“በአሸባሪው ህወሓት” ሲደርስባቸው የነበሩ ግፎችንና የውጭ ጣልቃ ገብነትን የሚያወግዝ ሠልፍ በሑመራ እየተካሄደ ነው


የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ አስተዳደር የሑመራ ከተማ ነዋሪዎች በአሸባሪው ህወሓት ሲደርስባቸው የነበሩ ግፎችንና የውጭ ጣልቃ ገብነትን የሚያወግዝ ሠልፍ በሑመራ እየተካሄደ ነው።

በአሸባሪው ህወሓት አገዛዝ ዘመን የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ በደሎች ደርሰውበታል፤ በርካቶች ለህልፈት ተዳርገዋል፣ ከሚኖሩበት ተፈናቅለዋል፣ አካላቸው ጎድሏል።

በሰቆቃቸው የት ነበራችሁ ያላሉ የውጭና የውስጥ ኃይሎች በወልቃይት ጠገዴ ነፃነት ላይ የተለያዩ ሐሳቦችን ማንሳት ጀምረዋል።

የአሜሪካ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች የአማራ ልዩ ኃይል ከአካባቢው መውጣት አለበትና ሌሎችን ጥያቄዎችን አንስተዋል። ከዚያም አልፎ በከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ላይ የቪዛ ክልከላ ጥለዋል።

የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ሕዝብ አሜሪካን ጨምሮ ሌሎች ኃይሎች የሚያነሱት ሐሳብ ያገኘነውን ነጻነት በመንጠቅ ወደ ዳግም ጭቆና ለመመለስ የተደረገ ነው ሲሉ ኮንነውታል፡፡

ነዋሪዎቹ ባካሄዱት ሰልፍ “በማንነታችን ላይ ተናጋሪዎቹ እኛ እንጂ የአሜሪካ መንግሥት ሊሆን አይገባም” ብለዋል። via ENA

Leave a Reply

%d bloggers like this: