Site icon ETHIO12.COM

መንግስት ለትግራይ ሕዝብ ጥሪ አቀረበ፤ አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርግ አስታወቀ

የትግራይ ህዝብ በመጀመሪያዉ ዙር ያባከነዉን የማስተዋል ጊዜ ዳግም እንዲያጤናዉ እና ራሱን ከአሸበሪዉ ሃይል ነጥሎ ለጥቅሞቹና መብቶቹ መከበር እንዲቆም ተጨማሪ እድል ለመስጠት ሲባል የመከላከያ ሃይል ወደ ትግራይ እንዳይገባ በመደረጉ ሕዝቡ ይህንን እድል እንዲጠቀም ጥሪ ቀረበለት። መንግስት ለትግራይ ሕዝብ አስፈአልጊውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑ ይፋ ሆነ።

መወሰኑንና ሰራዊቱ ነጻ ባወጣቸው አካባቢዎች መሰረቱን አፅንቶ እንዲቆይ በታዘዘዉ መሠረት ይዞታዉን በማጠናከር በነበረበት ምሽጉን ይዞ የቆመበትን ምክንያት መንግስት አብራራ።

በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ የሰጡት መግለጫ እንዳሉት የትግራይ ሕዝብ ያልበትን ችግር መንግስት በውል እንደሚረዳና አስፈአጊውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑንን ገልጸዋል። በትግራይ ያለውን ማግበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር መገንዘብ ብቻ ሳይሆን የትግራይ ሕዝብ አካል ህዝብ፣ ወይም “ሕዝባቸን ነው” ሲሉ መንግስት በጥልቅ ስሜት የህዝቡን ስቃይ እንደሚረዳና ችግሩን ለመቅረፍ እንደሚሰራ አስታውቀዋል።

የትግራይ ሕዝብ “ጥቅሞቹ እና መብቶቹ እንዲከበሩ ከተፈለገ በጦርነት ብቻ የመኖር ፍላጎትና ጥማት ያለዉን አሸባሪው የጥፋት ሃይል ዳግም የትግራይን ህፃናት በጦርነት እንዳይማግድ የሽብር ቡድኑን የጦርነትና የግጭት አባዜን ማስቆም ይኖርበታል” ሲሉ ለሕዝቡ የህሊና ዳኝነትና ውሳኔንን አሳልፈው ሰጥተዋል።

“ለጥቂት የሽብር ቡድኑ አባላት ፍላጎትና የስልጣን ጥማት ሲባል ምንም አይነት ጥቅም ያላስገኘለትን ይልቁንም ልጆቹ የተማገዱበትንና ህይወቱ እንዲመሰቃቀል ያደረገዉን ቡድን ድርጊት ማውገዝ ብቻ ሳይሆን በጥብቅ መቃወም፤ መታገል መጀመር መቻል አለበት” በማለት ዶክተር ለገሰው የትግራይ ህዝብ ካየውና ከገባበት ውጥንቅጥ አንጻር በማስላት አቋም ሊይዝ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በትግራይ ክልል፣ በሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎችና በዉጭ ያለዉ የትግራይ ማህበረሰብም የትግራይ ክልልና ህዝብ ወደ ሰላማዊ ህይወቱ እንዲመለስ፣ ማህበረ-ኢኮኖሚያዊ ችግሮቹ እንዲፈቱና ዘላቂ ጥቅሞቹ እንዲረጋገጡ የበኩለቸዉን ድርሻ መወጣት እንደሚገባቸው ሚኒስትሩ ጥሪ አሰምተዋል። ሙሉውን መየግለጫቸውን ነጥቦች ከስር ያንንቡ።

በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ የሰጡት መግለጫ ዋና ዋና ሃሳቦች፡-

1. ዳያስፖራ

• ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ባቀረቡት ጥሪ መሰረት “ኢትዮጵያ ተጣርታ አልቀርም” ብላችሁ ወደ እናታችሁ ቤት የመጣችሁ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች በሙሉ እንኳን በሰላም ለቤታችሁ አበቃችሁ፡፡ በተለያየ ምክንያት ወደ ወደ ሃገራችሁ መምጣት ያልቻላችሁና በያላችሁበት ቦታ ሆናችሁ መንፈሳችሁ እኛው ጋር የሆነዉ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች በጦርነቱ ምክንያት የተጎዱትን ወገኖቻችሁን በ eyezonethiopia.com አማካኝነት እያገዛችሁ ስለሆነ ትልቅ አክብሮት አለን፡፡

• በ “በቃ ወይም #NoMore ዘመቻ በዓለም አዳባበይ የኢትዮጵያ ድምፅና መከታ ሆናችሁ ሀገራችሁንና ህዝባችሁን አኩርታችኋል፡፡

• ኢትዮጵያ ሰው በሚያስፈልጋት ወቅት ከአቋማችሁ ሳትዛነፉ፤ ከኢትዮጵያዊነታችሁ ዝቅ ሳትሉ ሃገራችሁን ከፍ ለማድረግ እያበረካታችሁ ባለዉ አስተዋጽዖ ኢትዮጵያ አትርፋለችና ምስጋና ይገባችኋል፡፡

• መላዉ ህዝባችንም መልካም አቀባበል ከማድረግ ጀምሮ በሚሰጣቸዉ ልዩ ልዩ አገልግሎቶች ላይ የዋጋ ጭማሪዎችን ሳያደርግ፣ በኢትዮጵያዊ ባህልና ፍቅር ልጆቹን እየተቀበለ በመሆኑ ምስጋና ይገባዋል፡፡

• በርካታ የዳያስፖራ አባለት በግልና በቡድን ሆነዉ ወደ አገራቸዉ ሲመጡ በጦርነቱ ለተጎዱ ወገኖቻችን፣ ለመከለከያ ሰራዊታችን ድጋፍ የሚሆን የቁሳቁስና የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ የወገን አለኝታነታቸውን እያረጋገጡ ይገኛሉ፡፡ ይህም ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል፡፡

• በየአካበቢዉ ባለዉ የአገልግሎት አሰጣጥ መጓተትና አለመቀናጃት ላይ የሚነሱ የተወሰኑ ቅሬታዎች እንደሉም ተገንዝበናል፣

• ሀገራችሁ እንደ አዲስ እየተገነባች እንደሆነ ትገነዘባለችሁ ብለን ተስፋ እናደርጋለን፡፡ በሚቻለዉ ፍጥነትና አቅም ለማስተካከል እንጥራለን፡፡ እናንተም ለየሚመለከታቸው ተቋማት በተለያዩ ዓለማት ያዳበራችሁትን ልምድና ያበለፀጋችሁትን እዉቀት እንደምታካፍሉ ተስፋ እናደርገለን፡፡

• በጋራ ሆንን የተጋረጠብንን ፈተና በህብረ-ብሄራዊ አንድነታችን እንሻገራዋለን፡፡ የበለጸገች ኢትዮጵያንም እዉን እናደርጋለን!


2. ወቅታዊ ሁኔታን በተመለከተ ቀጣይ አቅጣጫ

• የመከለከያ ሃይላችን በዘመቻ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት በአማራና አፋር አካባቢዎች በአሸባሪዉ ሃይል የተወረሩ አከባቢዎችን ነፃ በመዉጣት የመጀመሪያውን ምዕራፍ አሳክቶና ተልእኮዉን አጠናቆ የያዘቸዉን አካባቢዎች አፅንቶ እንዲቆይ በታዘዘዉ መሠረት ይዞታዉን በማጠናከር በነበረበት ምሽጉን ይዞ ቆሟል፣

• መንግስት ወደ ትግራይ ክልል የመከላከያ ሠራዊቱ እንዳይገባ የወሰነዉ የትግራይ ህዝብ በመጀመሪያዉ ዙር ያባከነዉን የማስተዋል ጊዜ ዳግም እንዲያጤናዉ እና ራሱን ከአሸበሪዉ ሃይል ነጥሎ ለጥቅሞቹና መብቶቹ መከበር እንዲቆም ተጨማሪ እድል ለመስጠት ሲባል ነዉ፣

• በአሁኑ ወቅት የትግራይ ህዝብ በርካታ ማህበረ-ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ዉስጥ እንደሉ መንግስት መገንዘብ ብቻ ሳይሆን የህዝባችን አንዱ አካል በመሆኑ እነዚህ ችግሮቹ እንዲፈቱለት የበኩሉን ድርሻ ለመወጣት ዝግጁ ነዉ፡፡

• እነዚህ ጥቅሞቹ እና መብቶቹ እንዲከበሩ ከተፈለገ በጦርነት ብቻ የመኖር ፍላጎትና ጥማት ያለዉን አሸባሪው የጥፋት ሃይል ዳግም የትግራይን ህፃናት በጦርነት እንዳይማግድ የሽብር ቡድኑን የጦርነትና የግጭት አባዜን ማስቆም ይኖርበታል፡፡

• ለጥቂት የሽብር ቡድኑ አባላት ፍላጎትና የስልጣን ጥማት ሲባል ምንም አይነት ጥቅም ያላስገኘለትን ይልቁንም ልጆቹ የተማገዱበትንና ህይወቱ እንዲመሰቃቀል ያደረገዉን ቡድን ድርጊት ማውገዝ ብቻ ሳይሆን በጥብቅ መቃወም፤ መታገል መጀመር መቻል አለበት፡፡

• በትግራይ ክልል፣ በሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎችና በዉጭ ያለዉ የትግራይ ማህበረሰብም የትግራይ ክልልና ህዝብ ወደ ሰላማዊ ህይወቱ እንዲመለስ፣ ማህበረ-ኢኮኖሚያዊ ችግሮቹ እንዲፈቱና ዘላቂ ጥቅሞቹ እንዲረጋገጡ የበኩለቸዉን ድርሻ መወጣት ይኖርባቸዋል፡፡

• በተለይም የማህበረሰቡ አባል የሆኑ ምሁራን የመማር ፋይዳዉ የህብረተሰብን መሰረታዊ ችግር መፍታት ነዉና የትግራይ ህዝብ በአሸባሪዉ ሃይል እየደረሰበት ካለዉ ችግር እንዲላቀቅ ህብረተሰባዊ ግዴታችውን መወጣት ይኖርባቸዋል፡፡

• ለጥቂት የአሸባሪ ቡድን አበላት ጥቅምና የስልጣን ጥማት ሲባል ለሁለተኛዉ ጊዜ የተሰጠዉን ዳግም የማስተዋል እድል እንዳይመክን ከትግራይ ክልል ዉጭ ያሉ የትግራይ ተወላጆችን ጨምሮ ያገባኛል የሚሉ አካለት ሁሉ የበኩለቸዉን አበርክቶ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡


3. መልሶ መደረጃትና ግንባታ

• ከወራሪዉ ሃይል ነጻ በወጡ አካባቢዎች ተመሰቃቅሎ የነበረዉ ህይወትና ሁኔታ ወደ መደበኛ ባህሪዉ እየተመለሰ ይገኛል፣

• በእነዚህ አካባቢዎች በየደረጃዉ ያለዉ የመንግስት አስተዳደር እንደገና በአዲስ መልክ ተደረጅተዉ በተሟላ መልኩ ወደ ስራ ገብተዋል፡፡

• በአብዛኞቹ አካባቢዎች እንደ ኢትዮ-ቴሌኮም፣ ኤሌክትሪክ ሃይል፣ ባንክ ወዘተ ያሉ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ስራ ጀምረዋል፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድም በኮምቦልቻና በላሊበላ በረራ ጀምረዋል፡፡ ይህም ዓመታዊዉን የገና በዓል በታሪካዊቷ የላሊበላ ከተማ በሚገኙ ጥንታዊ አብያተ-ክርስቲያናት ለሚያከብሩ እና ጉብኝት ለማድረግ ላቀዱ ወገኞች መልካም የብስራት ዜና ነዉ፣

• ዩንቨርሲቲዎችን ጨምሮ የትምህርት፣ ጤናና የመሳሳሉት የማህበራዊ አገልግሎት ተቋማት ወደ ተጨባጭ ስራ ለመግባት የሚያስችላቸዉን ዝግጅት በማድረግ ላይ ይገኛሉ፣ አንዳንዶቹም ስራ ጀምረዋል፣ በዚህ ረገድ የአካባቢው ህብረተሰብና አስተዳደር እንዲሁም የክልል መንግስታት በትብብርና በቅንጅት እየሠሩ ይገኛሉ፣

• የመልሶ ማቋቋም መርሃ-ግብሩ በተቀናጀና ዘላቂ መፍትሄን ለማምጣት በሚያስችል ፕሮግራም መር አቅጣጫ እንዲመራ በመንግስት በኩል በትኩራት እየተሠራ ይገኛል፣

• ጦርነት በባህረዉ አዉዳሚ በመሆኑ ያደረሰብንን ጉዳት ለማካካስ በሁሉም ዘርፍ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ፣ የንግድና ገቢ አሰባሰብ ሥራን ማጠናከር ይገባናል፡፡

• በጦርነቱ ጉዳት የደረሰባቸዉ ዜጎችና ቤተሰቦቻቸውን በመስዋዕትነት ላጡ ወገኖቻችን ተከታታይ ድጋፍ ማድረግ አስፈላጊ ነዉ፡፡

• ህብረተሰቡ እነዚህን ጉዳዮች በመገንዘብ አባካኝነትን በማስወገድና ቁጣባዎችን በማጎልበት እርስ በእርስ የመረዳዳት ባህላችንን በማጎልበት የጀመረዉን ወገኑን የመታደግ እንቅስቃሴ አጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል፡፡

• ለምሳሌ ትርፍ አምራች አከባቢዎችን በጦርነትና በድርቅ ለተጎዱ አከባቢዎች ድጋፍ በማድረግ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነታቸውንና አለኝታናታቸዉን ማጠናከር አለባቸዉ፡፡

• ቀጣዮን የገናና የጥምቀት በዓላት ስናከብር አባከኝነትን ባስወገደና እርስ በርስ የመረዳዳትን ኢትዮጵያዊ ባህልን መሰረት በማድረግ መሆን ይኖርበታል፣

• ህዝቡ በተጋጋለ የአገር ፍቅር ስሜት የተፈነቃሉ ወገኖችን ለመደገፍ እየደረገ ያለዉን የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ አጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል፣

• በበጎ አድረጎት የተሰማሩ አከላትና ግለሰቦች እንዲህ አይነት የዜግነት ግዴታዎችን የሚወጡበት ጊዜ ቢኖር አሁን ነዉ፣

• ለዘላቂ እድገትና ብልፅግና ኢትያጵያን በቀጣይነት ማልማት፣ የወደመብንን ሃብትና ንብረት መልሰን መገንባትና ለየትኛዉም አይነት ፈተና ራሳችንን ማዘጋጃት ወቅቱ የሚጠይቀን የርብርብ መስክ መሆኑን በመገንዘብ ሁሉም አካላት የበኩላቸዉን መወጣት ይኖርባቸዋል፡፡


4. የህግ የበላይነትን ለማስከበር የተወሰዱ እርምጃዎችን በተመለከተ

• የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተከትሎ ከተለያዩ የሽብር ቡድኖች ጋር ግንኙነት አላቸዉ ተብለዉ የተጠረጠሩ ግለሰቦችን የፀጥታ አካለት በቁጥጥር ስር ማድረጋቸዉ የሚታወስ ነዉ፡፡

• በፀጥታ አካላት ተጠርጥረዉ ከታሰሩ ግለሰቦች ዉስጥ ከተለያዩ የሽብር ቡድኖች ጋር አብረዉ መስራታቸዉ ሀገርን እንደመካድ የሚቆጠር መሆኑን አምነዉና በድርጊታቸዉ ተፀፅተዉ ይቅርታ የጠየቁ፣ የጥፋት ደረጃቸዉ ዝቅተኛ የሆነና፣ መንግስት ከጥፋታቸዉ ተገቢዉን ትምህርት ወስደዋል ብሎ ጉዳዩን በሆደ ሰፊነት አይቶ የለያቸዉን በርካታ ሰዎች በይቅርታ እንዲለቀቁ አደርጓል፡፡

• የቀሩትም እንደሁኔታዉና የጥፋት ደረጃቸዉ እየታየ በቀጣይ የሚለቀቁ ይሆናል፡፡ ቁልፍ የጉዳዩ ተዋናዮች የሆኑት ደግሞ ለፍርድ የሚቀርቡ ይሆናሉ፡፡

• የመንግስት ዓላማ አስተማማኝና ዘላቂ ሰላም ሰፍኖ የምልአተ ህዝቡ ደህንነትና የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ ማስቻል ነዉ፡፡ ይህንን የሚገዳደሩና የሚቃረኑ ማናቸዉም እንቅስቃሴዎች ለድርድር የሚቀርብ አይደለም፡፡ ለዚህም ህብረተሰቡ ትብብርና ድጋፉን እንደወትሮዉ ሁሉ አጠናክሮ መቀጠል አለበት፡፡


5. የኮቪድ በሽታን መከለከል

• በዓለም አቀፍ ደረጃ የኮቪደ-19 የተለያዩ ቫይረሶች ወረርሽኝ ዳግም እያገረሸ መምጣቱን ተከትሎ ሀገራት በሰዎች እንቅስቃሴ ላይ ገደቦችን እየጣሉ ይገኛሉ፡፡

• በሀገራችን የጤና ሚንስቴርና የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በየጊዜዉ የሚያወጧቸዉ የሚያመለክቱት ስርጭቱ በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ መምጠቱንና አስጊ ደረጃ ላይ የሚገኝ መሆኑን የሚያመለክት ነዉ፡፡

• በመጪዉ ጊዜያት የሚከበሩ የገናና የጥምቀት በዓላት የህብረተሰብ ማሰባሰብንና መተፈፈግን የሚጋብዙ በመሆናቸዉ ህብረተሰቡም ሆነ ልዩ ልዩ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት የጤና ሚኒስቴሪና የህብረተሰብ ጤና እንስቲትዩት ያወጡዋቸዉን መመሪያዎች ለጋራ ደህንነት ሲባል በጥብቅ ማክበር ይገባቸዋል፡፡

(የመንግስት ኮሚኒኬሽን)


Exit mobile version