Site icon ETHIO12.COM

መስቀል አደባባይን በተመለከተ ቅዱስ ሲኖዶስ መመሪያ ሰጠ

ሰሞኑን በመስቀል አደባባይ የተደረገውን የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች መንፈሳዊና የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብር ላይ የተነሱ የመብትና የይዞታ ጉዳዮች ዙሪያ እንዲሁም ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስተላለፉት የተባለውን መልዕክት ተከትሎ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥር ፫ ቀን ፳፻፲፬ ዓ.ም ዓ.ም ረፋድ ዘጠኝ ሰዓት ላይ ጉባኤ አካሒዷል።


በጉባኤውም ከፍ ሲል የተገለጸውን ርዕስ መሰረት በማድረግ ሰፊ ውይይት ካደረገ በኋላ ክብርት ከንቲባዋ አርብ ጥር ፮ ቀን ፳ ፻ ወ ፲ ፬ ዓ.ም ጠዋት አራት ሰዓት በቅዱስ ሲኖዶስ መሰብሰቢያ አዳራሽ በሚካሔደው በጉባኤ ጉባዔ ላይ እንዲገኙና ማብራሪያ እንዲሰጡ ቀጠሮ አሰንዲያዝ አና ጉዳዩ በተረጋጋ መንገድ ውሳኔ እንዲያገኝ መመሪያ ሰጥቷል።


ይህ ሲኖዶሳዊ ውሳኔ የቤተክርስቲያኒቱ የመጨረሻ የሥልጣን ባለቤት የሆነው ቅዱስ ሲኖዶስ የሰጠው ውሳኔ በመሆኑ ለውሳኔው ተግባራዊነት ሁሉም ወገን የድሻውን ማበርከት የሚጠበቅበት መሆኑን በመገንዘብ ይህን ጉዳይ በተመለከተ ቅዱስ ሲኖዶስ አርብ ጥር ፮ ቀን ፳፻፲፬ ዓ.ም በሚካሔደው ጉባዔ እልባት እስከሚሰጠው ይታመናል።


ስለሆነም ቅዱስ ሲኖዶስ በጉዳዩ ዙሪያ ውሳኔ እስከሚሰጥ ድረስ ማንኛውም የቤተክርስቲያኒቱ እምነት ተከታይ ህግና ሥርዓትን ጠብቆ ቅዱስ ሲኖዶሱ የሚሰጠውን ውሳኔ ማክ በር እንደሚገባው ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን መልዕክቷን ታስተላልፋለች ሲል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ በፌስ ቡክ ገጹ አስታውቋል።(ኢኦተቤ ቴቪ)

Exit mobile version