Site icon ETHIO12.COM

ከባድ የውንብድና ወንጀል የፈፀሙት ሰባት ግለሰቦች በፅኑ እስራት ተቀጡ

ተከሳሾች 1ኛ, ታሪኩ ሀናቆ 2ኛ, ወልዴ አበበ 3ኛ, አምባው ሳሙኤል 4ኛ, ግርማይ ንጉስ 5ኛ, እናይ ሞገስ 6ኛ, ግርማይ መብራቱ 7ኛ, ተስፋዬ አብረሃም 8ኛ, መንበረ ገ/ስላሴ 9ኛ, ብረሃኑ ጣሰው 10ኛ, ሞገስ አበራ 11ኛ, ብረሃኑ መሰለ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢፌዴሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 32/1/ሀ/ን እና 671/ለ/ ስር የተመለከተውን በመተላለፍ በፈፀሙት ከባድ የውንብድና ወንጀል ዐቃቢ ህግ ክስ መስርቶባቸዋል፡፡

የክስ መዝገቡ እንደሚስረዳው ተከሳሾች የማይገባቸውን ብልፅግና ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ ታህሳስ 09 ቀን 2012 ዓ.ም በግምት ከሌሊቱ 10፡20 ስዓት ሲሆን በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 09 ልዩ ቦታው ወጂ ብርሀኑ ሆቴል 20/80 ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ንብረትነቱ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት የሆነውን በቆርቆሮ የተሰራ መጋዘን ተከሳሾች ከአልተያዙት ግብረ አበሮቻቸው ጋር በጋራ በመሆን ሰብረው በመግባት የተለያዩ የኤሌክትሪክ ገመዶች 1ኛ ውፍረቱ 2.5 ሚሊ ሜትር ብዛት 40 ጥቅል አጠቃላይ የዋጋ ግምቱ 60,000 /ስልሳ ሺህ/ ብር 2ኛ ውፍረቱ 4 ሚሊ ሜትር ብዛት 25 የዋጋ ግምቱ 62,500 /ስልሳ ሁለት ሺህ አምስት መቶ/ ብር 3ኛ የኤሌክትሪክ ኬብል ውፍረቱ 3በ6 የሆነ በጠኑ 800 ሜትር የዋጋ ግምቱ 80,000/ሰማኒያ ሺህ/ ብር አጠቃላይ የዋጋ ግምታቸው 202,500/ሁለት መቶ ሁለት ሺህ አምስት መቶ/ ብር የሚያወጡ ንብረቶችን ካልተያዙ ግብረ አበሮቻቸው ጋር በመሆን እየተጋገዙ ተሸክመው ሲወስዱ በጥበቃ ሰራተኞች እና በአካባቢው ፖሊሶች የተያዙ ቢሆንም ተከሳሾች ለማምለጥ በማሰብ በያዙቸው ግለሰቦች ላይ ጉዳት በማድረስ በፈፀሙት ከባድ የውንብድና ወንጀል ተከሰው ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡

ተከሳሾች በችሎት ቀርበው የዕምነት ክደት ቃለቸውን ሲጠየቁ ድርጊቱን አልፈፀምንም በማለት ክደው የተከራከሩ ስለሆነ ዓቃቢ ህግም የጠከሳሾችን ጥፋተኝነት ያስረዱልኛል ያላቸውን የሰው፤ የሰነድ እና የኤግዚቢት ማስረጃዎች አቅርቧል፡፡

ፍርድ ቤቱም ይህን ካየ እና ከመረመረ በኋላ የተከሳሾች የመከላከል መብት ተጠብቆላቸው ተከሳሾች የዓቃቢ ህግን ክስ ማስተባበል ባለመቻለቸው ችሎቱ የጥፋተኝነት ውሳኔ አስተላልፎባቸዋል፡፡ በዚህም መሰረት ፍ/ቤቱ ህዳር 09/2014 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሾችን ያርማል መሰል አጥፊዎችን ያስተምራል በማለት 1ኛ ተከሳሽ በ9 ዓመት ፅኑ እስራት 4ኛ ተከሳሽ በ10 ዓመት ፅኑ እስራት 5ኛ ተከሳሽ በ12 ዓመት ፅኑ እስራት 6ኛ ተከሳሽ በ8 ዓመት ፅኑ እስራት 7ኛ እና 8ኛ ተከሳሾች እያንዳንዳቸው በ10 ዓመት ፅኑ እስራት 9ኛ ተከሳሽ በ5 ዓመት ፅኑ እሳራት እንዲቀጡ ሲል ውሳኔ ሰቷል፡፡

Exit mobile version