባቴ እንዲሁም የ12ኛ ክፍል ፈተና ወስዳ ውጤቷን የምትጠባበቅ ወጣት ልጅ ከእናቷ ጋር ከተገደሉት 8 ሰዎች ናቸው፡፡”

እንደ የተጎጂ ቤተሰቦች ገለጻ አስከሬናቸው የተገኘው ስምንቱ ሰዎች ዓርብ ከሰዓቱን ወዲያ ተቀብረዋል፡፡ የአንደኛው ሟች ልጅ አቶ አዲሱ እንደሚሉት መሰል ጥቃት ያልተጠበቀና በአከባቢው በሽምግልና የታወቁ ሰላማዊ ሰዎች ላይ ነው ያነጣጠረው፡፡ ቤተሰባቸው የጥቃቱ ዒላማ የሆነበትን ምክኒያት ግን እንደማያውቁ ነው የየገለፁት፡፡

“ይህ ቤተሰብ የታጣቂዎች ዒላማ የሆነው በሁለት ምክኒያት እንደሆነ ነው እኛ እንደቤተሰብ በምላምት የተገነዘብነው፡፡ አንደኛው የዚያች ቀበሌ ሊቀመንበር የዚሁ ቤተሰብ አባል መሆኑና እሱን ፈልገው ባለማግኘታቸው ሲሆን፤ ታጣቂዎቹ የዓለማየሁ አቶምሳ ወንጅሞች ቤት የት ነው ብለው ጠይቀው መምጣታቸው ታስቦበት የተፈጸመ ግድያ አድርገን እንድንረዳ ያስገድደናል፡፡ እኛ እንደሚገባን አቶ አለማየሁ ህዝብን በአንድ አይን ያገለገሉና ቤተሰብም ምንም የተለየ ጥቅም ያላገኘበት ነው፡፡ አሁን አከባቢው ላይ ቤት ንብረቶች በመቃጠላቸው ሀዘን እንኳ መቀመጥ አልተቻለም፤ ሰው ሁሉ ተፈናቅለው ሄደዋል፡፡”

ግድያ ከተፈጸመባቸው በተጨማሪ ሌሎችም አሁን ላይ በስጋት ውስጥ መሆናቸውን ተጎጂ ቤተሰቦቹ ይናገራሉ፡፡ ቤቶችም በመቃጠላቸው ተረጋግተው ኃዘናቸውን እንኳ መቀመጥ አለመቻላቸውንም እንዲሁ፡፡

ግድያው በዚያ ቤተሰብ ላይ ያነጣጠረ መሆኑን ድርጊቱ ያሳያል የሚሉት የኖኖ ቤንጃ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ኩመራ ዲጋ ምክኒያቱን ግን ገና እያጣራን ነው ሲሉ ይመልሳሉ፡፡ በወረዳቸው ስር የምትገኘውና ግድያው የተፈጸመበት ኮንቺ የተባለች ቀበሌ ታጣቂዎች የሚንቀሳቀሱበት የምስራቅ ወለጋ ዞን ቦናያ ቦሼ ወረዳን የምታዋስን በመሆኗ እንጂ በወረዳቸው ታጣቂዎች እንደማይንቀሳቀሱም በመግለጽ፡፡ የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ኩመራ አክለው እንዳሉት ህብረተሰቡ አሁን ላይ ከአከባቢው የተፈናቀሉት የግድያውን አስከፊነት በመስጋት እንጂ የመንግስት የፀጥታ ኃይሎች አሁን ላይ አከባቢውን አረጋግተውታል፡፡

ስለዚህ ግድያ ክስ የቀረበበት መንግስት ሸነ ያለውና እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር ብሎ ከሚጠራው ታጣቂ ቡድን የማረጋገጫም ሆነ ማስተባበያ ድምጽ አልተሰማም፡፡ የአከባቢው ባለስልጣናትም በወንጀሉ ተጠርጥረው እስካሁን ተይዘው በቁጥጥር ስር የዋለ አካል መኖሩን አላረጋገጡም፡፡ ለ4 ዓመታት ገደማ የኦሮሚያ ክልልን በፕሬዝዳንትነት የመሩት አቶ ዓለማየሁ አቶምሳ፤ መጋቢት 2006 ዓ.ም. በታይላንድ በህክምና ላይ እያሉ ህይታቸው ማለፉ ይታወሳል፡፡

ፎቶ ቢቢሲ

Exit mobile version