Site icon ETHIO12.COM

አነጋጋሪ ሹመት – ጄኔራል ባጫ ከአዲስ ተሿሚ አምባሳደሮች አንዱ ሆኑ

ዛሬ ይፋ የሆነው የአምባሳደሮች ሹመት አነጋጋሪ ሆኗል። አቶ መለስን ለማስደሰት ተቀዋሚዎችን ሲያበሻቅጡ የነበሩት የቀድሞ ዋና አፈ ጉቤ ወ/ሮ ሽታዬና የጀነራል ባጫ ደበሌ ሹመት በበርካቶች ዘንድ በሁለት መልኩ ነው ያነጋገረው። አብዛኞቹ ግን ባለሙያ ዲፕሎማት እንደሆኑ የውጭ ጉዳይ ምንጮች ጠቁመውናል።

ለቦታው እንደማይመጥኑ፣ ነገር ግን የአማራ ክልል ቅር እንዳይሰኝ ለተለመደው ፖለቲካ ሲባል ፓርቲያቸው አቅርቧቸው የውጭ ጉዳይና የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ስራ ደርበው የያዙት አቶ ደመቀ ለምንና እንዴት ባለ መስፈርት ወ/ሮ ሽታዬን ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሊያደርጓቸው እንደቻሉ ማብራሪያ ሊሰጡ እንደሚገባ አስተያየት ሰጪዎች ጥይቀዋል። አገሪቱ ውስጥ ሰው የጠፋ ይመስል እንዲህ ያለ የዕውር ድንብር አሰራር ” ህዝብ ምን ያመጣል” ከሚል እብለት የሚመነጭ በመሆኑ ፓርቲያቸውን አድሮ ዋጋ እንደሚያስከፍል ተጠቁሟል።

ይህ ሲሆን አገሪቱን የሚመራው ፓርቲና ጠቅላይ ሚኒስትሩም ዝም ማለታቸው አግባብ እንዳልሆነ እንደሚያስወቅሳቸውና ሲረግሙት የነበረውን የኮታ አሰራር እየደገሙ መሆኑ እንደሚያስተቻቸው ተመልክቷል።

ሹመት በሜሪት እንደሚሆን፣ ለዚህም ማሳያ ተቃዋሚዎች እንዲሾሙ መደረጉ እጅግ የሚበረታታ ሆኖ ሳለ በአዲሡ ሹመት የታዩ ሶስትና አራት ሰዎች ሹመት ተነቅፏል። ከወይዘሮ ሽታዬ ቀጥሎ አነጋጋሪው ሹመት የጀነራል ባጫ ሲሆን፣ ሹመቱ ቀደም ሲል “ሰው ሲጠፋ” በሚል ተሰጥቲ የነበረውን አስተያየት የሚያጸና ሆኗል። አነቃቂ ንግግር በማቅረብ የሚታወቁት “አምባሳደር ጀነራል ባጫ” ከመከላከያ እንዲቀየሩ መውሰን የመንግስት ውሳኔ ቢሆንም አምባሳደርነት የጡረታ ስፍራ አይደለምና አሁንም ሹመቱን ሰባራ አሰኝቶታል። ለሁሉም የተሰጠው ሹመት ይህን ይመስላል። በሹመቱ አብዛኞቹ በሂደት የመጡ ዲፕሎማት እንደሆኑ ተመልክቷል።

በባለሙሉ ባለስልጣን አምባሳደርነት የተሾሙት ግለሰቦች

በአምባሳደርነት የተሾሙት ግለሰቦች

Exit mobile version