Site icon ETHIO12.COM

ፈረንሳይና አሜሪካ 8.3 ሚሊዮን ዶዝ የኮቪድ ክትባት ሰጡ

ፈረንሳይ ለኢትዮጵያ 6 ነጥብ 7 ሚሊየን ፣ አሜሪካ ደግሞ 1.6 ዶዝ የኮቪድ-19 ክትባት ድጋፍ ማድረጋቸው ተገልጿል። ድጋፉ በኢትዮጵያ ወረሽኙ እየተስፋፋ ከመሄዱ አንጻር ወቅታዊና አስፈላጊም መሆኑ ተመልክቷል።

ፈረንሳይ ያደረገቸውን ድጋፍ ኢትዮጵያ በኮቫክስ ጥምረት አማካኝነት በተያዘው ሳምንት መረከቧን በኢትዮጵያ ከፈረንሳይ ኤምባሲ ያገኘነው ያሰራጨው ዜና ያስረዳል።

በተመሳሳይ አሜሪካ ፋይዘር የኮቪድ-19 ክትባት ድጋፍ አድርጋለች። ድጋፉ 1 ሚሊየን 680 ሺህ 120 የዶዝ ብዛት እንዳለው ተገልጿል። ፉ የባይደን -ሃሪስ አስተዳደር የኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝን ለመከላከል የሚያደርገው አለም አቀፍ ጥረት አካል መሆኑን በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ አስታውቋል።

Exit mobile version