Site icon ETHIO12.COM

እኛ እና እነሱ (ሕዝባዊ እና ፀረ-ሕዝብ)

10ኛ ዙር ሰልጣኙ ‹ደመላሽ› የሚል ስያሜ ተሰጥቷል፡፡ ወሮ-በላ እና ነፍሰ-በላ የሆነውን የትግሬ ወራሪ መንጋን መቅጫ የሕዝብ ክንድ ነው ዛሬ በባዕከር የተመረቀው፡፡ የወገን መጠቃት የአገር መደፈር የእግር እሳት የሆነበት ደም ሳይመልስ የማይተኛ የማያንቀላፋ ሕዝባዊ ክንድ ተፈጥሯል፡፡ ይህ ለአማራም ሆነ ለኢትዮጵያ አስተማማኝ ደጀን የመሆን አንድ አቅም ነው፡፡ ለወገን ኩራት ለጠላት ራስ ምታት፡፡


ቹቹ አለባቸው – OPINION

የትህነግ ዘ-ፍጥረት እንደሚያስረዳው አፈጣጠሩ ትግራይን ነፃ ለማውጣት ሳይሆን ‹አማራን ለማጥፋት› ነው፡፡ በነቢብ ‹‹የትግራይ ሪፐብሊክ›› እያለ በገቢር ግን አማራን ለማጥፋት የትርክት፣ የሥርዓትና የተቋማዊ ጥቃት አድርሷል፡፡ በአማራ መቃብር ላይ የሚያብብ የትግራይ ሪፐብሊክ አልሞ ‹ሶፍት› እና ‹ሀርድ› ፓወሩን ተጠቅሟል፡፡ ከትግራይ ሪፐብሊክ በፊት አማራን መቅበር የምንግዜም ግቡ አድርጎት ረዥም ርቀት ተጉዟል፡፡
በተለይም በአማራና በሌሎች ወንድም ሕዝቦች የጋራ ተጋድሎ ከመሀል አገር ከተነቀለ በኋላ የጦር ኃይሉን በማደራጀት ተጠምዶ ታይቷል፡፡ ትህነግ በለውጡ ማግስት ግራንድ ስትራቴጂ አድርጎ የወሰደው ጦሩን ማደራጀት ሲሆን፤ ለዚህ ተግባሩ በመከላከያ ሠራዊትና በፌዴራል ፖሊስ ተቋማት ውስጥ ያሉ የትግሬ ወታደራዊ መኮንኖችን አቅም ተጠቅሟል፡፡

የልዩ ኃይል፣ ሚሊሺ፣ መደበኛ ፖሊስ አደረጃጀቶቹን በማሻሻል በክፍለ ጦር ደረጃ አዋቅሮ ነበር፡፡ በዚህ ሳይወሰን የኮማንዶና ልዩ ኦፕሬሽን ሰልጣኞችን በሬጅመንት ደረጃ እስከማደራጀት ደርሶ ነበር፡፡ ቀደም ሲል (በአገዛዝ ዘመኑ) የኢትዮጵያን አቅም ለትግራይ ልዩነት መፍጠሪያ ሲጠቀም የነበረ ኃይል በመሆኑ ከመከላከያ ሠራዊት ካዝና ካሸሸው የጦር መሳሪያ ክምችቱ በላይ ከሱዳን፣ ሊቢያና የመን በርካታ የጦር መሳሪያ ግዥ ፈጽሞ እንደነበር ዘግይተው የወጡ መረጃዎች ያስረግጣሉ፡፡
ይህ ሁሉ ዝግጁቱ አማራን የማጥፋት ፕሮጀክቱን ወደልዩ ምዕራፍ ለማሳደግ ነበር፡፡ ለዚህ ዓላማው ጥቅምት 24 ሰሜን ዕዝን በማጥቃት የጀመረው ልዩ የጥፋት ምዕራፉ አማራን በስድስት አቅጣጫ በመውጋት ነበር የጀመረው፡፡ በቅራቅር፣ ሶረቃ፣ አብራጅራ (ምድረ-ገነት)፣ ጠለምት፣ ዋግ፣ ራያ ግንባር ቀጥተኛ ወረራ መክፈቱ ይታወሳል፡፡ በወቅቱ ከመከላከያ አልፎ በአማራ ክልል፣ በሕዝቡና በመንግሥት ላይ ጥቃት ሲፈጽም ትህነግ ለጥፋት ፕሮጀክቱ የቀረጸውን ሰራዊት ተማምኖ ነበር፡፡

ይሁንና ሕዝባችንና የክልሉ መንግሥት ባደረጉት ተጋድሎ የጥቅምቱን ወረራ በመመከት ከሰሜን ዕዝ ክፍለ ጦሮች የተወሰኑትን ከገቡበት ከበባ ማውጣት ተችሏል፡፡ ትህነግ ለዓመታት አስቦበት የገነባው ሰራዊቱ በሦስት ሳምንት ወታደራዊ መሰረተ ልማቱ ተመትቶበት ቆላ ተንቤን ሲወርድ፣ ቀጣይ ምዕራፉ ዘራፊና ወሮ-በላ (pillager) ሠራዊት ለመፍጠር አልሞ ነበር የተንቀሳቀሰው፡፡

በቅድሚያ የሀገር መከላከያ ሠራዊትን ከትግራይ ለማስወጣት እንደሕዝብ ሠራዊቱን ወግተውታል፡፡ ይህን እኔ ሳልሆን የምለው ጠላት በሰነዱ ላይ ያሰፈረው እውነታ ነው፡፡ ትህነግ ባዘጋጀው ሰነድ ላይ፡-
‹‹ጠላት (የኢትዮጵያን መንግሥት ማለቱ ነው) ጦርነቱን ክረምት ሳይገባ እጨርሳለሁ ብሎ ቢያወራም አልቻለም። ከአገር ውስጥ እስከ ዳያስፖራው፣ ከከተማ እስከ ገጠሩ በሙሉ ተጋሩ (ትግሬ ማለቱ ነው) ለወራሪው የትግራይን ምድር ረመጥ አደረገበት፣ ይህ የማይናወጠው ፖለቲካዊ ስሪታችን ውጤት ነው። ይሄንን ሃይላችንን አደራጅተን ሁሉም የየፊናውን እንዲወጣ ያደረግነው በዚህ በሰለጠነው ፖለቲካችን ነው።››
ጠላት ይህን ሲል ኢትዮጵያን በተለይም ደግሞ አማራን በቋሚ ጠላትነት ፈርጆ ነው፡፡ መከላከያ ሠራዊቱ ከትግራይ ከወጣ በኋላ ለመጨረሻው የጥፋት ፕሮጀክቱ ያዘጋቸውን ‹የትግሬ ኢንተርሃሞይ› በአማራ ምድረ ለፍጅት አሰማርቷል፡፡ ከቀዳሚው ጊዜ በከፋ ሁኔታ በጥላቻ አስተምህሮት የተበከለው የትግሬ ዘራፊ በአማራና አፋር ላይ በታሪክ ጥቁር ጠባሳ የጣለ ሰብዓዊና ቁሳዊ ውድመት አድርሷል፡፡

ወሮ-በላነትን ብቻ ሳይሆን ነፍሰ-በላነትን የአስተምህሮው አስኳል አድርጎ ህጻናት፣ አዛውንቶች፣ ሴቶች፣ አራስ እናቶችን ሳይቀር መድፈርና መግደል የተፈጠረለት ዓላማው ሆኖ ታይቷል፡፡ ፆመኛ ግን ደግሞ ገዳይ ቄስ፤ ዱዓ አድራጊ ግን ደግሞ ዘራፊ ሸህ ትግሬ ሳይቀር ለጥፋት ዓላማው አሰልፎብናል፡፡ ወሮ መብላት ሕዝባዊ ባህሪው ስለመሆኑ በተግባር አይተናል፡፡
ይህ ሁሉ መዓት በአማራ ላይ ሲወርድ የአማራ ራስን የመከላከል አቅም እያደር ማደጉ አልቀረም፡፡ በእልህና በቁጭት በኢትዮጵያዊ ጽናትና የትግል ዓላማ የተቃኘው የክልሉ የፀጥታ ኃይል በቁጥር፣ በስልጠና ጥራት፣ በአደረጃጀትና በአመራር ራሱን እያበቃ ይበልጥ ህዝባዊ ውግንናውን ተላብሶ የውጊያ አቅሙ ያደገ ኃይል ተገንብቷል፡፡ ዛሬ ከውሰት የማሰልጠኛ ተቋም ተላቆ በራሱ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ካምፖች በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰልጣኞችን በየዙሩ በማስመረቅ ላይ ነው፡፡ በተለይም ባለፈው አንድ ዓመት በዋናነት ባለፉት ሰባት ወራት አዳዲስ የልዩ ኃይል ማሰልጠኛ ካምፖች ተከፍተው የአማራ የመመከት አልፎም የማጥቃት ክንድ አቅም ተፈጥሯል፤ በመፈጠር ላይ ነው፡፡ የልዩ ኃይል ማሰልጠኛ ካምፖቻችን ፆማቸውን ማደር አቁመው ለአማራ ብሎም ለኢትዮጵያ ህልውና መከበር ዘብ የቆመ ኃይል በማምረት ላይ ናቸው፡፡
በዛሬው ዕለት 10ኛ ዙር የልዩ ኃይል ምረቃ የተካሄደበት የባዕከር ማሰልጠኛ ካምፕ ሁለተኛ ዙር ተወርቀዋሪ ኮከብ ኃይሉን ለፍሬ አብቅቷል፡፡ በዚህ ካምፕ የሚሰጠው ወታደራዊ ስልጠና በዓይነቱ የተለየ ስለመሆኑ የሰልጣኞቹ የአውደ ውጊያ ውሎ በቂ ምስክር ነው፡፡ ሕዳር መጨረሻ ሳምንት የጋሸና ምሽግ ሲሰበር ከነባሩ ልዩ ኃይላችን ጋር በመቀናጀት ብሬን ከዲሽቃ እንደክራር እየመቱ ጠላትን እንደግራምጣ የሰነጠቁት የባዕከር ምሩቆች ነበሩ፡፡

በርግጥ ልዩ ኃይላችን በመከላከያ የጦር መኮንኖችና እግረኛ ሠራዊቱ ስለጀግንነቱ የተመሰከረለት ነው፡፡ አንድ የሰራዊቱ አባል ምስክርነቱን ሲሰጥ፡- ‹‹ስለ ዐማራ ልዩ ኃይል እና ስለ ዐማሮቹ ጀግንነት የምገልፅበት ቃላት ባይኖረኘም በቻልኩት አቅምና ባገኘውት አጋጣሚ ለሁሉም ከምንመሰክረው የጦር ሜዳ ውሎየና ከወታደር ታሪኬ አንዱ ይሄው ነው። ወታደራዊ ስልጠና ብቻውን እንዲህ አያደርግም ከትውልድ የሚተላለፍ አንዳች ድፍረትና ብልሃት ቢኖር እንጅ ብየ አስባለሁ።›› ብሏል፡፡ ይህ ምስክረነቱ እዚህ ማህበራዊ ሚዲያው ላይ ሰፊ መነጋገሪያ ሆኖ እንደነበርም ይታወሳል፡፡

አዎን! የእኛ ኃይል በበርካታ የውጊያ ዓይነቶች ፍጹም ተወዳዳሪ አልተገኘለትም። አስቸጋሪ ይሆናሉ ተብለው በተገመቱ ግንባሮች ለመሰለፍ አላመነታም። ጀብዱ ለመፈፀም ካለው ብርቱ ፍላጎት የተነሳ የጠላት ጦር ይበረታባቸዋል የተባሉትን ምሽጎች ለመደርመስ ሲሽቀዳደም ደብረዘቢጥ፣ ጋሸና፣ አምባሰል፣ ደሴ ቦሩ ስላሴ፣ ሸዋ ሮቢት፣… ወዘተ ላይ ታይቷል፡፡ ሕዝብን ማነሳሳት የቻለ ሕዝባዊ ልዩ ኃይል በመገንባት ላይ ነው፡፡

10ኛ ዙር ሰልጣኙ ‹ደመላሽ› የሚል ስያሜ ተሰጥቷል፡፡ ወሮ-በላ እና ነፍሰ-በላ የሆነውን የትግሬ ወራሪ መንጋን መቅጫ የሕዝብ ክንድ ነው ዛሬ በባዕከር የተመረቀው፡፡ የወገን መጠቃት የአገር መደፈር የእግር እሳት የሆነበት ደም ሳይመልስ የማይተኛ የማያንቀላፋ ሕዝባዊ ክንድ ተፈጥሯል፡፡ ይህ ለአማራም ሆነ ለኢትዮጵያ አስተማማኝ ደጀን የመሆን አንድ አቅም ነው፡፡ ለወገን ኩራት ለጠላት ራስ ምታት፡፡

እኛ የገነባነውና በመገንባት ላይ ያለነው ሠራዊት ሕዝባዊና ዓለማቀፋዊ የጦር ሕጎችን የሚያከብር የሐገረ-መንግሥቱን ዘብ ሲሆን፤ እነሱ የፈጠሩት ወሮ-በላና ነፍሰ -በላ መንጋ ነው፡፡ መውረርን፣ መዝረፍን፣ መግደልን፣ መድፈርን በጥቅሉ በሕገ-አውሬ የሚመራ ፀረ-ሕዝብ የሆነ ዓላማ የለሽ መንጋ የፈጠረው ጠላት አጥፍቶ ጠፊነት መለያ ባህሪው ሆኗል፡፡ እኛ ከአማራ አልፎ ለኢትዮጵያ ህልውና ሠላምና መረጋጋት የሚሰራ ሰራዊት እየገነባን ነው፡፡ እነሱ ደግሞ አማራን እንደሕዝብ፣ ኢትዮጵያን እንደሀገር፣ ኤርትራን እንደሕዝብና ሀገር ለማውደም መነሻና መድረሻው ጥላቻ ብቻ የሆነ በተናካሽ እብድ ውሻ የሚመሰል መንጋ ፈጥረዋል፡፡

እኛ ለቀጣናው ሠላምና መረጋጋት የሚሰዋ ዓላማ ያለው የፀጥታ ኃይል ስንገነባ፤ እነሱ ደግሞ ቀጣናውን ለማተራመስ ለሞት የሚሰለፍ ተስፋ የለሽ መንጋ ፈጥረዋል፡፡ እዚህ ላይ አንድ እውነት እንያዝ እነሱ ተስፋና አልሚ ጉልበት ያለው ኃይላቸው እየረገፈ ወሮ መብላትን ዓላማው ያደረገ ከሁሉም ጎረቤቶቹ ጋር ደም የተቃባ ተስፋ የለሽ ሆነዋል፤ እኛ ደግሞ በርካታ አጋር ያለን ፣ የአድማሳዊ ተስፋ ባለቤትና አልሚ ጉልበታችንን በቅጡ ያልተጠቀምን የእምቅ አቅም ባለቤት ነን፡፡ እነሆ ዛሬ አስረኛው ዙር ላይ ደርሰናል፡፡ ደም-መላሻችን አስመርቀናል፡፡ የአማራም፣ የኢትዮጵያም አልፎም የአፍሪካ ቀንድ ጠላት የሆነው ትህነግ በሕዝባዊ ክንዳችን ታሪክ የሚሆንበት ጊዜ ሩቅ አይደለም፡፡

መጣ መጣ ሲሉን እንትና ነው ብለን
መጣ መጣ ሲሉን እንቶኔን አስበን
ለካስ ደምላሽ ኖሯል ትልቁ ክንዳችን!!

Exit mobile version