Site icon ETHIO12.COM

«በህወሓት ድርድር ሰነድ ውስጥ የእንገንጠል ዶሴ ላይመለስ ይዝጋልን የሚል ይገኝበታል»

ህወሓት በአፋር በኩል ተኩስ የሚከፍተው ትኩረት እንዲያገኝ ነው። የሰላም በሩን እያጨለሙቡኝ ነው ከሚል የሚመነጭ ስጋት ነው። ድርድሩ እና ከእስር የተፈቱት የህወሓት ሰዎች ለህወሓት ትርጉም የለሽ ናቸው። በስብሃት መዝገብ ውስጥ ታስረው ክሳቸው የተቋረጠላቸው ሰዎች ስለወጡ ብቻ መንግስት ከህወሓት ጋር ያለውን ጦርነት ለማቆም የወሰነ ይመስላል እንጅ ነገሩ እንደዛ አይደለም። ድርድሩ ውስጥ መንግስት ከጠየቃቸው ጥያቄዎች መካከል ህወሓት ትጥቁን ጨርሶ ይፍታ የሚል ነው።

ህወሓት ደሞ እንኳን ትጥቁን መፍታት አይደለም ከዚህ በፊት በመከላከያ ስራዊት ውስጥ የነበሩ የሱ ቁልፍ ሰዎች ሳይቀር መልሰው መከላከያውን እንዲመሩት ይጠይቃል። አቦ ሳንጆ ጋር በነበረው ድርድር ላይ ጌታቸው ረዳ እንዳይገኝ አቦ ሳንጆ ጠይቀው ጥያቄያቸው ተቀባይነት አግኝቶ ደብረጽዮን እና ኦቦ ሳንጆ ብቻ ናቸው የመከሩት።

የኦቦ ሳንጆ መማለድ እና የህወሓት ጥያቄ እንዳልተምጣጣ በአፍሪካ ህብረት ውስጥ የሚገኙ ሚስጥረኞችን ዋቢ አድርጎ
ኦን ዘደይ አፍሪካ ዘግቧል።
.
አዲስ የተሾሙት የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ የህወሓት ድርቀት እንዳስቸገራቸው ኬኒያ ላይ በነበራቸው ውይይት ላይ ተንፍሰዋል። ሆኖም ግን ጦርነቱ እንዲቋጭ መፍትሄ እንፈልጋለን የሚል መግለጫ ሰተዋል። በመንግሥት በኩል ሲወቀስበት የነበረውን ጉዳይ አመቻችቶ ጫዋታውን በመቀሌ ፖለቲከኞች እጅ አስገብቶ ቁልፉን ይዞባቸዋል።
.
ትግራይ አልገባም የሚለው የመንግስት ውሳኔ ትልቅ የፖለቲካ ትርፍ ያመጣው አሁን በሚካሄደው ውይይት ነው። ከዚህም ባሻገር የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ የሚለውም ተመሳሳይ ጥቅም አምጥቷል። የሁመራ ኮሪደር ይከፈትልኝ የሚለው ጥያቄ ብቻ ነበር የቀረው፣ እሱም መንግስት ሁመራ ላይ ህወሓት 7000 አማራዎችን ጨፍጭፏል አሁንም የቀሩትን እንዲጨርስ አለቅም ብሏል። ከዚህ በተጨማሪ 19ሺ የናይል ዘበኛ የሚለው የግብፅና የሱዳን ጥምር ጦር የሰፈረበት የሀምዳይት ግዛት አለ የሚል መልስ ሲሰጥ አሜሪካና አፍሪካ ህብረት ተመድ የኢትዮጵያን መንግስት አቋም በበጎ ይዘውታል።
.
ሂዊ አሁን በፖለቲካ ሜዳው ተበልታለች። በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ነይ ቅረቢ ሲሏት የቀረ ጥያቄ የላትም። የትግራይ ህዝብ ተራበ መንገድ ተዘጋ እንዳትል ሁሉም መንገዶች ክፍት ናቸው። ያላት አማራጭ ጦርነት እየከፈተች የትግራይን ህዝብ እያስጨረሰች አዲስ ቦታን ተቆጣጠርኩ እያለች ሌላ ትኩረት ሳቢ ነገር መፈለግ ነው። በዚህም እነ ቢቢሲ ዛሬ ህወሓት ሁለት ወረዳጅ ተቆጣጠረ የሚል ዜና ሰርተውለታል።

ምናልባት ሊቆጣጠር ይችላል። መንግስት በየቀዳዳው ጦሩን አያስቀምጥም። የኢትዮጵያ ጦር የደራጀ ጦር ነው። ተራ የሽምቅ ተዋጊ አይደለም። ህወሓት የመንግስት ጦር ባለበት ተኩስ አይከፍትም። ንፁህ የአፋር ህዝብ ቀበሌዎች ላይ እየገባ ነው የሚተኩሰው። በዚህ ምክኒያት የአፋር ህዝብ ተለይቶ ዋጋ መክፈል የለበትም። መንግስትም ይሁን የሁለቱ ክልል ሀይሎች በተጠናና በተደራጀ መንገድ ጦርነት በከፈተበት ቦታ ገብቶ የሚገርፍ አሰራር ሊኖራቸው ይገባል።
.
የቀረው ያው እንደነገርኳችሁ ነው። ህወሓት የጦርነትም የፖለቲካም ምች ተመቷል። ከዚህ የሚያገግምበት አንድ መንገድ አለው። እሱም ከተራ ትቢትና ፉከራ ወጥቶ ለህዝቡ ሲል የታጠቀውን መሳሪያ ፈቶ እጅን ለሰላም መዘርጋት ነው። በርግጥ ዶሴው አይዘጋም። መቼም ቢሆን ከተጠያቂነት አይድኑም። ይቺን እንኳን ሂዊ ሲአይኤም ያቃታል። ፈተናውም ከዚህ ይጀምራል። በህወሓት ድርድር ሰነድ ውስጥ የእንገንጠል ጥያቄው እንደዚጋ መንግስት ዶሴን ላይመለስ ይዝጋልን የሚል ይገኝበታል።

Suleman Abdela

Exit mobile version