ETHIO12.COM

የአዲስ አበባ ማዘገጃ ቤት ዜና ፎቶ – ከሰኞ ጀምሮ ለጉብኝት ክፍት ይሆናል

እድሜ ጠገቡ የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ህንፃ ከስድስት አስርት ዓመታት በኋላ ቅርስነቱና ነባሩ ገፅታው ሳይለቅ መሰረታዊ እድሳት ሲድረግለት መቆየቱ ይታውሳል። በዚሁ ቢሊዮን ብሮች በወጣበት እድሳት አስተዳደሩ ያማረና ምቹ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ከባቢ ሁኔታ ስለመፍጠሩ አስታውቋል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ “ከተማችንን ገፅታዋን መቅየርና ዘመናዊነትን የተላበሰች ማድረግ፣ ብሎም ደረጃዋን የሚመጥን ማድረግ ዋናው ዓላማ ነበር” ብለዋል። የኢትዮጵያችን፣የአፍሪካውያን፣ የዓለም ዓቀፍ ተቋማት መቀመጫና የዲፕሎማቲክ ማዕከል የሆነችው አዲስ አበባ፣ ልክ እንደ ስሟና እንደ ተሸከመችው አህጉርና ዓለም ዓቀፍ ተግባራትዋን ለማከናወን የሚመጥናት ደረጃ ላይ የሚያስቀምጣት ስራ ተሰርቶላታል።

“ተመሳሳይ ተግባራትን መከወናችንን እንቀጥላለን” ያሉት ከንቲባዋ “ይህ ህንፃ የትውልድ ታሪክ፣ ሃብትም ቅርስም ገፀበረከትም ነው” ሲሉ ከውበቱና ከማራኪነቱ በዘለለ ታሪካዊ ፋይዳውንም አስታውቀዋል። በመሆኑም ይህ ውድ ዋጋ የፈሰሰበትና ቅርስነቱን ሳይለቅ የተዋበው የአዲስ አበባ ሕዝብ መገለገያ፣ ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ለህዝብ ክፍት የሚደረግ እንደሆነ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል። “ኑ እና ቤታችሁን ጎብኙ!!” ሲሉ ትሪ አቅርበዋል። ዛሬ በይፋ ምርቃት ይካሄዳል።

1 / 20
Exit mobile version