Site icon ETHIO12.COM

[አክቲቪስቱ] የዓለም ጤና ድርጅት መሪ በድጋሚ ክስ ቀረበባቸው

ከሚመሩት “የዓለም” በሚል የሚጠራው ድርጅት ዓላማና መርህ በማፈንገጥ ስልጣናቸውን ተጠቅመው የተራ አክቲቪዝም ስራ ላይ ተጠምደዋል በሚል የሚከሰሱት፣ በአባልነት የመዘገባቸው ትህነግ “አሸባሪ” ተብሎ የተፈረጀ መሆኑ እየታወቀና የሚመሩትን ድርጅት መርህ መጣሳቸው እየታወቀ በድጋሚ ድርጅቱን እንዲመሩ ብቸኛ እጩ መደረጋቸውን በመቃወም ተቆርቋሪዎች ክስ መሰረቱ።

በዓለም አቀፍ ደረጃ ለኢትዮጵያ ጥብቅና በመቆም የሚንቀሳቀሰው “የተቆርቋሪ ኢትዮጵያውያን” ማኅበር ለዓለም ጤና ድርጅት ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ የድርጅቱን ዋና ዳይሬክትር ሕገ-ወጥ እንቅስቃሴ በተመለከተ ደብዳቤ ጽፏል።

በደብዳቤው ዳይሬክተሩ የድርጅቱን መርሕ በመጣስ ከሙያ ሥነ-ምግባር እና ከገለልተኝነት ውጪ እየፈጸሙት ስለሚገኘው ከሥነ-ምግባር ውጭ የሆኑ ተግባራት አስረድቷል።

ዳይሬክተሩ የሚያካሂዱት ሕገ-ወጥ ተግባር የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን ታማኝነት ጥያቄ ውስጥ የሚከት መሆኑን አመልክቶ በኢትዮጵያ መንግሥት በአሸባሪነት የተፈረጀውን ድርጅት ሽፋን በመስጠት በሚያከናውኑት ተግባር ላይ ምርመራ እንዲደረግ ክስ አቅርቧል።

“ማንኛውም ሰው በእምነቱ፣ በቆዳው ቀለም እና በአካባቢው ምክንያት ጤናው የመጠበቅ መብቱን ሊያጣ አይገባም” የሚለውን የዓለም ጤና ድርጅት ሕገ መንግሥታዊ መርሕ በመጣስም ዳይሬክተሩ የተወለዱበት አካባቢን ችግር ብቻ በመጥቀስ በአሸባሪው የተፈጸሙ ወንጀሎችን እና የጤና ተቋማት ውድመቶችን መደበቃቸውን ገልጿል።

በአፋር እና አማራ ክልሎች በአሸባሪው ቡድን ወረራ ምክንያት የደረሱ ከፍተኛ ጥፋቶችን በመሸፈንም ወደ ትግራይ ክልል ሰብአዊ ድጋፍ እየገባ አይደለም በሚል ሥልጣናቸውን ተጠቅመው ክስ እያቀረቡ መሆኑን አስገንዝቧል።

በአማራ እና አፋር ክልሎች ስለ ወደሙት ከ500 በላይ የጤና ተቋማት እና ከ1 ሺ 700 በላይ የጤና ጣቢያዎች ያሉት ነገር አለመኖሩን እና በዚህም ሥራ አስፈጻሚ ቦርዱ ምርመራ እንዲያካሂድ አሳስቧል።

በተለይም በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው በኩል የዓለም ጤና ድርጅትን መርሕ በመጣስ የሚያካሂዱትን የወገንተኛ እንቅስቃሴ ቦርዱ በማስረጃነት ተጠቅሞ ምርመራ እንዲያካሂድ መጠየቁን ኢዜአ ዘግቧል።

የዓለም ጤና ድርጅት ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ድርጅቱን ዳግም ለቀጣይ አምስት ዓመታት በዳይሬክተርነት እንዲመሩ ዕጩ ማድረጉ ይታወሳል። ድርጅቱን ለሁለተኛ ዙር ለመምራት ዶ/ር ቴድሮስ ያለተፎካካሪ ብቸኛ ዕጩ ሆነው የቀረቡ ሲሆን የመጨረሻው ውጤትም ግንቦት 2014 ዓ.ም. ላይ ይፋ እንደሚሆን ታውቋል።

Exit mobile version