ETHIO12.COM

አሜሪካ የ10.2 ቢሊዮን ብር ፕሮጀክቶች ይፋ ታደርጋለች

የአሜሪካ መንግሥት በአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ተራድኦ ድርጅት /USAID/ አማካይነት በኢትዮጵያ በኦሮሚያ ክልል፣ 400ሺ በላይ ሰዎችን ኑሮ ሊያሻሽል የሚችል፣ በ10.2 ቢሊዮን ብር ሁለት አዳዲስ የመዋዕለ ንዋይ ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ እንደሚያደርግ አስታውቋል።

May be an image of text

በኢፋ /Iffa/ እና በUSAID ተግባራዊ የሚደረጉ 2ቱ የመዋዕለ ንዋይ ፕሮጀክቶች በኢትዮጵያ መንግሥት የሚመራውንና 9 ሚሊዮን ሰዎች ራሳቸውን ከድህንነት እንዲያወጡ የሚያግዘውን የማኅበራዊ የምርት ደህንነት ወይም ሴፍቲኔት መርኃግብር እንደሚያጠናክር በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

በመላው ኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎች እየተካሄዱት ለሚገኙ ተመሳሳይ መርኃግብሮች ቀዳሚውን ድጋፍ እየሰጠ ያለው ዩኤስኤድ መሆኑን መግለጫው ጠቅሶ እኤአ ከ2015 ጀምሮ ወደ 60 ቢሊዮን ብር ማውጣቱን አስታውቋል፡፡

አሁን የሚካሄዱት ሁለቱ መርኃግብሮችም በአሜሪካ እና በኢትዮጵያ መካከል የቆየውን ወዳጅነትና የጋራ ፍላጎት እንደሚያረጋግጡም መግለጫው አመልክቷል፡፡

በዚህ ሳምንት ውስጥ ይፋ የተደረጉት ሁለቱ ፕሮጀክቶች USAID ባላፉት 5 ዓመታት ውስጥ በ220 ቢሊዮን ብር ኢትዮጵያ ውስጥ ተግባራዊ እያደረጋቸው የሚገኙ ፕሮጀክቶች አካል መሆናቸውንም አመልክቷል፡፡

የሚሰጠው ድጋፍ በሁሉም አካባቢ ያሉ ኢትዮጵያውያን የተሻለ ጤናማና የበለጸገ ህይወት እንዲመሩ የሚያግዝ መሆኑንም በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ መግለጫ አስታውቋል፡፡

ምንጭ፦ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ / ቪኦኤ

Exit mobile version